በመጠጥ ውስጥ በመደበቅ ችግርን መርሳት አምላክ ያዝዛልን?

 


17. ምሳሌ 31፡5-7 “ለሚጠፉት የሚያሠክር መጠጥ፣ በስቃይ ላሉትም የወይን ጠጅ ስጧቸው፤ ጠጥተው ድህነታቸውን ይርሱ፤ ችግራቸውንም ከእንግዲህ አያስቡ” ይላል፡፡ በመጠጥ ውስጥ በመደበቅ ችግርን መርሳት ዘላቂ መፍትሄ ነውን? ወይስ ጥፋት? እውን ይህ የአምላክ መጽሐፍ የሚያዘው ነገር ነውን? አምላክ ወደ ጥፋት ያዛልን?

መጽሐፍ ቅዱስ ስካርን አጥብቆ ይከለክላል (1ቆሮንቶስ 6፡10)፡፡ ነገር ግን አልኮልን ለመድኃኒትነት መጠቀም አይከለክልም (1ጢሞቴዎስ 5፡23፣ ሉቃስ 10፡34)፡፡ በጥንት ዘመን ማደንዘዣ መድኃኒቶች ስላልነበሩ በህመም ለሚሰቃዩ ሰዎችና ሥነ ልቦናዊ ችግሮች ለደረሱባቸው ሰዎች የወይን ጠጅ ይሰጣቸው ነበር፡፡ ይህ ደግሞ የህመም ስቃያቸውን ስለሚያስታግስላቸው ሰናይ እንጂ እኩይ አይደለም፡፡ “ድህነታቸውን” ተብሎ የተተረጎመው የእብራይስጥ ቃል “አማል” የሚል ሲሆን ሥቃይ፣ መከራ፣ ድካም፣ የሚሉ ትርጉሞች አሉት፡፡[2]