ኢየሱስ ለዘለዓለም ድነት የሆነውን ወንጌል ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያ ድርስ በደቀ መዛሙርቱ አማካኝነት የተላከው ወንጌል የት ሄዶ ነው ሌላ የተጻፈው?

 


12. በቀላል ትርጉም የ1980 እትም መጽሐፍ ቅዱስ የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ቁጥር 8 ሥር በቀረበው የግርጌ ማስታወሻ ላይ “በአያንዳንድ የጥንት መጽሐፍት በዚህ ምዕራፍ በቁጥር 8 ቀጥሎ ያለው ቃል ይገኛል” ይልናል የሚከተለውን አስፍሯል፦ “ሴቶቹ ወደ ጴጥሮስና ወደ ጓደኞቹ ሄደው መልአኩ የነገራቸውን ሁሉ አወሩላቸው፣ ከዚያ በኋላ ኢየሱስ እራሱ ለዘለዓለም ድነት የሆነውን የማይለወጠውንና ቅዱስ ወንጌል ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያ ድርስ በደቀ መዛሙርቱ አማካኝነት ላከ” ይላል፡፡ ያ የተላከው ወንጌል የት ሄዶ ነው ሌላ የተጻፈው? ጠፋ? በጉባኤ ድምፅ ብልጫ ውድቅ ተደርገ?

በእርግጥ ይህ ጥቅስ በማቴዎስና በሉቃስ ጽሑፎች ውስጥ የሚገኙትን የታላቁ ተልዕኮ መልዕክታት ጨምቆ የሚያቀርብ ቢሆንም ተዓማኒ በሆኑት ጥንታዊ የማርቆስ ወንጌል ቅጂዎች ውስጥ አይገኝም፡፡ ቢሆንም ግን የጠያቂውን የተሳሳተ መረዳት የሚያንጸባርቅ ምንም ነገር በዚህ ቦታ አይገኝም፡፡ ኢየሱስ በደቀ መዛሙርቱ አማካይነት የላከው ወንጌል (የምስራች) የተጠረዘ ወይም የተጠቀለለ መጽሐፍ ሳይሆን የአዳኝነቱን መልዕክት ነው፡፡ ይህ መልዕክት ነው ከጊዜ በኋላ በመጽሐፍ የሰፈረው፡፡