ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው ያለውን የጌታ የኢየሱስን ቃል እናስታውስ” የሚለው በአራቱም ወንጌሎች ውስጥ ቢፈለግ አይገኝም

 


19. “የሐዋርያት ሥራ 20:35 ላይ “በጉልበታችን ደክመን ችግረኞችን መርዳት እንዳለብም ባደርግሁት ሁሉ አሳይቻለሁ፡፡ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው ያለውን የጌታ የኢየሱስን ቃል እናስታውስ” ይላል፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ይህንን ያለበት ስፍራ በአራቱም ወንጌሎች ውስጥ ቢፈለግ አይገኝም፡፡ ታድያ ጳውሎስ ከየትኛው ወንጌል ይሆን ይህን ያገኘው? ምን አልባት በጉባኤና በድምፅ ብልጫ ካልተመረጡ ወንጌላት መካከል ይሆንን?

ኢየሱስ የተናገረውና ያደረገው በአራቱ ወንጌላት ውስጥ የተጻፈው ብቻ እንደሆነ የተናገረ ማንም የለም፡፡ ነገር ግን ጌታችን ስለ መስጠት አስፈላጊነት በተደጋጋሚ ስላስተማረ ይህ ቃል በወንጌላት ውስጥ አለመመዝገቡ ምንም የሚያጎድለው ነገር የለም (ሉቃስ 6፡38፣ )፡፡ የኢየሱስ ንግግሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እስከተጠቀሱ ድረስ በአራቱ ወንጌላት ውስጥ ብቻ እንዲሰፍሩ የሚያስገድድ ምን ሁኔታ አለ? አሕመዲን ጀበል “በድምፅ ብልጫ ስለተደረገ ምርጫ” ደጋግመው ቢናገሩም አንድም ጊዜ ማስረጃ እንዳልጠቀሱ ልብ በሉ! “ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል” የሚለውን ብሂል ከልባቸው የሚያምኑ ይመስላሉ፡፡

  • ወንጌሎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርው ተጻፋ ብለው ያምናሉን? ወንጌሎች ይህንን ያረጋግጣሉን? እንደውም በተቃራኒ ቢያረጋግጡስ?

ቁርኣን ከላይ የወረደ መገለጥ ነው ብለው ያምናሉን? ቁርኣን “ወርጃለሁ” ከሚለው ባዶ ንግግር ባለፈ ይህንን ያረጋግጣልን? በተቃራኒው ቢያረጋግጥስ?