ጳውሎስ ደብዳቤዎቹን ያኔ ጽፎ ሲልክ ዛሬ እንደሆነው ለዓለም አስቦ ነበርን?
20. ጳውሎስ ደብዳቤዎቹን ያኔ ጽፎ ሲልክ ዛሬ እንደሆነው ለዓለም አስቦ ነበርን? ቢሆንማ ለምን አንዴም ቢሆን ለኢትዮጵያ/አፍሪካ ወዘተ. አልላከም? የተጻፈው ለዓለም ከሆነ ለምን “ለቆሮንቶስ”፣ “ለሮሜ”፣ “ለገላትያ”፣ “ለኤፌሶን ሰዎች” ወዘተ. ተላከ?
ዋናው ቁምነገር ጳውሎስ ማሰብ አለማሰቡ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ በእርሱ መጠቀሙ ነው፡፡ የጳውሎስ መልእክቶች በወቅቱ ክርስትናን ለተቀበሉት ሕዝቦች የተጻፉ ነበሩ፡፡ የጳውሎስ መልእክቶች ለተጠቀሱት አብያተ ክርስቲያናት የተላኩ ቢሆኑም ነገር ግን ዓለም አቀፋዊ ይዘት ስላላቸው ከዚያን ዘመን ጀምሮ እስከዚህ ዘመን ድረስ ላሉት በዓለም ዙርያ ለሚገኙት ክርስቲያኖች ሁሉ መመርያ ለመሆን በቅተዋል፡፡ ይህም የመልዕክቱ ደራሲ ሐዋርያው ጳውሎስ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ያሳያል፡፡ ቁርኣን ለዓለም ሁሉ የተላከ መጽሐፍ ከሆነ ለምን በሙሐመድ ዘመን በአረብያ የተከናወኑት ጉዳዮች ላይ ብቻ ያተኩራል? ባለፈው ክፍለ ዘመን በካይሮና በአማን በተደረጉት ስብሰባዎች ላይ ሙስሊም ሊቃውንት እስኪፈቅዱ ድረስ ወደ ሌሎች ቋንቋዎች መተርጎም ስለምን ተከልክሎ ቆየ?[36]