ኢየሱስ “የእኔ ትምህርት ከእግዚአብሔር ወይም ከራሴ እንደመጣ” ሲል ራሱንና እግዚአብሔርን ለይቶ ከተናገረ ስንት አምላክ አለ?

 


29. እንደ ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 7 ከቁጥር 16-17 ከሆነ፡- «ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፡- የማስተምረው ትምህርት ከራሴ ሳይሆን ከላከኝ የመጣ ነው፡፡ ማንም የእግዚአብሔር ፈቃድ ለማድረግ ቢፈልግ የእኔ ትምህርት ከእግዚአብሔር ወይም ከራሴ የመጣ መሆኑን ለይቶ ያውቃል፡፡» ሲል ተናግሯል፡፡ በዚህ ጥቅስ ላይ ኢየሱስ «ከእግዚአብሔር ወይም ከራሴ» ሲል እግዚአብሔርና እርሱ የተለያዩ መሆናቸውን አስረድቷል፡፡ ታዲያ ኢየሱስና እግዚአብሔር የተለያዩ ከሆኑ ክርስቲያኖች ስንት አማልከትን ነው እየተገዙ ያሉት? ኢየሱስን ወይስ እግዚአብሔርን?

እኛ በሦስት አካላት የተገለጠ አንድ አምላክ ነው የምናመልከው፡፡ ወልድ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ መለኮትነቱ ባይቋረጥም ፍፁም ሰው ሆኖ ስለተመላለሰ የራሱን ፈቃድ ለአብ በማስገዛት እንደ አገልጋይ ተመላልሷል፡፡ ከላይ የተጠቀሰውን ቃል የተናገረው ከዚያ አኳያ ነው፡፡

 

 

ለአሕመዲን ጀበል 303 ጥያቄዎች የተሰጠ መልስ ማውጫ