ኢየሱስ አምላክ ከሆነ አምላክ በገነት ውስጥ ከሰዎች ጋር አብሮ ምግብ ይበላል?

 


40. ማቴዎስ 26:29 ላይ «በአባቴ መንግስት አዲሱን የወይን ፍሬ ጭማቂ ከእናንተ ጋር እስከምጠጣበት ቀን ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ የወይን ፍሬ ጭማቂ ዳግመኛ አልጠጣም እላችኋለሁ» ይላል፡፡ ኢየሱስ አምላክ ነው ካልን ነገ አምላክ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ገነት ገብቶ የወይን ጭማቂ ሊጠጣ ነው? አምላክ ገነት ይገባል ወይንስ ያስገባል?

አምላክ ገነት የመግባትም ሆነ የማስገባት መብት አለው፡፡ ገነት ውስጥ ተገኝቶ ከሕዝቡ ጋር መሆኑ አምላክነቱን ውድቅ የሚያደርገው እንዴት ሆኖ ነው? የእግዚአብሔር የማዳን ዓላማ የሰው ልጆችን በሙሉ በፍጥረት ጅማሬ ላይ ወደነበረው ወደዚያ ፍፁም ወደሆነ ሕበረት መመለስ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ በመስቀል ላይ ዋጋን በከፈለው በከበረው የትንሣኤ አካል ሆኖ ፊቱን እያየን በመንግሥተ ሰማያት ውስጥ እንደምንኖር ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ይህ ከሁሉም የላቀ ደስታን የሚያጎናፅፍ የክርስቲያኖች ተስፋ ነው፡፡ የትንሣኤ አካሉ መለኮታዊ ክብርን ከመጎናፀፉ ሌላ ከኛ የትንሣኤ አካል የተለየ ባለመሆኑ “አዲሱ የወይን ጠጅ” ተብሎ የተጠቀሰውን ሰማያዊ “የወይን ጠጅ” መጠጣትን ጨምሮ እኛ በመንግሥተ ሰማያት ውስጥ ማድረግ የምንችላቸውን ነገሮች ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡ በቁርኣን ውስጥ የተገለፀው የሙስሊሞች ገነት ግን የወይን ጠጅ እንደ ልብ የሚጠጣበት ቦታ ከመሆኑም በተጨማሪ ሙስሊም ወንዶች ቁጥር ስፍር ከሌላቸው ሴቶች ጋር ፍትወት እየፈፀሙ የሚኖሩበት ቦታ መሆኑን ቁርኣን ይናገራል፡፡[11] በእስላማዊ ትውፊቶች ውስጥ ደግሞ አንድ ሙስሊም ወንድ በገነት ከ72 ሴቶች ጋር ጋብቻ እንደሚፈፅም ተጽፏል፡፡[12] ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በገነት እንዲህ ያለ ነገር አለመኖሩንና እንደ መላእክት በደስታ እንደምንኖር ነግሮናል (ሉቃስ 20:34-36፣ ዮሐንስ 14፡1-3)፡፡

 

 

ለአሕመዲን ጀበል 303 ጥያቄዎች የተሰጠ መልስ ማውጫ