መንፈስ ቅዱስ ደግሞ እናቱ ማርያን ካስጸነሰ (ማቴዎስ 1፡1-20 ፤ ሊቃስ 1፡35) ኢየሱስ ስንት አባት ነዉ ያለዉ?

 


82. ከሥላሴ አንዱ አብ ለሌላኛዉ (ለኢየሱስ) አባት ነዉ ይባላል፡፡ ሌላኛዉ የሥላሴ አባል የሆነዉ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ እናቱ ማርያን አስፀንሷል (ማቴዎስ 1፡1-20 ፤ ሊቃስ 1፡35) ታዲያ ኢየሱስ ስንት አባት ነዉ ያለዉ?

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድመ ተሠግዎ ከአብ ጋር እንደነበር በቁጥር 81 ላይ በማስረጃዎች አስደግፈን ገልጠናል፡፡ ወደ ዓለም የመጣው ተዓምራዊ በሆነው ልደቱ አማካይነት ቢሆንም አብ አባቱ የሆነው ወደዚህች ምድር እንደ ሰው ተወልዶ በመምጣቱ አይደለም፡፡ ብፅዕት እና ንፅህት ከሆነችው ከማርያም የመወለዱን ተዓምራዊ ሂደት መንፈስ ቅዱስ መከወኑ መንፈስ ቅዱስን የኢየሱስ አባት ካሰኘው ከሞላ ጎደል ፈጠራ በሆነው የቁርኣን ታሪክ መሠረት ዒሳ ከመርየም እንዲወለድ የማድረጉን ተግባር የከወነው ጂብሪል በመሆኑ ጂብሪል የዒሳ አባት ሊሆን ነው (ሱራ 19፡21-22)፡፡ ቁርኣን በግልፅ እንዳስቀመጠው ጂብሪል በእስትንፋሱ አማካይነት ዒሳ እንዲፀነስ አድርጎ ሳለ አሕመዲን ጂብሪልን የዒሳ አባት ብለው ካልጠሩት የጌታችንንም ልደት በዚያው መልኩ መረዳት ስለ ምን ተሳናቸው? በሁለት ሚዛን በመመዘን ማወናበድ ለምን ይሆን ያስፈለጋቸው?