ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት ስሙ ማን ነበር?

 


84. ማርያም ፀንሳ ሳለ “ኢየሱስ” የሚለዉን ስያሜ እንደምታወጣለት ተገልጧል፡፡ በእርሷ ይህንን ስያሜ ከመሰጠቱ በፊት እዉን ኢየሱስ ከነበር ማን ነበር ስሙ?

ለዚህ ጥያቄ ሐዋርያው ዮሐንስ እንደሚከተለው መልስ ይሰጣል፡- “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፡፡ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ… ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን፡፡” (ዮሐንስ 1፡1-3፣ 14)

ሥጋ ከመሆኑ በፊት ኢየሱስ “እግዚአበሔር” እና “ቃል” (ሎጎስ) ተብሎ መጠራቱን ሐዋርያው ይነግረናል፡፡ “ኢየሱስ” የሚለውን ስም እና “ክርስቶስ” የሚለውን ማዕርግ ያገኘው ከተሠግዎ በኋላ ነው፡፡