ድንግል ወንድ ልጅ ትወልዳለች ከተባለ! ታዲያ ‹‹ድንግል አምላኳን ወለደች›› የሚለዉ ከየት መጣ?

 


88. ማቴዎስ 1፡23 ላይ “እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፡፡ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው፡፡” ይላል፡፡ ድንግል ምን ትወልዳለች ተባለ? ወንድ ልጅ! ታዲያ ‹‹ድንግል አምላኳን ወለደች›› የሚለዉ ከየት መጣ?

ድንግል የወለደችው ወንድ ልጅ አማኑኤል (እግዚአብሔር ከእኛ ጋር) ተብሏል፡፡ ለዚህ ነው ክርስቲያኖች ድንግል አምላኳን እንደወለደች የሚናገሩት፡፡ የተጠቀሰው ጥቅስ ራሱ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ያሳያል፡፡