እስራኤላዊያን በኢየሱስ አያምኑም ግን ሮሜ 11:26 እስራኤል ሁሉ ይድናሉ” ይላል፡፡ ታድያ በኢየሱስ ሳያምኑ ዳኑ?

 


97. ሮሜ 11:26 “ስለዚህ እስራኤል ሁሉ ይድናሉ” ይላል፡፡ እስራኤላዊያን ግን ያኔ በኢየሱስ ዘመንም ሆነ ዛሬ በኢየሱስ ክርስቶስ አላመኑም፡፡ የአይሁድ እምነት (ጁዳይዝምን) ተከታይ ናቸው፡፡ ታድያ በኢየሱስ ሳያምኑ ዳኑ? ወይስ ጥቅሱ ውሸት ነው?

የመጀመርያዎቹ ክርስቲያኖች እስራኤላውያን ነበሩ፡፡ ኢየሱስ ራሱ እስራኤላዊ ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ አይሁድ ክርስቲያኖች በመላው ዓለም ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ ኢየሱስን እንደካዱ በጅምላ መናገር ስህተት ነው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ እስራኤል ሁሉ መዳን ሲናገር በዘካርያስ 12፡10 ላይ በተጻፈው መሠረት እስራኤል ብሔራዊ ንስሐ በማወጅ ከእግዚአብሔር ጋር ስትታረቅ እና ወደ መሲሁ ስትመለስ የሚኖረውን ትውልድ ለማለት እንጂ በዘመናት መካከል መሲሁን ክደው ክፋትን እያደረጉ የኖሩትን ሁሉ ለማለት አይደለም፡፡