ኢየሱስ የፍጡር ስም? አላህ የፍጡር ስም?

ኢየሱስ የፍጡር ስም? አላህ የፍጡር ስም?


አንዳንድ ሙስሊሞች ኢየሱስ በሚለው ስም የተጠሩ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኙ ኢየሱስ የፍጡር ስም ነው ይሉናል። ኢየሱስ የስሙ ትርጉም “ያሕዌ አዳኝ” ማለት በመሆኑ ምክንያት ለፈጣሪ ተገቢ የሆነውን ስም ለፈጣሪያቸው ክብር ፍጡራን ተሸከሙት እንጂ በትርጉም ደረጃ ወደ ፍጡራን የሚያመለክት ስም አይደለም። ሰዎች በዚህ ስም ሲጠሩ ስሙ መታወቂያ ቢሆናቸውም የሚያስተላልፈው መልእክት ወይም ትርጉሙ ወደ ፈጣሪ እንጂ ወደ ፍጡራን አያመለክትም። ነገር ግን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ስም ሲጠራ የስሙ ትርጉም ሙሉ በሙሉ እርሱን እንደሚያመለክት አምላክ እንጂ እንደ ፍጡር አይደለም። ይህ መሆኑ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፏል:-

ማቴዎስ 1:21 “ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።”

ጌታችን ከኃጢአት ስለሚያድን ነው በዚህ ስም  የተጠራው። ከኃጢአት የሚያድን ደግሞ አምላክ ብቻ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ በዚህ ስም መጠራቱ እርሱ ከኃጢአት የሚያድን ያሕዌ መሆኑን ከማልከት አንጻር ሲሆን ሰዎች በዚህ ስም የተጠሩት ስሙ የተሸከመው ትርጉም ወደ ራሳቸው ሳይሆን ወደ ያሕዌ በሚያመለክት መንገድ ነው።

በቀጣይ የሙስሊሞችን ተመሳሳይ ሎጂክ ተጠቅመን “አላህ የፍጡር ስም” በምትል አጭር ጽሑፍ እንገናኛለን።



አላህ የፍጡር ስም?


ሙስሊም ወገኖቻችን ኢየሱስ የሚለው ስም ለሰዎች መጠርያ ሆኖ ያገለገለባቸው አጋጣሚዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኙ የፍጡር ስም ነው የሚል ሙግት እንደሚያቀርቡ ከዚህ ተመልክተናል፤ ምላሻችንንም አስቀምጠናል። አሁን ደግሞየእነርሱኑ ሎጂክ ተጠቅመን አላህ የሚለው ስም የፍጡር ስም መሆኑን እናስረዳለን።

ሙስሊም ወገኖቻችን ትክክለኛው የፈጣሪ ስም አላህ መሆኑን ለማስረዳት ከእብራይስጥና ከአራማይክ ጋር በማገናኘት ሲሞግቱ ይታያሉ። የተያዩ ምሑራዊ ምንጮችን ስንመለከትም አላህ የሚለው ቃል አል-ኢላህ የሚለው ቃል እጥርጥር መሆኑንና ሴማዊ ስረመሠረት ካላቸው ቃላት ጋር ተያያዥ መሆኑን እንገነዘባለን። ቃሉም “አምላክ” ተብሎ የሚተረጎም እንጂ የተፀውዖ ስም አለመሆኑን እንረዳለን። ለምሳሌ ያህል የኢስላም ባሕረ ዕውቀት እንዲህ ይላል፡-

Allah is the Arabic equivalent of the English word God, and is the term employed not only among Arabic-speaking Muslims but by Christians and Jews and in Arabic translations of the Bible. A contraction of al-ilah, meaning “the god,” Allah is cognate with the generic pan-Semitic designation for “God” or “deity” (Israelite/Canaanite El, Akkadian ilu) and is particularly close to the common Hebrew term Elohim and the less frequent Eloah. It is thus, strictly speaking, not a proper name but a title. (Richard C. Martin, Encyclopedia of Islam and the Muslim World, p. 39)

ኤል፣ ኢሉ፣ ኤለሂም፣ ኤሎሃ፣ የሚሉት ሁሉ “አምላክ” የሚል ትርጉም ያላቸው የወል ስሞች አንጂ የተጸውዖ ስሞች አይደሉም። አላህ ወይም አል-ኢላህ የሚለው ቃል ተመሳሳይ ስረ መሠረት ያለው የወል ስም እንጂ የተጸውዖ ስም አይደም። ሙስሊም ወገኖቻችን ይህ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙት የእብራይስጥና አራማይክ ቃላት ጋር እንደሚገናኝ ዕውቅና መስጠታቸው ቃሉ በብቸኝነት እውነተኛውን አምላክ እንደሚጠቅስ መናገራቸው ስህተት መሆኑን ያሳይል። ከላይ የተዘረዘሩት “አል-ኢላህ” ከሚለው ቃል ጋር አንድ ስረ መሠረት የሚጋሩት ቃላት እውነተኛውን አምላክ ብቻ ሳይሆን ሰብዓውያን ፈራጆችን፣ መላእክትንና ጣዖታትንም ጭምር ለማመልከት ጥቅም ላይ ውለዋልና።

ቅድመ እስልምና የነበሩት አረቦች ቃሉን ከብዙ አማልክት (ኢላህ) መካከል አንዱና ትለቀኛው አድርገው ለሚያመልኩት አምላክ (አል-ኢላህ) ይጠቀሙት እንደነበረ ምሑራዊ ምንጮች ያሳያሉ፡-

Historical evidence indicates that Allah was the name of an ancient Arabian high god in a pantheon of other gods and goddesses like those found in other ancient Middle Eastern cultures. Worshipping him as the only real god may have started before the seventh century in Arabia, but it was in the Quranic revelations delivered by Muhammad as the prophet of Islam between 610 and 632 that the monotheistic ideal received its first clear expression among Arab peoples. (Campo, Encyclopedia of Islam, p. 34)

ቅድመ እስልምና አረብ ጣዖታውያን ትልቀኛው አምላክ አድርገው ያመልኩ የነበሩትና የካዕባ ትልቀኛው አምላክ ሁባል ነበር፡-

The religion of the pre-Islamic Bedouin was primarily animistic, while urban populations, such as the Meccans, worshiped a supreme God, al-Ilah, and its three daughters, al-Uzza, al-Lat, and Manat. Hubal was the chief deity of the Kaba. (Richard C. Martin, Encyclopedia of Islam and the Muslim World, p. 370)

ቅድመ አረብያ እስልምና አላህ የሚባለው አምላክ ሦስት ሴት ልጆች እንዳሉት ይታወቃል፤ እነዚህም አል-ላት፣ መናትና ኡዛ በመባል ይጠራሉ። “አል-ላት” “አል-ላህ” የሚለው ቃል ሴቴ ፆታ ሊሆን እንደሚችል ሊቃውንት ይናገራሉ፡-

The three most popular goddesses in preIslamic Arabia were al-Lat, Manat, and al-Uzza, sometimes called the daughters of Allah. Al-Lat (possibly the female counterpart of the Arabian high god Allah) was worshipped by Arab tribes in much of the peninsula. (Campo, Encyclopedia of Islam, p. 265)

ከዚህ ምን እንረዳለን? አላህ የሚለው ቃል እውነተኛውን አምላክ ብቻ ሳይሆን ሰዎችን፣ ጣዖታትንና መላእክትን ለማመልከት ጥቅም ላይ ከዋሉት ሴማዊ ቃላት ጋር አንድ ስረ መሠረት የሚጋራ ቃል ነው። አረብ ጣዖታውያንም ከሁሉም ትልቅ ብለው የሚያስቡትን ጣዖት ለመጥራት ይጠቀሙበት ነበር። ስለዚህ በሙስሊም ወገኖች ሎጂክ መሠረት አላህ የፈጣሪ ስም ብቻ ሳይሆን የፍጡራንም ስም ነው ማለት ነው።

 

መሲሁ ኢየሱስ