ሙሐመድ አብድ ወረሱል አ-ሸይጧን! – ሙሐመድና አጋንንታዊ ልምምዶቹ

ሙሐመድ አብድ ወረሱል አ-ሸይጧን!

ሙሐመድና አጋንንታዊ ልምምዶቹ

የሙሐመድን ሕይወት ስንመረምር ብዙ አስገራሚ ታሪኮችን እናገኛለን፡፡ እነዚህን ታሪኮች መጽሐፍ ቅዱስንና የቀደሙትን ነቢያት ሕይወት መሠረት አድርገን ስንመዝን ሙሐመድ የእውነተኛ ነቢይነትን መስፈርት ወድቆ እናገኘዋለን፡፡ ከታሪኮቹ መካከል አንዱ ከልጅነቱ ጀምሮ እስከ ዕውቀቱ አልፎም እስከ ህልፈተ ሕይወቱ ድረስ ያስተናገደው መናፍስታዊ ልምምድ ነው፡፡ የሐዲስና የሲራ መጻሕፍት ሙሐመድ ከልጅነቱ ጀምሮ ክፉ መንፈስ የተጠናወተው እንደነበር ያመለክታሉ፡፡ ይህ የክፉ መንፈስ መጠናወት “ለነቢይነት” ከተመረጠም በኋላ እንደቀጠለ አልፎም እርኩሳን መናፍስት ያስጨንቁትና ምሪትን ይሰጡት እንደነበር ተዘግቧል፡፡ ይህንን ሁሉ የምንናገረው ከእስላማዊ ምንጮች ውስጥ የማይታበሉ ማስረጃዎችን ይዘን እንጂ ሙስሊም ወገኖቻችንን ለማስከፋት ያለ በቂ ማስረጃ ነቢያቸውን የማብጠልጠል ዓላማ ኖሮን አይደለም፡፡[1] እነሆ ሐቲት፡-

1. ሙሐመድና የልጅነት አጋንንታዊ ልምምዱ

ሙሐመድ በተፀነሰ በስድስተኛው ወር ወላጅ አባቱ አብደላህ  ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየና እናቱ አሚና ቢንት ወሒብ በወቅቱ በነበረው የአረቦች ልማድ መሠረት ህፃኑ ሙሐመድን ጡት እንድታጠባ ሐሊማ ለተባለች ሴት በመስጠቷ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ገጠር እንደኖረ ግለ ታሪኩ ይናገራል፡፡ በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ ምስጢራዊ ፍጥረታትን መገናኘት የጀመረው፡፡ ይህ ታሪክ ታላቁ ሊቅ ኤም. ደብሊዩ ዋት በተረጎሙት የኢብን ይስሐቅ የነቢዩ የሕይወት ታሪክ ገፅ 36 ላይ እንዲህ ይነበባል፡-

እጃቸው በረዶ የሞላበትን ሰሀን የያዙ ሁለት ሰዎች ወደ እኔ መጡ፡፡ ያዙኝና ሰውነቴንም ሁለት ቦታ ከፍለው ከፈቱት፤ ልቤንም አወጡትና ሁለት ቦታ ሰንጥቀው ከውስጡም የረጋ ደም አውጥተው ጣሉ፡፡ ከዚያም ልቤንና ሰውነቴን ንጹህ እስኪሆን ድረስ በያዙት በረዶ አጠቡኝ፡፡[2]

ይህ ክስተት ሐሊማና ቤተሰቧን እጅግ ከመረበሹ የተነሳ ሙሐመድን ለእናቱ እንደመለሰችው ታሪኩ ይናገራል፡፡ የሐሊማን ስጋት በኢብን ይስሐቅ በተጻፈው ሲራ ውስጥ እንደሚከተለው እናነባለን፡-

(የሙሐመድ ጓደኛ) አባት እንዲህ አለኝ “ይሄ ልጅ የልብ በሽታ እንዳለበት እሰጋለው፡፡ የከፋ ነገር ሳይከሰት ወደ ወላጆቹ መልሱት” የሙሐመድም እናት ምን እንደተከሰተ እና አጋንንት ይዞት እንደሆን አጥብቃ ጠየቀችኝ፡፡ እረፍትም አልሰጠችኝም፡፡ እኔም በእርግጥ እንደምጠረጥር ነገርኳት፡፡[3]

እንግዲህ የሙሐመድ ሞግዚት ሙሐመድ በሰይጣን ቁጥጥር ስር እንደነበረ ማመኗን ልብ ይሏል፡፡ ምን ያህል ነገሩ የከፋ ቢሆን ነው መልሳ ለቤተሰቦቹ የሰጠችው? ከሴቲቱ አቅም በላይ የሆነ ጉዳይ መከሰቱ ግልፅ ነው፡፡

2. ሙሐመድ በሒራ ዋሻ ውስጥ፡- የነቢይነት ጥሪ

ሙሐመድ በሒራ ዋሻ ውስጥ የገጠመውን ክስተት በተመለከተ ሳሒህ አል-ቡኻሪ 9.111 ላይ እንዲህ ተብሏል፡-

አይሻ እንዳወራችው፡- ለአላህ መልእክተኛ የመጣው የመጀመርያው ራዕይ በንፁህ (እውነተኛ) ህልም መልክ ነበር፡፡ እውነተኛ የጠራ የቀን ብርሃን የሚመስል ካልሆነ በቀር አያልምም ነበር፡፡ እርሱም ወደ ሒራ ብቻውን በመሄድ ለብዙ ቀናትና ምሽቶች አላህን ያመልክ ነበር፡፡ እርሱም ሲሄድ ለሚቆይባቸው ቀናት የሚሆን ምግብ ይዞ ይሄድ ነበር፤ ሲያልቅበትም ለሌላ ጊዜ የሚሆን ምግብ ለመውሰድ ወደ ሚስቱ ወደ ከድጃ ተመልሶ ይመጣ ነበር፡፡ ይህንንም መገለጡ በሒራ ዋሻ እስኪወርድለት ድረስ አድርጎታል፡፡ በዚያም ሳለ መልአኩ ወደ እርሱ መጥቶ እንዲያነብ ጠየቀው፡፡ ነቢዩም “እኔ ማንበብ አልችልም” ብሎ መለሰለት፡፡ ነቢዩም እንዳሉት “መልአኩም በጉልበት ያዘኝና አስጨንቆ ከአቅሜ በላይ ጨመቀኝ፡፡ ከዚያም ለቀቀኝና አንብብ አለኝ፡፡ እኔም መልሼ “እኔ ማንበብ አልችልም አልኩት፡፡” ይሄኔ እንደገና ያዘኝና መቋቋም ከምችለው በላይ ጨመቀኝ፡፡ ከዚያም ለቀቀኝና እንደገና አንብብ አለኝ፡፡ እኔም በድጋሚ ማንበብ አልችልም አልኩ፡፡ እርሱም ለሦስተኛ ጊዜ ይዞ መቋቋም ከምችለው በላይ ጨመቀኝና ለቀቀኝ ከዚያም እንዲህ አለኝ፡- “አንብብ በጌታህ ስም፡ ሁሉን በፈጠረው፡፡ ሰውንም ከረጋ ደም በፈጠረው፡፡ አንብብ ጌታህም ታላቅ ነውና… (ሱራ 96፡15) የአላህ መልእክተኛም መገለጡን ተቀብሎ ሲመለስ ከድጃ ጋር እስኪገባ ድረስ በፍርሃትና የአንገቱ ጡንቻዎቹ በመንቀጥቀጥ ይብረከረኩ ነበር፡፡ እርሷ ጋ ሲደርስም “ሸፍኑኝ ሸፍኑኝ” አለ፡፡ እነርሱም ፍርሃቱ እስኪለቀው ድረስ ሸፈኑት፡፡ እርሱም “ከድጃ ሆይ ምን እየሆንኩ ነው; ብሎ ጠየቃት፡፡ የገጠመውንም ነገር ሁሉ ከነገራት በኋላ “የሆነ ነገር ሳልሆን አልቀርም” አላት፡፡ ከድጃም መልሳ “በፍፁም፤ በአላህ! አንተ ታላቅ መልካም የምሥራች ያለብህ ነህ፡፡ አንተ ከዘመዶችህ ጋር መልካም ግንኙነት እስካለህ ድረስ፤ እውነትን እስከተናገርክ ድረስ፤ ድሆችንና ምስኪኖችን እስከረዳህ ድረስ፤ እንግዶችንም በአክብሮት እስካስተናገድክ ድረስ አላህ በፍፁም አይጥልህም” አለችው፡፡ ነገር ግን ከጥቂት ቀናት በኋላ ዋራቃ ሞተ፤ መለኮታዊውም መገለጥ ለጊዜው ቆመ፡፡ ከዚህም የተነሳ ነቢዩ እጅግ አዘነ፡፡ ብዙ ጊዜም ራሱን ከትልቅ ተራራ ጫፍ ላይ ፈጥፍጦ ሊገድል እንደሞከረና ራሱን ሊወረውር ወደ ተራራው በደረሰ ቁጥር ገብርኤል ይገለጥለትና “ሙሐመድ ሆይ በእርግጥ አንተ የአላህ መልእክተኛ ነህ” ሲለው ልቡ እንደሚረጋጋና እንደሚሰክን ከዚያም ወደ ቤት እንደሚመለስ ሰምተናል፡፡ የመገለጡ መምጣት በዘገየ ቁጥር እንደበፊቱ ያደርግ ነበር፡፡ ወደ ተራራው በቀረበም ቁጥር ገብርኤል ከዚህ በፊት እንዳለው ይለው ነበር፡፡

ተከታዮቹ እስላማዊ ምንጮች ሙሐመድ በዋሻው ውስጥ ከገጠመው ነገር የተነሳ ያደረበትን ፍርሃት ይናገራሉ፡-

ሲራ ኢብን ሳድ ቅጽ 1፣ ክፍል 1.45.4

ኸድጃ ሆይ ብርሃን አይቻልሁ ድምጽም ሰምቻለሁ እና ጠንቋይ እንዳልሆን ፈራሁ አሉ፡፡…[4]

ሙስናድ አሕመድ ቢን ሐንባሊ ቅጽ 3፣ ቁጥር 2845

ነቢዩ ለኸድጃ እንዲህ አሏት፡- “ብርሃን አይቻለሁ ድምጽም ሰምቻለሁ፤ ምናልባት ውስጤ በጂን ቁጥጥር ውስጥ ሥር ተይዞ እንዳይሆን ፈራሁ አሏት፡፡…”[5] 

ሲራ ኢብን ሳድ ቅጽ 1, ክፍል 1.45.3

ኸድጃ ሆይ…በአላህ ጣኦትና ጠንቋይ እንደምጠላ ምንም ነገር አልጠላም፤ እናም እኔው ራሴው ጠንቋይ እንዳልሆን ፈራሁ አሉ፡፡[6]

ከተለያዩ ሰዎች እንደመዘገቡ መጠን በዚህ እንግዳ አካል ለሙሐመድ ስለተደረገው ጉብኝት በሚዘግቡት ድርሳናት መካከል ጥቂት ልዩነቶች መኖራቸው ግልፅ ነው፡፡ እነዚህ ታሪኮች በጥቃቅን ጉዳዮች ፍፁም የሆነ ስምምነት ባይኖራቸውም ትልቁን የታሪኩን ክስተት ማግኘት እንችላለን፡፡ ይህም ሙሐመድ ከአንድ ክፉና አስጨናቂ መንፈስ ጋር ግንኙነት ያደርግ እንደነበር ነው፡፡ ነገር ግን ሚስቱ ኸዲጃ ጭኗን ገልጣ በማሳየት የታየው አካል መልአክ እንጂ ክፉ መንፈስ አለመሆኑን ልታሳምነውና ልታረጋጋው ሞክራለች፡-

የአል-ዙቤይር ኢስማኢል ቢን ሐኪም ከኸድጃ ሰምቶ እንደ ነገረኝ ኸድጃ የአላህን መልእክተኛ እንዲህ አለቻቸው፡- የአጎቴ ልጅ ሆይ በዋሻው የተገለጠልህ ወደ አንተ ሲመጣ ልትነግረኝ ትችላለህ? አዎን እችላለሁ አሏት፡፡ እርሷም ሲመጣ ንገረኝ አለቻቸው፡፡ ገብርኤል በመጣ ጊዜ ወደእኔ መጥቶ የነበረው ይኸውና መጥቷል አሏት፡፡ የአጎቴ ልጅ ተነሳና በግራ ጭኔ ላይ ተቀመጥ አለቻቸው የአላህ መልእክተኛም ተቀመጡ፡፡ እርሷም ታየዋለህን? አለቻቸው፡፡ እርሳቸውም አዎን አሏት፤ ዙርና በቀኝ ጭኔ ላይ ተቀመጥ አለቻቸው፤ እርሳቸውም ተቀመጡ፡፡ እርሷም አሁን ታየዋለህን? አለቻቸው አዎን አሏት፤ አሁንም ልብሷን ገለጥ አድርጋ ወደላይኛው ጭኔ ከፍ ብለህ ተቀመጥ አለቻቸው፤ እንደገና ተቀመጡ፡፡ እርሷም አሁን ታየዋለህ? አለቻቸው፤ አዎን አሏት፤ አዎን ባሏት ጊዜ ጭኗ ላይ ከፍ ብለው እንደተቀመጡ መሸፈኛዋንና የለበሰችውን ጠቅላላ ልብሷን አወላልቃ እራቁቷን በመሆን አሁን ታየዋለህን? አለቻቸው፤ አላየውም አሏት፤ እርሷም የአጎቴ ልጅ ሆይ ልብህ ይረጋጋ ደስም ይበልህ፤ በአላህ እርሱ መልአክ እንጅ ሰይጣን አይደለም አለቻቸው፡፡[7]      

በኸድጃ ሎጂክ መሠረት ለሙሐመድ የተገለጠው ሰይጣን ከሆነ ሥነ ምግባር ስለሚጎድለው የሴት እርቃን ለማየት ችግር የለበትም፤ መልአክ ከሆነ ግን ጨዋ በመሆኑ የሴት እርቃን ሊያይ አይችልም፡፡ ስለ መንፈሳዊው ዓለም ዕውቀት የጎደለው ሰው ካልሆነ በስተቀር እንዲህ ያለውን እሳቤ ከቁምነገር ቆጥሮ የሚሰማ ሰው አይኖርም፡፡ የሚገርመው ነገር የኸዲጃን ጭን አፍሮ ሸሸ የተባለው ጂብሪል በቁርአን ተረት መሠረት ከ600 ዓመታት በፊት ለማርያም ሲገለጥ በጭኗ መካከል ተንፍሶባታል (ሱራ 66፡12፣ 19፡21)፡፡ በጉዳዩ ላይ ኢብን ከሢር የሰጠውን ሐተታ በግርጌ ማስታወሻው ላይ ይመልከቱ፡፡[8] ታድያ ከ600 ዓመታት በፊት ወደ ሴት “ጭን” መተንፈስ ያላሳፈረው ጂብሪል የኸዲጃን ጭን ሊያፍር እንዴት ቻለ?

ይህ የተገለጠለት አካል ጂብሪል (ገብርኤል) መሆኑን ለሙሐመድ የነገረው ደግሞ ዋረቃ የተሰኘ የኸዲጃ አጎት ነበር፡፡ ለሙሐመድ የተገለጠለት አካል ግን ገብርኤል ነኝ አላለውም፤ የመልአክ ባሕርይም አልነበረውም፡-

“… ከዛም ከዋረቃ ኢብን ናውፋል ጋር አገናኘቻቸው፡፡ እርሱም ከእስልምና በፊት ክርስትናን የተቀበለና አላህ እንዲጽፍ የፈቀደለትን ያክል፣ ወንጌልን ከእብራይስጥ ወደ አረብኛ ተርጉሞ መጽሐፍ የጻፈ ሰው ነው፡፡ ዋራቃ፣ በጊዜው ሸምግሎና የዓይን ብርሃኑን አጥቶ ነበር፡፡ ኸድጃም ዋራቃን፣ አጎቴ፣ የወንድምህን ልጅ ታሪኩን አድምጠው አለችው፡፡ ዋራቃም የወንድሜ ልጅ ሆይ ያየኸው ምንድን ነው? ሲል ጠየቃቸው፡፡ የአላህ መልእክተኛም ያዩትን ሁሉ ገለጹለት፡፡ ዋራቃም፣ እርሱማ አላህ ወደ ሙሴ ልኮት የነበረው ገብርኤል ነው አላቸው … ዋራቃ እንደ ሞተ፣ ለነቢዩ ይወርድ የነበረው ራዕይ ቆመ…”[9]

ዋረቃ ይህ አካል ገብርኤል መሆኑን እንዴት አወቀ? የሚለው መልስ ያላገኘ ጥያቄ ነው፡፡ ነገር ግን የዚህ አካል ባሕርይ ለቅዱሳን ሲገለጥ ከነበረው ገብርኤል ጋር እንደማይሄድ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ መረዳት ይቻላል፡፡

3. የሙሐመድ መገለጥ አቀባበል

ለሙሐመድ መገለጥን ሲሰጠው የኖረው አካል በደዎል (ቃጭል) ድምጽ ይናገር እንደነበርና ይህ ድምጽ ደግሞ የሰይጣን መሆኑን በእስላማዊ ምንጮች ውስጥ ማንበብ በእጅጉ አስደንጋጭ ነው፡-

ሳሒህ ሙስሊም 30 ፡ 5765

ሳሒህ አል-ቡኻሪ ቅጽ 4፣ 54 ፡ 438

አል-ሃሪሳ ቢን ሒሻም ነቢዩን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- ራዕዩ ሲወርድለዎት በምን ሁኔታ ነው? እርሳቸውም ሲመልሱ መልአኩ አንዳንድ ጊዜ የደዎል ድምጽ በሚመስል ድምጽ እየተናገረ ይመጣል፤ ይህ አይነቱ የራዕይ አወራረድ ለእኔ በጣም ልቋቋመው የማልችለው ከባድ አይነት ነው፡፡ መልአኩ ትቶኝ ከሄደ በኋላ የተቀበልኩትን ራዕይ አስታውሰዋለሁ፡፡ አንዳንዴ ሰው በመምሰል ወደ እኔ ይመጣና ያናግረኛል እኔም ምን እንዳለኝ እረዳዋለሁ፣ አስታውሰዋለሁም፡፡ አኢሻ ጨምራ መልአኩ በእርሳቸው ላይ በወረደ ጊዜ በከባድ ብርድ ሰዓት ግንባራቸው ላብ በላብ ይሆናል፡፡[10] 

በሌላ ጊዜ ሙሐመድ ይህ የደዎል ድምጽ የማን እንደሆነ እንዲህ ተናግሯል፡-

ሳኢድ ቢን ጁቤይር ሲናገር አላህ ኢብሊስን (ሰይጣንን) በረገመው ጊዜ መልኩ ከመላዕክት ወደተለየ መልክ ተቀየረ፣ ድምጹም እንደ ደወል ድምጽ ሆነ፡፡ በዚህም ምድር ላይ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ የሚሰማ ማንኛውም የደወል ድምጽ የዛው የሰይጣን ድምጽ አካል ነው፡፡ ኢብን አቢ ሃቲም ያስተላለፈው ሃዲስ ነው[11] 

ሙሐመድ “ጂብሪል” ብሎ የሚጠራው መንፈስ ሰይጣን ለመሆኑ ከዚህ በላይ ምን ማረጋገጫ ያስፈልገዋል? መቼስ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰይጣን ድምጽ ጋር በሚመሳሰል ድምጽ ሊናገር አይገባውም፡፡

የሙሐመድ “የራዕይ” አቀባበልም አንድ አጋንንት ያደሩበት ሰው ከሚያሳየው ምልክት ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ሌላው አስደንጋጭ እውነታ ነው፡- 

ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅጽ 3፣ 27 ፡ 17

ነቢዩ በጂራና ሳሉ አንድ ሰው መጣ፡፡ ሰውየው ኻሉቅ ወይንም ሱፈራ በሚባል ሽቱ የተቀባ ካባ ለብሶ ነበር፡፡ ሰውየው ነቢዩን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- በኡምራየ ወቅት ላደርገው የሚገባ የሚያዙኝ ነገር ምንድን ነው? ከዛ በጨርቅ መጋረጃ በተጋረደ ቦታ ሆነው አላህ ለነቢዩ መልእክት ይሰጣቸው ጀመር፡፡ እኔም አላህ ለነቢዩ መገለጥ ሲሰጣቸው እንዴት እንደሚሆኑ ለማየት ጓጓሁ፡፡ ኡመርም እንዲህ አለኝ፡- ና! አላህ ለነቢዩ መገለጥ ሲሰጣቸው እንዴት እንደሚሆኑ ማየት ትፈልጋለህ? እኔም አዎን ስል መለስኩለት፡፡ ኡመርም የመጋረጃውን አንዱን ጎን አነሳልኝ፣ እኔም ነቢዩ ሲያንኮራፉ አየሁ፡፡ (ሌላ ተናጋሪ እንዲህ እንደተናገረ አስቧል፡- ኩርፊያው የግመል ይመስል ነበር)

ኡመር እንዲህ አለኝ፡- የአላህ መልእክተኛ ራዕይ ሲወርድላቸው ማየት ትፈልጋለህ? እርሱም የመጎናጸፊያቸውን ጠርዝ ከፊታቸው ላይ ሲያነሳው ጅራና ላይ ነበር ራዕዩን ይቀበሉ የነበረው፣ ፊታቸው ደም መስሎ ቀልቶ ነበር፤ አዲስ እንደተወለደ ጥጃም ያቃስቱ ነበር፡፡[12]

እስኪ ይህንን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፈው ከዚህ ታሪክ ጋር በማነጻጸር እንመልከት፡-

“እነሆም፥ ከሕዝቡ አንድ ሰው እንዲህ እያለ ጮኸ፦ መምህር ሆይ፥ ለእኔ አንድ ልጅ ነውና ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ። እነሆም፥ ጋኔን ይይዘዋል፥ ድንገትም ይጮኻል አረፋም እያስደፈቀው ያንፈራግጠዋል፥ እየቀጠቀጠም በጭንቅ ይለቀዋል፤ ደቀ መዛሙርትህንም እንዲያወጡት ለመንሁ፥ አልቻሉምም። ኢየሱስም መልሶ፦ እናንተ የማታምን ጠማማ ትውልድ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጅህን ወደዚህ አምጣው አለ። ሲቀርብም ጋኔኑ ጣለውና አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኵሱን መንፈስ ገሥጾ ብላቴናውን ፈወሰው ለአባቱም መለሰው።” (ሉቃስ 9፡38-42)

የሙሐመድ ሁኔታ ከዚህ ልጅ ጋር በእጅጉ የሚመሳሰል ነው፡፡ በዘመኑ የነበሩት ሰዎች ይህንን ሁኔታ በመታዘብ ጋኔን እንዳደረበት ተናግረዋል፡፡ ቁርአን እንዲህ ይላል፡-

ሱረቱል አል-ተክዊር (81) ፡22-25 “ ነቢያችሁም በፍፁም እብድ አይደለም፡፡በግልፁ አድማስም በእርግጥ አይቶታል፡፡ እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም፡፡ እርሱም (ቁርአን) የእርዱም የሰይጣን ቃል አይደለም፡፡

ሱረቱል አል-ሓቃህ (69) ፡ 41-43 እርሱም የባለቅኔ ቃል (ግጥም) አይደለም፡፡ ጥቂት ብቻ ታምናላችሁ፡፡ የጠንቋይም ቃል አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታሰታውሳላችሁ፡፡ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡

በዘመኑ የነበሩት ሰዎች ሙሐመድ በሰይጣን ቁጥጥር ስር እንደነበረና የሚናገረው ነገር ሐሰት መሆኑን፣ ቁርአንም ከሰይጣን እንደሆነ ማመናቸው ግልፅ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሙሐመድ የመልስ ምት ከላይ ያሉ አንቀፆችን ከአላህ ወረዱልኝ ብሎ የተናገረው፡፡

በሐዲስ ውስጥም እንዲህ ተብሏል፡-

“ጁንዱብ ቢን ሱፊያን እንዳወራው፡- በአንድ ወቅት የአላህ መልእክተኛ ስለታመሙ የሁለት ወይንም ሦስት ለሊቶችን ጸሎት ማድረስ አልቻሉም ነበር፡፡ ከዚያም አንዲት ሴት (የአቡ ለሃብ ሚስት) በመምጣት እንዲህ አለቻቸው ‹ሙሐመድ ሆይ! ያንተ ሰይጣን ትቶህ የሄደ ይመስለኛል፤ ለሁለት ወይም ሦስት ለሊቶች ካንተ ጋር አላየሁትምና!› ከዚያ አላህ እንዲህ የሚል ቃል ገለጠ፡- ‹በረፋዱ እምላለሁ፤ በሌሊቱም ጸጥ ባለ ጊዜ፤ ጌታህ አላሰናበተህም አልጠላህምም።› (93፡1-3) (Sahih Al-Bukhari, Volume 6, Book 60, Number 475)

ይህች ሴት ሙሐመድ እንግዳ የሆነ ልምምድ እንደነበረው አስተውላለች፤ እናም ከዚያ ቀደም አብሮት የነበረው ክፉ መንፈስ አብሮት እንደሌለ አስተውላ ‹ያንተ ሰይጣን ትቶህ የሄደ ይመስለኛል› ስትለው አብሮት ያለው አካል ሰይጣን አለመሆኑን እንደማስረዳት “አይ ጌታዬ ትቶኝ አልሄደም” ማለቱ አስገራሚ ነው፡፡

4. ሙሐመድ እና የጥንቆላ አስማት

ሙሐመድ አስማት ስለተሰራበት ሚስቶቹ በሌሉበት ቦታ ከሚስቶቹ ጋር እንደሚሆን ይሆን እንደነበረ፣ ብዙ ያላደረጋቸውን ነገሮች እንዳደረገ እንደሚሰማው ሐዲሳቱ ሳይሸሽጉ ዘግበውልናል፡፡

አል-ቡኻሪ ቅፅ 7፣ ቁጥር 660

አይሻ እንዳወራችው

በኣላህ መልእክተኛ ላይ አስማቱ ሰርቶባቸው ከሚስታቸው ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ሳያደርጉ  የሚያደርጉ ይመስላቸው ነበር፡፡

በተጨማሪም አል-ቡኻሪ 4.490፣ 7.658፣ 7.661፣ 8.89፣ 8.400

እንኳንስ በእግዚአብሔር ነቢይ ላይ ይቅርና በእግዚአብሔር በእውነት ባመነ በማንኛውም ሰው ላይ አስማት እንዴት ሊሠራ ይችላል? የበለአም አስማት እንኳንስ በሙሴ ላይ ሊሠራ ይቅርና በሙሴ ከሚመራው ህዝብ መካከል በአንዱ ላይ እንኳ ሊሠራ አልቻለም፡፡ ይልቅስ ይህንን የተረዳው አስማተኛው በለአም “በያዕቆብ ላይ አስማት የለም በእስራኤልም ላይ ሟርት የለም” በማለት መስክሯል (ዘኁልቁ 23፡23)፡፡

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ደግሞ ጌታ ኢየሱስ የአጋንንት ኃይል በስሙ ባመኑት ሰዎች ላይ እንደማይሠራና ይልቁኑ በስሙ አጋንንትን ከሰዎች ውስጥ እንዳሚያስወጡ ተናግሯል፡፡ ይህ ተስፋ በሐዋሪያት ዘመን ሲሠራ ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን እየሠራ እንደሆነ ማንም አይቶ መመስከር ይችላል (ማርቆስ 16፡17-18)፡፡

5. ሙሐመድና ሰይጣናዊ አንቀፆች

ሙሐመድ በአንድ ወቅት ከጣዖት አምላኪያን ጋር ለማስማማት ሰይጣን በአፉ መልእክትን እንዳስቀመጠ አምኖ ነበር፡፡ ኋላም አላህ እንዳረመውና የቁርአኑም ቂርአት እንደተለወጠ ተናግሯል፡፡ የሰይጣናዊ ጥቅሶች ክስተት በመጀመርያዎቹ 150 ዓመታት ውስጥ የሙስሊም ማሕበረ ሰቦችን የታሪክ ትውስታ ተቆጣጥሮ የነበረ ሲሆን በተፍሲርና ሲራህ-መግሐዚ ዘርፍ በሚሠሩ ከሞላ ጎደል ሁሉም ሊቃውንት የተመዘገበ ነው፡፡[13]

ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡ ሙሐመድ በመካ በነበረባቸው ዓመታት መካውያን እንዳይጎዱት በአጎቱ ጥበቃ ይደረግለት ነበር፡፡ ሆኖም አብዛኞቹ ተከታዮቹ እንዲህ ያለ ጥበቃ ያልነበራቸው ሲሆን ከዚህ የተነሳም ተሰደዱ፡፡ ስደተኙቹም ክርስቲያናዊት መንግስት ወደነበረችው አቢሲንያ መጡ፡፡ ይህ ሁኔታ አመቺ ባለመሆኑ ከመካውያን (ቁረይሾች) ጋር እርቅን ለማውረድ ሲል ስለ መካ አማልክት ተከታዮን ጥቅስ ተናገረ፡-

“አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም መናትን አያችሁን? እነዚህ ከፍ ያሉ ግሃራኒቅ (በራሪዎች) ናቸው፡፡ ምልጃቸውም ተስፋ ይደረጋል፡፡” ቁረይሾች ይህንን በሰሙ ጊዜ አማልክታቸውን በማሞጋገሱ ደስተኛ በመሆን ያደምጡት ጀመር … ከዚያም ሰዎች ሁሉ ወደየመጡበት ተበተኑ፣ ቁረይሾችም ስለ አማልክቶቻቸው በተናገረው ነገር ሀሴት አድርገው “መሐመድ ስለ አማልክታችን እያደናነቀ ተናገረ” አሉ፡፡[14]

ሙሐመድ የመካ አማልክት ምልጃ ተቀባይነት እንዳለው በመናገሩ ተቀብሏቸዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ መካውያን ከእርሱ ጋር ሰላምን ስለፈጠሩ ተከታዮቹ ከአቢሲንያ መመለስ ጀመሩ፡፡ ከዚም መልአኩ ገብርኤል ወደ ሙሐመድ በመምጣት “ሙሐመድ ሆይ ያደረከው ምንድነው?” አለው፡፡ “እኔ ከፈጣሪ ዘንድ ያላመጣሁልህን ነገር ለዚህ ሕዝብ አንብበሃል፤ እርሱ ያልተናገረውንም ተናግረሃል፡፡” … አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል፡፡[15]

ስለዚህ በእስላማዊ ምንጮች መሠረት ሙሐመድ የሰይጣንን ቃል በመናገር አሓዳዊነቱን አመቻምቿል፡፡ ይህ በጣም ከባድ ጉዳይ ቢሆንም ሙስሊሞች የማይማሩት ለሌላውም ሕዝብ የማይነግሩት ጉዳይ ነው፡፡

አል-ጠበሪ እንዲህ ይለናል፡-

የአላህ መልእክተኛ ስለ ህዝቡ ደህንነት ስጋት አደረበት፡፡ በተቻለው መጠንም ሊማርካቸውና ልባቸውን ሊስብ ይጥር ነበር፡፡ እርሱም እንዲወድዱት ይጓጓ እንደነበር እንዲህ ተዘግቧል፡፡ “የአላህ መልእክተኛ ተከታዮቹ ጀርባቸውን እንዳዞሩበት ሲያይ እጅግ አዘነ፡፡ ከፈጣሪ ዘንድ ወደነርሱ ስላወረደው ነገር እንቢተኛ በመሆናቸው እርሱንና ህዝቡን የሚያስታርቅ መልዕክት ከፈጣሪ ዘንድ እንዲመጣ ፈለገ፡፡ ለህዝቡ ካለውም ፍቅር የተነሳ እና ስለሚጨነቅላቸው አላማውን እንዳያስፈፅም የተቀመጡ መሰናክሉች ቢነሱ እጅግ ደስ ይለው ነበር፡፡ እርሱም ስለዚሁ ጉዳይ መመሰጥ እና ከልቡ በመነጨ ጉጉት ይጓጓ ነበር፡፡ ይህም ለእርሱ ቅርብ ነበር፡፡ ከዚያም አላህ ይህንን መገለጥ አወረደ፡-  “በኮከብ እምላለሁ በወደቀ (በገባ) ጊዜ። ነቢያችሁ፣ (ሙሀመድ) አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም። ከልብ ወለድም አይናገርም።” እያለ and when he reached His words, ” አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን አያችሁን?” የሚለውን ሲያሰላስል እርቅን ለመፍጠር የነበረውን የልቡን ጉጉት በመጠቀም ሰይጣን “እነዚህ ከፍ ያሉ በራሪዎች (ገራኒቅ) ናቸው፡፡ ምልጃቸውም ተስፋ ይደረጋል” የሚል ቃል በምላሱ ላይ አስቀመጠ፡፡ ቁረይሾች ይህንን ሲሰሙ እጅግ ደስ አላቸው፤ ስለ እነርሱ አማልክት የተናገረበትን መንገድም አወደሱት፤ ከልባቸውም ይሰሙት ነበር፡፡ አማኞች ነቢያቸው ከጌታቸው ዘንድ እውነትን ብቻ እንደሚያወርድ ያምኑ ነበር እንጂ ሐሰትን፤ የግል መሻትንና ስህተትን ያወርዳል በለው አልጠረጠሩም ነበር፡፡ የስግደት ሰዓት ሲደርስ የሱራውን መጨረሻ እርሱም ሆነ ሌሎች ሙስሊሞች ቢሆኑም እርሱ ያመጣውን በማረጋገጥ እና በመታዘዝ ሰገዱ፡፡ የቁረይሽ ጣዖት አምላኪያን እና ሌሎችም በመስጊድ ውስጥ የነበሩት አማልክቶቻቸው ሲጠሩ በመስማታቸው ሁሉም አብረው ሰገዱ፡፡ … ከዚያም ህዝቡ ሲበታተን ቁረይሾች ስለ አማልክቶቻቸው የተባለውን በተባለው ነገር እየተደሰቱ ወደ ቤቶቻቸው ይሄዱ ነበር፡፡  እንዲህም አሉ “ሙሐመድ ስለ አማልክቶቻችን ድንቅ በሆነ መልኩ ይናገር ነበር፡፡ ገራኒቅ በምልጃቸው ከፍ ማለታቸውን ያነበበውን ይነግረን ነበር፡፡ … ገብርኤልም ወደ ነቢዩ መጣና እንዲህ አለው፡- “ሙሐመድ ምንድነው ያደረግከው; ለእነዚያ ሰዎች እኔ ወዳንተ ከፈጣሪ ዘንድ ያላመጣሁትን ነገር አንብበሃል እርሱ ያላለውንም ብለሃል፡፡ ነቢዩም አምርሮ አዘነ አላህንም እጅግ ፈራ፡፡ ከዚያ አላህ መሃሪ እንደሆነ፤ እያፅናናው እና ጉዳዩን በተመለከተ እያጠራለት፤ እርሱ ብቻ ሳይሆን ከእርሱ በፊት የነበሩ ነቢያትም ልክ እንደ እርሱ የልባቸውን መሻት እንዳሹ እርሱ የፈለገውን እንደፈለጉ ሰይጣንም በምላሱ ላይ እንዳደረገው ሁሉ በልቡም ላይ እንዳደረገ መገለጦችን አወረደለት፡፡[16]

የጉዳዩን ታሪካዊነት በተመለከተ ሻቢር አኽታር የተሰኙ ሙስሊም ጸሐፊ የሚከተለውን ብለዋል፡- “ይህ በጣም ሐቀኛ በሆነ እስላማዊ ትውፊት የተዘገበው አውዳሚ የሆነ ክስተት ሰይጣን በነቢዩ የመገለጥ ንባብ አቀባበል ጣልቃ ሊገባ እንደሚችል አሳይቷል … ሩሽዲ በሱራ 53 ላይ የሚገኘውን ሙሉ ተቀባይነት ያለውንና ሳይከለስ የተጠበቀውን ተያያዥ አንቀፅ ጠቅሶ በማጣመም በመጀመርያው መገለጥ ውስጥ የነበረውን ሰይጣን ያስገባውን ተክቷል፡፡”[17]

ማጠቃለያ

ከነዚህ ታሪኮች እንደምንረዳው ሙሐመድ ከጨቅላ ሕፃንነቱ እስከ እውቀቱ አልፎም እስከ ነቢይነቱ ዘመን ድረስ የሰይጣን መጫወቻ ነበር፡፡ በህፃንነቱ ምስጢራዊ ፍጥረታት አግኝተውት ወድቆ ተንፈራግጦ ነበር፤ አሳዳጊዎቹም አጋንንት አድሮበት ሊሆን እንደሚችል ተናግረው ነበር፡፡ በዋሻ ውስጥ የተገናኘው አካል አፍኖ አስጨንቆት ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ሙሐመድ የተገለጠለት አካል ሰይጣን መሆኑን አውቆ ነበር፡፡ ዕድሜ ለኸዲጃና ለዋረቃ ሚዛን የማይደፉ መስፈርቶችን በመጠቀም ያ ክፉ መንፈስ ጂብሪል መሆኑን አሳምነውታል፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ አስማት ተሠርቶበት ሲሠቃይ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ከሰይጣን የተላኩ መገለጦች እንደሆኑ በግልጽ የተነገረላቸው መገለጦች በቁርአን ውስጥ ተካትተው ነበር፡፡ ሙሐመድ ከእርኩሳን መናፍስት ጋር የነበረውን ልምምድ ለማጽደቅ እንዲህ ያለ ልምምድ ያልነበራቸውንና ከእግዚአብሔር የሆኑ መልእክታትን ብቻ ያስተላለፉትን ቅዱሳን ነቢያት ወደ ራሱ ደረጃ ለማውረድ ሞክሯል፤ በእርሱ ላይ የደረሰው ችግር ያልተለመደና በሌሎች ነቢያት ላይ ያልደረሰ አለመሆኑን ለማስረዳት ሌሎች “መገለጦችን” ሲናገር እንመለከታለን (ሱራ 22፡52-53)፡፡ እንዲህ ያለ ልምምድ የነበራቸው ነቢያት እስኪ እነማን ናቸው በስም ጥቀስልን ብለን ብንጠይቅ ሊጠቅስልን አይችልም፡፡ ምክንያቱም እንደ ሙሐመድ በሰይጣን ምሪት መገለጥ ያወረደ አንድም ነቢይ አልነበረምና፡፡

እንግዲህ ከዚህ ሰው ምን እንሻለን? እርሱ ያስተማረው እምነት ለሌሎች የዘላለምን ሕይወት ሊሰጥ ይቅርና እርሱ ራሱ የዘላለም ሕይወት እያስፈለገው ሳያገኝ ሞቷል፡፡ እውነትና ሕይወት የሆነ የዘላለምን ሕይወት ሊሰጠን የሚችለው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻና ብቻ ነው፡፡ ቅዱስ ቃሉ እንዲህ ይላል፡-

“ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው፦ ጌታ ሆይ፥ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት። እንዲህም አላቸው ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ። እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።” (ሉቃስ 19፡17-20)

ውድ ሙስሊም ወገኖቼ! ዕድሜ ዘመኑን ሁሉ በሰይጣን ፍርሃት ውስጥ የኖረውን ሙሐመድን በመከተል እስከ መቼ ትስታላችሁ? እነዚህን ሁሉ ማስረጃዎችንስ እስከ መቼ ድረስ ትክዳላችሁ? ጌታ እግዚአብሔር የልብ ዐይኖቻችሁን በመክፈት በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘውን አርነት እንድትጎናጸፉ ይረዳችሁ ዘንድ የዘወትር ጸሎታችን ነው!



ማጣቀሻዎች

[1] በዚህ ርዕስ ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ፡- አብዱልሃቅ ጀሚል፤ ኢስላም መለኮታዊ ሃይማኖት ነውን?፤ 2011 ዓ.ም፡፡

[2] “Muhammad at Mecca”, by W.M. Watt, Pub. Oxford University Press. P. 36

[3] “The Life of Muhammad”, by A. Guillaume, Oxford University Press. P. 72

[4] Abu ‘Abd Allah Muhammad Ibn Sa’d Ibn Mani’, KITAB AL-TABAQAT AL-KABIR, www.soebratie.nl/religie/hadith/IbnSad.html

[5] Bin Hanbal, Musnad Imam Ahmed bin hanbal, Vol 3, page 14.

[6] Abu ‘Abd Allah Muhammad Ibn Sa’d Ibn Mani’, KITAB AL-TABAQAT AL-KABIR, www.soebratie.nl/religie/hadith/IbnSad.html

[7] Muhammad Ibn Ishaq, The Life of Muhammad, translated by A.Guillaume,  page 107  

[8] በኢብን ከሢር ተፍሲር መሠረት አላህ ጂብሪልን ልኮ ወደ ማህፀኗ እንዲተነፍስ አድርጓል፡- <And Maryam, the daughter of ‘Imran who guarded her chastity (PRIVATE PART).> meaning who protected and purified her honor, by being chaste and free of immorality, <And We breathed INTO IT (PRIVATE PART) through Our Ruh,> meaning, through the angel Jibril. Allah sent the angel Jibril to Maryam, and he came to her in the shape of a man in every respect. Allah commanded him TO BLOW into a gap of her garment and that breath went into her womb THROUGH HER PRIVATE PART; this is how ‘Isa was conceived. This is why Allah said here, <And We breathed INTO IT through Our Ruh, and she testified to the truth of her Lords Kalimat, and His Kutub,> meaning His decree and His legislation. (Tafsir Ibn Kathir – Abridged, Volume 10, Surat At-Tagabun to the end of the Qur’an, pp. 75-76; bold and capital emphasis ours)

[9]Abridged Tafsir Ibn Kathir Volume 1 – 10, http://www.tafsir.com sura 96: 1-5, Sahih Al-Bukhari, vol 1 page 46-47

[10] Sahih Al-Bukhari, translated by Muhammad Muhsin Khan, Maktaba Dar us Salam, Riyadh 1997, vol 1 p 46

[11] Tafsir Ibn Kathir, vol 5 page 394

[12] Al-Sira Al-Nabawiyya, vol 1 page 307.  

[13] Shahab Ahmed, The Satanic Verses Incident in the Memory of the Early Muslim Community, Princeton University PhD thesis, 1999, p. i. Also, “Ibn Taymiyyah and the Satanic Verses”, Studia Islamica, no. 87, 1998, p. 70 & 122.

[14] Ibn Ishaq, pp. 165-166

[15] Ibn Ishaq, p. 166

[16] አል ጠበሪ ቅጽ 1 ገፅ 237

[17] Shabbir Akhtar. Be Careful With Muhammad; 1992, p. 114



ነቢዩ መሐመድ