ሙስሊሞች እውን ሙሐመድን አታመልኩትም?
ሙስሊም ወገኖቻችን ሙሐመድን አናመልከውም ይላሉ ነገር ግን ከአላህ ይልቅ ለሙሐመድ ያላቸው ክብርና ፍቅር የገነነ ነው/ ይህንን ለማወቅ የአላህን ስሞችና የሙሐመድን ስሞች ማነጻጸር ብቻ በቂ ነው። በእስልምና አላህ 99 የታወቁ ስሞች ያሉት ሲሆን ሙሐመድ ወደ 1000 የሚሆኑ ስሞች አሉት። ከአላህ ስሞች መካከል የሙሐመድ መጠርያ ያልሆኑት በጣት የሚቆጠሩት ብቻ ናቸው። ለምሳሌ ያህል በዚህ ዌብሳይት 425 የሚሆኑ በጥንታዊ እስላማዊ ምንጮች ውስጥ የተዘረዘሩ የሙሐመድ ስሞች ተጠቅሰዋል (ዌብሳይቱ ከ149 በኋላ እንደገና 140 በማለት ስለጀመረ 416 ላይ ቢጨርስም በትክክል ሲቆጠሩ 425 ነው የሚሆኑት)፤ ብዙዎቹም ለፍጡር ተገቢ ያልሆኑ ናቸው። https://alahazratnet/articles/personalities/hazrat-muhammad-mustafa/-exalted-names-of-the-prophet/
በቀጥታ በቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ ስሞች
- ሙሐመድ፦ የተመሰገነ
- አሕመድ፦ ምስጋና የተገባው
- አል-አህሳን፦ እጅግ ውብ የኾነው/ ምርጡ
- ኡዙን ኸይር፦ ወዳጅ የኾነ ጆሮ
- አል-ዓላ፦ ታላቁ (ከፍጥረት ኹሉ)
- አል-ኢማም፦ መሪው
- አል-አሚን፦ ታማኙ
- አል-ነቢ፦ ነቢዩ
- አል-ኡሚ፦ ያለ አስተማሪ የተማረ/ የአፅናፈ ዓለሙ መሠረት ወይንም የመጀመርያውና የመጨረሻው
- አንፈስ አል-አረብ፦ ከአረቦች ኹሉ በጣም ውድ የኾነው
- አያቱላህ፦ የአላህ ምልክት
- አሊፍ ላም ሚም ራ፦ ሐ-ለ-መ-ረ
- አሊፍ፣ ላም፣ ሚም፣ ሳድ፦ አ-ለ-መ-ሰ
- አል-ቡርሀን፦ ማረጋገጫው
- አል-በሺር፦ የመልካም ዜና አምጪ
- አል-በሊግህ፦ አንደበተ ርቱዕ
- አል-በዪነ፦ ገላጩ
- ሣኒ ኢሥናይን፦ ከሁለት ሁለተኛው
- አል-ሐሪስ፦ አጥብቆ ጠያቂው
- አል-ሐቅ፦ እውነት የኾነው
- ሐ ሚም፦ ሐ-መ
- ሐ ሚመ ዐይን ሲን ቃፍ፣ ሐ-መ-ዐ-ሰ-ቀ
- አል-ሐኒፍ፦ የመጀመርያው እምነት ተከታይ
- ኸቲም አል-ነቢዪን፦ የነቢያት መደምደሚያ (ማክተሚያ)
- አል-ኸቢር፦ ታዋቂው
- አል-ዳዒ፦ ሰባኪው
- ዙ አል-ቁዋ፦ ጠንካራው
- ራህመቱን ሊ አል-ዓለሚን፦ ለዓለም ምሕረት
- አል-ራዑፍ፦ አስተዋዩ/ ጀብራሬው
- አል-ረሂም፦ የሚራራ
- አል-ረሱል፦ መልእክተኛው
- ሰቢል አላህ፦ ወደ አላህ የሚወስደው መንገድ
- አል-ሲራጅ አል-ሙኒር፦ አብሪው መብራት
- አል-ሻሒድ፦ የዓይን ምስክሩ
- አል-ሸሂድ፦ መስካሪው
- አል-ሳሂብ፦ አጋር ወዳጅ
- አል-ሲድቅ፦ እውነተኛነት እራሱ
- አል-ሲራት አል-ሙስተቂን፦ ቀጥተኛው መንገድ
- ታህ ሲን ተ-ሰ
- ታህ ሲን ሚም፦ ጠ-ሰ-መ
- ታህ ሐ፦ ጠ-ሀ
- አል-ዓሚል፦ ሠሪው
- አል-ዓብድ፦ ባርያው
- ዓብድ አላህ፦ የአላህ ባርያ
- አል-ዑርዋት አል-ውሥቃ፦ አስተማማኙ ገመድ
- አል-ዓዚዝ፦ ሃያሉ/ ተወዳጁ
- አል-ፈጅር፦ ንጋቱ
- ፈድል አላህ፦ የአላህ ጸጋ
- ቀዳሙ ሲድቅ፦ እውነተኛው መሠረት
- አል-ከሪም፦ ለጋሹ
- ካፍ-ሀዕ-ያዕ-ዓይን-ሳድ፦ ከ-ኅ-የ-ዐ-ሰ
- አል-ሊሳን፦ ቋንቋ ራሱ
- አል-ሙበሺር፦ የመልካም ዜና አምጪ
- አል-ሙቢን፦ መገለጫው
- አል-ሙደሢር፦ ተሸፋፋኙ
- አል-ሙዘሚል፦ ስውሩ
- አል-ሙዘኪር፦ አስታዋሹ
- አል-ሙርሰል፦ ተወካዩ
- አል-ሙስሊም፦ የተገዛው
- አል-መሽሁድ፦ የተመሰከረለት
- አል-ሙሰዲቅ፦ አጽዳቂው
- አል-ሙታዕ፦ የሚታዘዙት
- አል-መኪን፦ አስተማማኙ
- አል-ሙነዲን፦ ጯኺው
- አል-ሙንዚር፦ መካሪው
- አል-ሚዛን፦ ሚዛኑ
- አል-ናስ፦ ሰው
- አል-ነጅም፦ ኮከቡ
- አል-ሣቂብ፦ ፈጣን አሳቢው፣ ብልሁ
- አል-ነዚር፦ አስጠንቃቂው
- ኒዕማት አላህ፦ የአላህ ታላቁ በጎነት
- አል-ኑር፦ ብርሃኑ
- ኑን፦ ነ
- አል-ሐዲ፦ ምሪት እራሱ
- አል-ዋሊ፦ ረዳቱ
- አል-የቲም፦ ወላጅ አልባው፣ ለየት ያለው
- ያ ሲን፦ የ-ሰ
እንደ ግሥ በቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ ስሞች
- አኺዝ አል-ሰደቃት፦ ምጽዋት ሰብሳቢው
- አል-አሚር፦ አዛዡ
- አል-ነሒ፦ ከልካዩ
- አል-ጣሊ፦ ወራሹ
- አል-ሐኪም፦ ፈራጁ
- አል-ዘኪር፦ አስታዋሹ
- አል-ራዲ፦ ተስማሚው
- አል-ረግሂብ፦ ቀራቢው
- አል-ዋዲዕ፦ አጠራቃሚው
- ረፊዕ አል-ዚክር፦ ዝነኛው
- ረፊዕ አል-ደረጃት፦ ከፍ ያለ ደረጃ ያለው
- አል-ሳጂድ፦ ሰጋጁ
- አል-ሳቢር፦ ለረጅም ጊዜ መከራን የተወበለው
- አል-ሳዲዕ፦ እንቅፋቶችን አሸናፊው
- አል-ሰፉህ፦ ሁሌ ይቅር ባዩ
- አል-ዐቢድ፦ አምላኪው
- አል-ዓሊም፦ አዋቂው
- አል-ዐሊም፦ በጥልቀት አዋቂው
- አል-ዓፉው፦ ይቅር ባዩ
- አል-ግሃሊብ፦ ድል ነሺው
- አል-ግሃኒ፦ ከፍላጎቶች ነፃ
- አል-ሙባሊግህ፦ ዜና ያለው
- አል-ሙጠባ፦ የሚከተሉት
- አል-ሙተበጢል፦ ሙሉ በሙሉ ራሱን የሰጠው
- አል-መቱረቢስ፦ የሚጠበቀው
- አል-ሙሐሊል፦ ፈቃድ ሰጪው
- አል-ሙሐሪም፦ ከልካዩ
- አል-ሙረጢል፦ ሀሳቡን በቀላሉ መግለፅ የሚችለው
- አል-ሙዘኪ፦ የሚለየው
- አል-ሙሰቢህ፦ ድምፁን ከፍ አድራጊው
- አል-ሙስተዒዝ፦ ተሰዳጁ
- አል-ሙስተግህፊር፦ ይቅርታን ፈላጊው
- አል-ሙዕሚን፦ አማኙ/ ደህንነትን ሰጪው
- አል-ሙሸዊር፦ መካሪው
- አል-ሙሰሊ፦ ጸላዩ
- አል-ሙዓዘዝ፦ ጠንካራው
- አል-ሙወቀር፦ አስደማሚው
- አል-መዕሱም፦ የመከላከል አቅም ያለው
- አል-መንሱር፦ መለኮታዊ እርዳታ ያለው
- አል-መውላ፦ የሞገስና የእርዳታ አለቃ
- አል-ሙዓየድ፦ ድጋፍ ተቀባይ
- አል-ነሲብ፦ የሚለፋ
- አል-ሐዲ፦ ምሪት የኾነው
- አል-ዋዒዝ፦ ነፃ አውጪው
በሐዲስና በጥንታዊ መጻሕፍት ውስጥየተጠቀሱ ስሞች
- አጂር፦ የዳነው
- ኡህያድ፦ መላሹ
- አሐድ፦ አቻ የሌለው
- አኹማኽ፦ ከእውነተኛ መገዛት የኾነ
- አል-አትቃ፦ ፈጣሪን ፈላጊው
- አል-አበር፦ በጣም ጻድቅ የኾነው
- አል-አብያድ፦ ፍትሃዊው
- አል-አግሀር፦ በጣም አንጸባራቂው
- አል-አንፋር፦ ብዙ ጉባኤ ያለው
- አለል-አስደቅ፦ በጣም እውነተኛ የኾነው
- አል-አጅዋድ፦ ብዙ ምርኮ ያለው
- አሽጃዕ አል-ናስ፦ ከሰው ልጆች ኹሉ ድፍረት ያለው
- አል-አኺዝ ቢ አል-ሁጁዛት፦ የወገብ ማሰርያ ያዢው
- አርጃህ አል-ናስ ዓቅለን፦ በዕውቀት ከሰው ልጆች ኹሉ አንደኛ
- አል-አዕለሙ ቢላህ፦ በአላህ ዕውቀት ከኹሉ በላጩ
- አል-አኽሻ ሊላህ፦ አላህን በመፍራት አንደኛ
- አፍሳህ አል-ዐረብ፦ ከአረቦች ኹሉ በንግግር በላጩ
- አኽታሩ አል-አንቢያዒ ታቢዐን፦ በተከታዮች ብዛት አንደኛ የኾነ ነቢይ
- አል-አክራም፦ ክፍ ያለ ክብር ያለው
- አል-ኢክሊል፦ አክሊሉ
- ኢማም አል-ነቢዪን፦ የነቢያት መሪ
- ኢማም አል-ሙጠቂን፦ ፈጣሪን ለሚፈልጉት መሪ
- ኢማም አል-ናስ፦ የሰው ልጆች መሪ
- ኢማም አል-ኸይር፦ መልካሙ መሪ
- አል-አማን፦ ደህነት
- አመነቱ አስ-ሀቢህ፦ የአጃቢዎቹን እምነት ጠባቂ
- አል-አወል፦ የመጀመርያ
- አል-አኺር፦ የመጨረሻ
- ኡኽራያ፦ የመጨረሻ (ከነቢያት)/ ስሙ በቶራ ውስጥ
- አል-አዋህ፦ አህ ብሎ የሚጮኸው
- አል-አብታሂ፦ መካና ሚና መካከል የሚገኘው ቢታህ ከተባለ ቦታ የመጣ
- አል-ባሪቅሊጥ፣ አል-ባርቃሊጦስ፦ ጰራቅሊጦስ/ የቅድስና መንፈስ/ የዋሁ
- አል-ባቲን፦ ስውሩ
- ቢዑምዝማዑድ፦ በቶራ ውስጥ ከሚገኙ ስሞቹ መካከል አንዱ
- አል-ባይን፦ አጋላጭ
- አል-ታቂ፦ ራሱንውጠባቂወ
- አል-ቲሃሚ፦ ቲሃማ ከተባለ ቦታ የመጣ
- አል-ሢማል፦ ጠባቂው
- አል-ጀበር፦ ቁጡው
- አል-ኸቲም፦ አታሚው
- አል-ሐሺር፦ ሰብሳቢው
- ሐት ሐተ፦ በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ የሚገኝ ስሙ
- አል-ሐፊዝ፦ ጠባቂው/ ሸምዳጁ
- ሐሚድ፦ ተመስጋኙ
- ሐሚል ሊዋዕ አል-ሐምድ፦ የምስጋናን ሰንደቅ የያዘው
- ሐቢብ አላህ፦ የአላህ ተወዳጅ
- ሐቢብ አል-ረህማን፦ የርህሩሁ ተወዳጅ
- ሐቢተን፦ በኢንጂል ውስጥ የሚገኝ ስሙ
- አል-ሑጃ፦ ማረጋገጫው
- ሒርዛን ሊ አል-ዐይን፦ ክፉ ዓይን (ቡዳ) ተከላካዩ
- አል-ሐሲብ፦ በቂው/ ታላቅ አወላለድ የተወለደው
- አል-ሐፊዝህ፦ ጠባቂው/ ሸምዳጁ
- አል-ሐኪም፦ ጠቢቡ
- አል-ሐሊም፦ የዋሁ
- ሐሚታያ፦ የአምልኮ ቦታው ጠባቂ
- አል-ሐማይድ፦ ተመስጋኙ
- አል-ሐሚድ፦ የተመሠገነው
- አል-ሐይ፦ ሕያው የኾነው
- ኸዚን መል አላሀ፦ የአላህ ግምጃ
- አል-ኸሺዕ፦ አስፈሪው
- አል-ኻዲዕ፦ የተገዛው
- ኸቲብ አል-ነቢይን፦ ከነቢያት አንደበተ ርቱዕ
- ኸሊል አላህ፦ የአላህ የቅርብ ወዳጅ
- ኸሊፋት አላህ፦ የአላህ ወኪል
- ኸይር አል-ዓለሚን፦ በዓለም ውስጥ ታላቁ መልካም
- ኸይሩ ኸልቅ አላህ፦ በአላህ ፍጥረት ታላቁ መልካም
- ኸይሩ ሐዚሂ አል-ኡማ፦ የዚህ ትውልድ በላጭ
- ደር አል-ሒክማ፦ የጥበብ ቤት
- አል-ዳሚግህ፦ አስወጋጁ (ሐሰትን)
- አል-ዚክር፦ ዝክር/ ማስታወስ
- አል-ዘካር፦ ትልቅ የማስታወስ ችሎታ ያለው
- አል-ራፊዕ፦ ከፍ አድራጊው
- ራኪብ፦ አል-ቡራቅ፦ በቡራቅ የሚጋልበው
- ራኪብ አል-ጀመል፦ ግመል ጋላቢው
- ራህመቱን ሙህዳት፦ የተሰጠ ምህረት
- ረሱል አል-ረህማን፦ የምህረት መልእክተኛ
- ረሱል አል-ራሃ፦ የእረፍት መልእክተኛ
- ረሱል/ ነቢ አል-መላሂ፦ የጦርነት መልእክተኛ/ ነቢይ
- ሩክን አል-ሙተወዲዕን፦ የትሁታን አምድ
- አል-ረሀብ፦ በጣም አስፈሪው
- ሩህ አል-ሐቅ፦ የእውነት መንፈስ
- ሩህ አል-ቁዱስ፦ መንፈስ ቅዱስ
- አል-ዘሂድ፦ ያለ ምንም የሚሠራ
- አል-ዘኪ፦ ንፁህ የኾነው
- አል-ዘምዘሚ፦ የዘምዘም ወራሽ
- ዘይኑ መን ዋፋ አል-ቂያማ፦ በፍርድ ቀን የሚገኙት ኹሉ ጌጥ
- ሰቢቅ፦ በላጩ
- ሰርሓቲሎስ፦ ጰራቅሊጦስ (በሦርያንኛ)
- ሰዒድ፦ የሚበቃ/ ትክክለኛ ምርጫ
- አል-ሰላም፦ ሰላም
- ሰይድ አል-ናስ፦ የሰው ልጆች አለቃ
- ሰይድ ወለድ አደም፦ የአዳም ልጆች አለቃ
- ሰይፍ አላህ፦ የአላህ ሰይፍ
- አል-ሻሪ፦ ሕግ ሰጪው
- አል-ሻፊ፦ አማላጁ
- አል-ሻፊዕ፦ ቋሚ አማላጁ
- አል-ሙሸፈዕ፦ ምልጃ የተሰጠው
- አል-ሸኪር፦ አመስጋኙ
- አል-ሸካር፦ በጣም አመስጋኙ
- አል-ሸኩር፦ ለዘላለም አመስጋኙ
- ሳሂብ አል-ታጅ፦ ዘውድ የደፋው
- ሳሂብ አል-ሁጃ፦ የማስረጃው አምጪ
- ሳሂብ አል፦-ሀውድ፦ የምንጭ ባለቤት
- ሳሂብ አል-ከውሠር፦ የከውሠር ወንዝ ባለቤት
- ሳሂብ አል-ሀቲም፦ በካዕባ ፊት የሚገኘው ፍርድ ቤት ባለቤት
- ሳሂብ አል-ኸቲም፦ የማህተሙ ባለቤት
- ሳሂቡ ዘምዘም፦ የዘምዘም ባለቤት
- ሳሂብ አል-ሱልጣን፦ የሥልጣን ባለቤት
- ሳሂብ አል-ሰይፍ፦ የሰይፍ ባለቤት
- ሳሂብ አል-ሸፈዓት አል-ኩብራ፦ ታላቁ አማላጅ
- ሳሂብ አል-ቀዲብ፦ የብትር ባለቤት
- ሳሂብ አል-ሊዋዕ፦ የሰንደቅ ተሸካሚ
- ሳሂብ አል-መህሻር፦ የመሰብሰብ ጌታ
- ሳሂብ አል-ሙደራዕ፦ የጦር መሣርያ የታጠቀው
- ሳሂብ አል-መቀም አል-መሽዓር፦ ባለ ምልክት ቦታ ያለው
- ሳሂብ አል-ሚዕራጅ፦ ወደላይ የወጣው
- ሳሂብ አል-ማሕሙድ፦ የከበረ ቦታ ያለወው
- ሳሂብ አል-ሚንበር፦ የወንበሩ/ የምስባክ ባለቤት
- ሳሂብ አል-ነዕለይን፦ ሸበጥ ጫማ አድራጊው
- ሳሂብ አል-ሂራዋ፦ ሸምበቆ ያዡ
- ሳሂብ አል-ዋሲላ፦ የሁኔታው/መንገዱ ባለቤት
- ሳሂብ ላ ኢላሀ ኢለላ፦ “ከአላህ በስተቀር አምላክ የለም” የሚለውን የሚያስተምር
- አል-ሳዲቅ፦ እውነተኛው/ ጻድቁ
- አል-መስዱቅ፦ የጸደቀው/ የተረጋገጠው
- አል-ሳሊህ፦ ጻድቅ የኾነው
- አል-ዳቢት፦ አለቅነት የተሰጠው
- አል-ዳሁክ፦ ደስተኛው
- አል-ጣሂር፦ ንፁህ የኾነው
- ታብ ታብ፦ ብሩክ የሚታወስ/ ስሙ ቶራ ውስጥ የሚገኝ
- አል-ጠይብ፦ ሰላምተኛው
- አል-ዛሂር፦ ኗሪው
- አል-ዐቂብ፦ በውርስ የመጨረሻው
- አል-ዐድል፦ ፍትሃዊው
- አል-ዐረቢ፦ አረባዊው/ አረብኛ ተናጋሪው
- ኢስመቱላህ፦ የአላህ መጠበቂያ
- አል-ዐዚም፦ ብዙ የኾነው
- አል-ዐፊፍ፦ የተቀደሰው
- አል-ዐሊ፦ ታላቁ
- አል-ጋፉር፦ በተደጋጋሚ ይቅር ባይ
- አል-ጋይሥ፦ ዝናብ/ እርዳታ
- አል-ፈቲህ፦ ድል ነሺው
- አል-ፋሪቅ፦ በመልካምና በክፉ መካከል የሚለይ
- ፋርቂላተ፦ ጰራቅሊጦስ
- ፈርት፦ ፈር ቀዳጁ
- አል-ፈሲህ፦ የንግግር ችሎታ ያለው
- ፈላህ፦ ሐሴት/ ስኬት
- ፊዓት አል-ሙስሊሚን፦ የሙስሊሞች ዋና አካል
- አል-ቀዒም፦ ቆሞ የሚያስጠነቅቀው
- ቃሲም፦ አከፋፋዩ
- ቃዒድ አል-ኸይር፦ ወደ መልካም የሚመራ መሪ
- ቃዒድ አል-ግሁር አል-ሙሐጀሊን፦ የመብራት መሪ
- አል-ቀታል፦ ተዋጊው/ ገዳዩ
- ቁሠም፦ ፍጹም የኾነ ስነ ምግባር ያለው/ መልካም ነገሮች ኹሉ የተሰጡት
- ቀድማያ፦ ቀዳሚው (ከነቢያት)/ ስሙ ቶራ ውስጥ የሚገኘው
- አል-ቁራሺ፦ ከቁራይሽ የኾነው
- አል-ቀሪብ፦ የቀረበው
- አል-ቀይም፦ ቀጥተኛው
- አል-ከፍ፦ እንዲቆም አድራጊው (አለመታዘዝን)
- አል-መጂድ፦ አክባሪው
- አል-ማሂ፦ አስወጋጁ (አለማመንን)
- አል-ማዕሙን፦ ከጉዳት የጠራ
- አል-ሙባረክ፦ የተባረከው
- አል-ሙተቂ፦ ፈጣሪን ፈላጊው
- አል-ሙተመኪን፦ ጠንካራ የኾነው
- አል-ሙተወኪል፦ ሙሉ በሙሉ በአላህ ላይ የተደገፈው
- አል-ሙጅታበ፦ የተመረጠው
- አል-ሙኽቢት፦ በአላህ ፊት ትሁት የኾነወው
- አል-ሙኽቢር፦ የዜና አምጪ
- አል-ሙኽታር፦ የተመረጠው
- አል-ሙኽሊስ፦ ፍጹም ቅን የኾነው
- አል-ሙርተጀ፦ በጣም የተጠበቀው
- አል-ሙርሺድ፦ ምሪት የኾነው
- መርሐማ፦ አጠቃላይ ይቅርታ
- መልሐመ፦ ታላቅ ጦርነት
- መርግሐማ፦ ታላቅ ኃይል
- አል-ሙሰደድ፦ ጻድቅ የተደረገው
- አል-መስዑድ፦ ኃብት
- አል-መሲህ፦ የተቀባው
- አል-መሽፉዕ፦ ምልጃ የተሰጠው
- መሸቃህ/ ሙሸፋህ፦ የተመሰገነው
- አል-ሙስጠፋ፦ የተመረጠውና ንጹህ የተደረገው
- አል-ሙስሊህ፦ አዳሹ
- አል-ሙተሒር/ አል-ሙተሐር፦ ንጹህ አድራጊው/ ንጹህ የኾነው
- አል-ሙቲዕ፦ ታዛዡ
- አል-ሙዕቲ፦ ሰጪው
- አል-ሙዓቂብ፦ በምልጃ መጨረሻ የመጣው
- አል-ሙዓሊም፦ መምህሩ
- አል-ሚፍዳል፦ በጣም ለጋሹ
- አል-ሙፈደል፦ ከሌሎቹ በላይ የተደረገ
- አል-ሙቀደስ፦ የተቀደሰው
- ሙቂም አል-ሱና፦ የመንገዱ መሥራች
- አል-ሙክሪም፦ ሌሎችን ያከበረው
- አል-መኪ፦ የመካው
- አል-መዳኒ፦ የመዲናው
- አል-ሙንተኻብ፦ የተመረጠው
- አል-ሙንሐሚነ፦ የተመሰገነው (በሦርያንኛ)
- አል-ሙንሲፍ፦ እኩል አድራጊው
- አል-ሙኒብ፦ በተደጋጋሚ ተጸጻቹ (ንስሐ ገቢው)
- አል-ሙሐጂር፦ ስደተኛው
- አል-መሕዲ፦ በትክክል የተመራው
- አል-ሙሐይሚን፦ ጠባቂው/ ዘብ የሚቆመው
- አል-ሙዕተሚን፦ የታመነው
- ሙሰል፦ ምህረት የተደረገለት (በቶራ ውስጥ)
- ማዝ ማዝ/ ሙዝ ሙዝ/ ሚዝ ሚዝ፦ የተባረከ ትዝታ
- አል-ናሲኽ፦ ሻሪው
- አል-ናሺር፦ አዋጅ ነጋሪው
- አል-ናሲህ፦ በቅንነት መካሪው
- አል-ናሲር፦ አጋዡ
- ነቢ አል-መርሐመ፦ የአጠቃላይ ምሕረት ነቢይ
- አል-ነሲብ፦ የከበረ የዘር ሐረግ ያለወው
- አል-ነቂይ፦ ግልፅ የኾና
- አል-ነቂብ፦ አደራ የተሰጠው/ ጠባቂው
- አል-ሐሺሚ፦ ከሐሺም ዘር የኾነው
- አልል-ዋሲጥ፦ የከበሩ ቤተሰቦች ኹሉ ማዕከል
- አል-ዋዒድ፦ የአስፈሪ ዜና ነጋሪው
- አል-ወሲል፦ መጠቀሚያ መንገድ
- አል-ዋፊ፦ ተስፋውን/ ቃሉን አክባሪ
- አቡ አል-ቃሲም፦ የቃሲም አባት
- አኑ ኢብራሂም፦ የኢብራሂም አባት
- አቡ አል-ሙዕሚኒን፦ የምዕመናን አባት
- አቡ አል-አራሚል፦ የመበለቶች አባት
ከአልጀዙሊ (870) ዳላይል አል–ከይራት የተወሰዱ
- ዋሒድ፦ ልዩ የኾነው
- ሰይድ፦ አለቃ
- ጃሚዕ፦ አንድ አድራጊው
- ሙቅታፊ፦ ምሳለሌውን ሰዎች የሚከተሉት
- ካሚል፦ ፍጹም የኾነው
- ናጂ አላህ፦ የአላህ የቅርብ ጓደኛ
- አፊ አላህ፦ የአላህ ምርጡና ንጹህ የተደረገው
- ከሊም አላህ፦ ከአላህ ጋር ተነጋጋሪው
- ሙህዪን፦ ሕይወት ሰጪ
- ሙነጂ፦ አዳኝ
- ሙዕሉም፦ ከሚታወቅ ደረጃ የተገኘ
- ሻሒር፦ ታዋቂው
- መሽሁድ፦ የሚታየው
- ሚስባህ፦ መብራት
- መድዑው፦ የሚጠሩት
- ሙጂብ፦ ለጥሪ ምላሽ ሰጪ
- ሙጂብ፦ ጥያቄው የሚመለስለት
- ሀፊይ፦ የሚጠጋጋና ደግ
- ሙከረም፦ በጣም የተከበረው
- መቲን፦ ተስፋ የማይቆርጠው
- ሙዐሚል፦ ተስፋን አዳሽ
- ወሱል፦ አድራሽ
- ዙ ሁርማ፦ የተቀደሰ
- ዙ መካነ፦ ከፍ ያለ መኖርያ ያለው
- ዙ ዒዝ፦ ታላቅነት የተሰጠው
- ዙ ፈድል፦ ቀደም ሲል የነበረ
- ግሃውሥ፦ ረዳት
- ግሀያሥ፦ በየጊዜው የሚረዳ
- ሐዲያቱላህ፦ የአላህ ስጦታ
- ሲራት አላህ፦ የአላህ መንገድ
- ዚክሩላህ፦ የአላህ ማስታወሻ/ ዝክር
- ሒዝቡላህ፦ የአላህ ቡድን
- ሙንተቀ፦ በጥንቃቄ የተመረጠ
- አቡ አል-ጣሂር፦ የጣሂር አባት
- በር፦ ጻድቅ፣ ግዴታ ያለበት
- ሙቢር፦ የበላይ የሚኾነው
- ወጂህ፦ በአላህ ዓይን የተመረጠ
- ነሲህ፦ በትክክለኛ ምክር ከፍ ያለ
- ወኪል፦ የታመነ/ የሚደገፉት
- ከፊል፦ ዋስትና ሰጪ/ ጠባቂ
- ሻፊቅ፦ የሚንከባከብ/ የሚወድድ
- ሩህ አል-ቂስት፦ የፍትህ መንፈስ
- ሙክተፊ፦ በትንሽ ነገር የሚሠራ
- ባሊግህ፦ ግቡን የመታ?
- ሻፊ፦ ፈዋሽ
- ዋሲል፦ ግቡን የመታ
- መውሱል፦ የተቆራኘ
- ሳዒቅ፦ እያሰበ የሚፈፅም
- ሙሕዲ፦ ምሪት
- ሙቀደም፦ ቀደም ሲል የነበረው
- ፋዲል፦ እጅግ በጣም ጥሩ የኾነው
- ሚፍታህ፦ ቁልፍ
- ሚፍታህ አል-ራህማ፦ የምህረት ቁልፍ
- ሚፍታህ አል-ጀነ፦ የገነት ቁልፍ
- ዓለም አል-ኢማን፦ የእምነት ልኬት
- ዓለም አል-ያቂን፦ የእርግጠኛነት ልኬት
- ደሊል አል-ኸይረት፦ ወደ መልካም ነገር የሚመራ
- ሙሰሂህ አል-ሐሰናት፦ የመልካም ሥራዎች አጽዳቂ
- ሙቂል አል-ዓሣራት፦ የግል ስህተቶችን አስወጋጅ
- ሰፉህ ዓን አል-ዘላት፦ መቅደምን የማይቀበል
- ሳሂብ አል-ቀደም፦ የዕድል ፋንታ ባለቤት
- መኽሱስ ቢ አል-ዒዝ፦ ብቻውን ሃያልነት የሚሰጠው
- መኽሱስ ቢ አል-መጅድ፦ ብቻውን ክብር የሚሰጥጠው
- መኽሱስ ቢ አል-ሸረፍ፦ ብቻውን አክብሮት የሚሰጥጠው
- ሳሒብ አል-ፈዲላ፦ ታላቁን የቀዳሚነት ቦታ የያዘው
- ሳሂብ አል-ኢዛር፦ የአንበሳን መደረብያ የለበሰው
- ሳሂብ አል-ሪዳዕ፦ መደረብያ ለባሹ
- ሳሂብ አል-ደረጃ አል-ራፊዓ፦ የታላቁ ደረጃ ባለቤት
- ሳሂብ አል-ሚግህፋር፦ የራስ ቁር አጥላቂው?
- ሳሂብ አል-በያን፦ አፈ ቀላጤው
- ሙተሐር አል-ጀናን፦ ልቡ የነጻ
- ሳሂህ አል-ኢስላም፦ የእስልምና ፍጹማዊነት
- ሰይድ አል-ከውነይን፦ የሰው ልጆችና የጂኒዎች አለቃ
- ዐይን አል-ነዒም፦ የሐሴት ምንጭ/ ሐሴት ራሱ
- ዐይን አል-ግሁር፦ የአንጸባራቂው ምንጭ/ ነጸብራቅ ራሱ
- ሰዕዱላህ፦ በአላህ ፍስሐ የወረደበት
- ሳዕድ አል-ኸልቅ፦ በፍጥረት ካላይ የወረደ ፍስሐ
- ኸቲብ አል-ዑማም፦ ለሕዝቦች ተናጋሪ
- ዓለም አል-ሁዳ፦ የምሪት ሰንደቅ
- ካሺፍ አል-ኩብራ፦ የጠላትነት አስወጋጅ
- ራፊዕ አል-ሩጥባ፦ ደረጃን ከፍ አድራጊ
- ዒዝ አል-ዐረብ፦ የአረቦች ክብር
- ሳሂብ አል-ፈረጅ፦ የነፃነት አምጪ
አምልኮ በአንደበት ብቻ ሳይሆን የፈጣሪን ክብር ለፍጡር በመስጠትም ይገለጻል። ይህ ዝርዝር ብዙ የአላህ ስሞችን በግልጽ ለሙሐመድ ያጎናጽፋል፣ ሙስሊሞች እውነት ሙሐመድን አታመልኩትም? መልሱን ለኅሊናችሁ።