የኒቅያ የሃይማኖት መግለጫ

የኒቅያ የሃይማኖት መግለጫ (ሁለተኛው)

ሁሉን በሚችል ሰማይንና ምድርን፣ የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ። እርሱ ብቻ የአብ ልጅ በሚሆን፣ ዓለም ሳይፈጠር ከአብ በተወለደ፣ ከአምላክ በተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን በተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ በተገኘ እውነተኛ አምላክ፣ በህልውናው ከአብ ጋር አንድ የሆነ፣ በተፈጠረ ሳይሆን በተወለደ፣ ሁሉ በእርሱ በሆነ፣ ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለ ደህንነታችንም ከሰማይ በወረደ፣ በመንፈስ ቅዱስ ከድንግል ማርያም ሥጋ ነስቶ ሰው በሆነ፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ በተሰቀለ፣ መከራ በተቀበለ፣ በሞተ፣ በተቀበረም፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም እንደተጻፈ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ በተነሣ፣ ወደ ሰማይም በወጣ፣ በአብ ቀኝ በተቀመጠ፣ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ዳግመኛ በክብር በሚመጣ፣ ለመንግሥቱም ፍጻሜ በሌለው በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ። ከአብና ከወልድ ጋር በሚሰገድለትና በሚከበር፣ ከአብ በሚሠርጽ፣ በነቢያት በተናገረ፣ የሕይወት ጌታና ሰጪ በሆነ፣ በመንፈስ ቅዱስም አምናለሁ። የሁሉም በሆነች በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንም አምናለሁ። ለኃጢአት ማስተስረያ በአንዲት ጥምቀትም አምናለሁ። የሙታንን ትንሣኤና ገና የሚመጣውን ዓለም ሕይወትም እጠባበቃለሁ። አሜን