የቁምራን ጥቅልሎችን በተመለከተ በወንድም ዳንኤልና በኡስታዝ የሕያ መካከል የተደረገ ውይይት
ተከታዩ ውይይት ዲሴምበር 2018 በፌስቡክ ገጻችን ላይ በወንድም ዳንኤልና የሕያ ኢብኑ ኑህ በተባለ ኡስታዝ መካከል የተደረገ ሲሆን ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘነው እዚህ አምጥተነዋል፡፡ ለውይይቱ መነሻ ከሆነው ኦሪጅናል ፖስት በማስከተል በአንድ ሙስሊም ተወያይ አማካይነት በተደረገለት ጥሪ ወደ ገጹ በመምጣት ኡስታዝ የሕያ ውይይቱን ጀምሮታል፡፡ ምልልሱን በመከታተል የራሳችሁን ፍርድ ትሰጡ ዘንድ እንጋብዛለን፡፡
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ምን ያህል ያውቃሉ? በጥንታውያን ጽሑፎች ብዛት መጽሐፍ ቅዱስ የዓለም ቁጥር አንድ መጽሐፍ መሆኑን ያውቃሉ? “ከ5,686 በላይ የሚሆኑ የታወቁ የአዲስ ኪዳን የግሪክ ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች አሉ፡፡ በተጨማሪም 10,000 የላቲን ቩልጌቶችና ሌሎች 9,300 ቀዳሚያን ቅጂዎች፣ በአጠቃላይ ከ 25,000 በላይ ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች አሉ፡፡ ከጥንት መዛግብት መካከል አንዱም እንኳ ይህንን ያህል ቁጥርና የማረጋገጫ ብዛት ወደ ማስመዝገብ የቀረበ የለም፡፡ በንፅፅር እስከ አሁን የተረፉ 643 የእጅ ጽሑፎች ብቻ ያሉት የሆሜር ኢሊያድ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡”
ተከታዩን ጽሑፍ በማንበብ ከዚህ እውነታ ጋር ይተዋወቁ፡፡ http://www.ewnetlehulu.net/am/the-holy-bible/manuscripts/
Abdulfatah Kader ለምን ይዋሻል? ለምሳሌ ኦሪት ሙሴ ነው የፃፈው ከመባሉ ውጭ በፅሁፍ ያስተላለፈውን ስረ–መሰረተ አናገኝም። እሱ ይቅርና አምስቱ መፅሐፍት መሰረት አድርገው የተነሱበት አራቱ ምንጮች የሉም። እንደዚሁ የዕብራይስጥ ቀደማይ እደ–ክታባት(manuscript) አናገኝም። ዛሬ ላይ የቀዳማይ እደ–ክታባ ተብሎ የተመዘገባው በ280(እ.ኤ.አ) የእስክንድርያ 70 የአይሁድ ሊቃውንት አምስቱ መፅሐፍትን ከዕብራይስጥ ወደ ኮይኔ ግሪክ የተረጎሙት ነው
በአጠቃላይ እሪት ከሙሴ ሕልፈት ብኋላማንነታቸው በማይታወቁ ሰዎች ተፃፈና በጊዜ ሂደት እየተጨመረና እየተቀነሰ የመጣ መፅሐፍ መሆኑ ተረጋግጧል።
ለምን መዋሸት አስፈልገ?
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
ለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net Abdulfatah ኮፒ ከማድረግህ በፊት የመረጃህን ትክክለኝነት አጣራ፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት የተጻፉ ከመጽሐፈ አስቴር በስተቀር ሁሉንም የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የሚወክሉ የእብራይስጥ ጽሑፎች በቁምራን ዋሻዎች ተገኝተዋል፡፡ በሙሴ ዘመን ስለተጻፉት የመጀመርያዎቹ ጽሑፎች የምትጠይቅ ከሆነ ከዛሬ 3500 ዓመታት በፊት የነበሩ ማቴሪያሎች ለምን እስከ ዛሬ አልቆዩም? ብሎ የሚጠይቅ ጅል ብቻ ነው፡፡ የቁርአን ኦሪጅናል ጽሑፎችም ስለሌሉ እንዲህ ያለ ጥያቄ ከሙስሊም አይጠበቅም፡፡ በእጃችን የሚገኙት ጽሑፎች ሁሉ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ያለ ምንም መለዋወጥ ዘመናትን ተሻግረው እንደኖሩ ያረጋግጣሉ፡፡ ተራ ውንጀላ ማስረጃ አይሆንም፡፡
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
Abdulfatah Kader ና ሳቅ በአላህ ሰል ማን ሀቢቢ
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
ለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net Abdulfatah የጠቀስከው መዝገበ ቃላት ምሑራን ስላስቀመጡት ግምት ነው የሚናገረው፡፡ በእነርሱ ግምት መሠረት ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ቅድመ ክርስቶስ ጀምሮ የነበሩት መምሕራንና ነቢያት በጽሑፍ የነበሩ ሕግጋትን አቀናብረዋል፡፡ አንተ ግን የመዝገበ ቃላቱን ሐሳብ በተሳሳተ መንገድ ከመረዳትህም በላይ በማቀናበሩ ሒደት ውስጥ ነቢያት እንደነሩበት የተጻፈውን ቆርጠህ አውጥተህ ነው የጠቀስከው፡፡
የንፅፅር ተማሪ ያለ ማስረጃ ያወራል እንዴ? እስኪ ቀደም ሲል ለተናገርካቸው ነገሮች ማስረጃ አቅርብ፡፡ የተናገርካቸው ነገሮች ማን በሚባል ምሑር፣ ምን በሚል መጽሐፍ የትኛው ገፅ ላይ ተጻፈ? እውነቱን ለመናገር ስለ ቁምራን ጥቅልሎች ሰምቶ የማያውቅ “የንፅፅር ተማሪ” አንተን አየሁ! 😅
እስኪ የቁርአን ኦሪጅናል በዚህ ዘመን ስለመኖሩ ያለህን ማስረጃ ጥቀስልኝ፡፡
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
Abdulfatah Kader ስለ ውንጌልም ካወረን ጀግሞ የሌሎችም ወንጌላትን ኦሪጅናል ጹሁፍ በእጃችን አይገኝም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በእጃችን አይደለም ኦሪጅናሉ የኮፒ ኮፒው እንኳን የለንም፡፡ በአንጻራዊነት ጥንታዊ ናቸው የሚባሉት እደ–ክታባት /Manuscripts/ የቫቲካነስ ኮዴክስ/Codex Vaticanus/ እና የሲናይቲከስ ኮዴክስ/Codex Sinaiticus/ ናቸው፡፡ የእነዚህ እድሜ ደግሞ የሚጀምረው ከ4ኛው ክፍለዘመን ነው፡፡ ይህ ማለት እንኝህ የኮፒ ኮፒ እንኳን አይደሉም ማለት ነው፡፡
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
ለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net Abdulfatah ስለምታወራው ነገር ምንም አታውቅም፡፡ ቫቲካነስና አሌክሳንዲሪነስ ሁሉንም የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት አንድ ላይ ይዘው የተገኙ ቀዳሚያን ጽሑፎች እንጂ ብቸኛ ቀዳሚያን ጽሑፎች አይደሉም፡፡ ከሁለቱ በክፍለ ዘመናት የሚቀድሙ ተናጠል የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ጽሑፎች ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል የጆን ሪላንድ የዮሐንስ ወንጌል ቁራጭ በ130 ዓ.ም. የተጻፈ ሲሆን ከኦሪጅናሉ ጋር ያለው የጊዜ ልዩነት 40 ዓመት ብቻ ነው፡፡ ኦሪጅናል ኦሪጅናል የምትለው የቁርአንም ኦሪጅናል የለም፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፎች የተጻፉበት ማቴሪያል 2000 ዓመታት ያህል የመቆየቱ ዕድል በጣም አናሳ ነው፡፡ ምሑራን የአንድን መጽሐፍ ተዓማኒነት የሚገመግሙት በኮፒዎች ብዛትና ጥራት እንጂ ኦሪጅናሉ የግድ መኖር አለበት አይሉም፡፡
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
ለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net የቁርአንም ኦሪጅናል የለም፡፡ አለ የምትል ከሆነ አሳየን፡፡ ምሑራን የአንድን መጽሐፍ ተዓማኒነት ለማረጋገጥ ኦሪጅናሉ የግድ መኖር አለበት አይሉም፡፡ ከዛሬ 2000 ዓመት በፊት የተጻፈ ማቴሪያል መበስበሱ የግድ ነው፡፡ እስኪ 1ኛ ክፍል ከተማርክባቸው ደብተሮች መካከል ሳይበላሹ እጅህ ላይ የሚገኙት ስንት ናቸው?
የንፅፅር ተማሪ ነኝ አላልክም እንዴ? ምነው በ2 ኮሜንት ትንፋሽ አጠረህሳ?
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
Abdulfatah Kader ኡስታዝ አንዴ ብቅ በትል?! Yahya Ibnu Nuhe
ለእስልምና መልስ ኡስታዝን በሐፍሷ ቤት የነበረውን ኦሪጅናል ቁርአን ይዘህ ና በለው፡፡
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
ሰል ማን ለእስልምና መልስ…
ከመጽሐፈ አስቴር በስተቀር ሁሉም የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት በቁምራን ዋሻ ተገኝተዋል ብለሃል። እስኪ ማስረጃውን ስጠን።
ቁምራን ዋሻ የተገኙ የተወሰኑ ጥቅሎች አሉ። እነሱም ቢሆኑ አሁን ካለው የብሉይኪዳን ኮፒ በእጅጉ ይለያያሉ።
አንተ ከዚህ የተለየ አለኝ ካልክ ማስረጃህን ስጠን እስኪ።
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
ለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net Yahya Ibnu Nuhe ኦሪጅናል የቁርአን ጽሑፍ አለ ብለህ አስተማርከው እንዴ? 🤔
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
ለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net ሰል ማን ማስረጃውንማ ከላይ በለጠፍኩት አርቲክል ውስጥ በስፋት ጠቅሻለሁ፡፡ አንብበውና ጥያቄ ካለህ ተመለስ፡፡ በጣም ይለያያሉ ላልከው ቁርአንን ጨምሮ እንደ ማንኛውም የጥንት መጻሕፍት መጠነኛ የንባብ ልዩነቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ መሠረታዊ በሆነ ሁኔታ ልዩነት እንደሚያሳዩ የተናገረ ምሑር ግን አላየሁም፡፡ ስለ Textual Criticism ማውራት የምትፈልግ ከሆነ ቁርአንንም ለመፈተሽ ዝግጁ ከሆንክ ከፍ ብለን መነጋገር እንችላለን፡፡
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
Yahya Ibnu Nuhe ለእስልምና መልስ ሌላውን ላቆይልህና ስለ ቁምራን እናውራ፤ እስኪ ዲቴል ይዘቱ የት እንዳለና ይፋ ስለመሆኑ ንገረኝ
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
Yahya Ibnu Nuhe ሰል ማን የቁምራን ማኑስክሪፕት እራሱኮ ከሙሴ ዘመን ጋር ያለው ልዩነት ወደ አንድ ሺህ አመት ይጠጋል Regardless of its Content.
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
ሰል ማን ከYahya Ibnu Nuhe ጋር ቀጥሉ። ኢንሻአላህ ከእኔ ጋር እጠራሃለሁ በዚሁ ርዕስ።
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
ለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net ስለ ቁምራን ጽሑፎች በአርቲክሉ ውስጥ በስፋት ጽፌያለሁ፤ አንብበውና ያልተስማማህበትን ነጥብ ጥቀስልን፡፡ ከዚያ እንነጋገራለን፡፡
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
ለእስልምና መልስ ስለ ዘመኑ ልዩነት ነው መነጋገር የምትፈልገው? ከተስማማህ በዚያ እንሂድ፡፡
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
Yahya Ibnu Nuhe ለእስልምና መልስ አርቲክሉ ውስጥ ስፔስፊካሊ የጠየቅኩትን ጥያቄ አድሬስ የሚያደርግ ክፍል ካለ አምጣውና አስቀምጠው፥ ድካም ይቀንሳል
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
Yahya Ibnu Nuhe ለእስልምና መልስ እሱን ለሰልማን ነው ያነሳሁለት ከላይ አንተን የጠየቅኩህ ስለይዘቱ ነው። ጊዜ ያለመኖር እንጅ ሁሉንም ባየው እኔም ደስ ይለኛል። እስኪ ያለችንን ሰአት የተሻለ ክፍል ላይ በመወያየት ላይ እናሳልፋትና በይዘቱ ላይ እናውራ
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
ለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net ስለ ይዘቱ ያለህ ጥያቄ ምንድነው? ወደ Textual Criticism አንገባም፡፡ ጥንቃቄ የሚፈልግና ሰፊ ርዕስ ነው፡፡ ስለ አጠቃላይ ይዘቱና ለመጽሐፍ ቅዱስ ተዓማኒነት ያለውን ፋይዳ ጠቅለል አድርገን መነጋገር እንችላለን፡፡
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
Yahya Ibnu Nuhe ለእስልምና መልስ በስሱ ለምን አንገባም? ይዘት ካነሳሁ ታዲያ Textual Critism ውስጥ ሳይገባ አለንዴ? ስለፋይዳውማ ቸርች ለሚመጡ ምዕመናን መንገሩ አይሻልም? የያዝነው ሰበካ አይደለም እኮ።
ለማንኛውም የቁምራንን ማኑስክሪፕት አስመልክቶ ከዘመነኛው ቶራህ ጋር ያለውን ምስስሎሽና ልዩነቶች እንዲሁም ለክርስቲያኖች እንደ እየሱስ ተከታይነት የሚያያዘው ነገር ከይዘት አንፃር መፈተሽ አለብን። እነዚህን ፕሩፍ ማድረግ ትችላለህ? ይዘቱን በማቅረብ?
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
Yared Amareg Amare Abdulfatah Kader የንጽጽር ተማሪ አስተማሪህ ኡዝታዝ ነው እንዲ? የረዳት ያለህ ኡስታዝየ ሆሆ ብለህ መጮክ ነው ኮፒ አቀ ?ክክ
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
ፀረ ቦርጭ ነኝ ደስ የሚል ውይይት ኑ ተጋበዙ
Nathay Danny
Selam Haile
Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
Bottom of Form
ለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net እንደርሱ ካልክ ከአቬሬጅ ሙስሊም የተሻለ ዕውቀት አለህ ማለት ነው፡፡ እንግዲያውስ ቁርአንንም በተመሳሳይ መንገድ ለመመዘን ዝግጁ መሆን ያስፈልግሀል፡፡ ሁለት ሚዛን የምትጠቀም ከሆነ የገዛ መጻሕፍትህን ጠቅሼ እንደምይዝህ እወቅ፡፡
“ይዘቱን በማቅረብ ፕሩፍ ማድረግ ትችላለህ?” ብለህ ስትጠይቅ ምን ማለትህ ነው? ለምሳሌ ከኢሳይያስ ጥቅልል አምጥቼ ፎቶግራፉን ባሳይህ አንብበህ አሁን ካለው የኢሳይያስ ቅጂ ጋር አንድ መሆን አለመሆኑን ልትነግረኝ ትችላለህ? እኔም አንተም የመጽሐፍ ቅዱስ የጥንት ጽሑፎች ሊቃውንት አይደለንም፡፡ ስለዚህ እዚህ አቅርበን ፕሩፍ የምናደርገው ምንም ነገር ስለሌለ ከዚህች የአውቃለሁ ባይነት ኮረብታ ላይ ወረድ በል፡፡ ጉዳዩን ያጠኑ ተዓማኒ ሊቃውንት የተናገሩትን ጠቅሰን ነው መነጋገር የምንችለው፡፡ በዚህ መሠረት ለምሳሌ ያህል ከሁሉም አነጋጋሪ የሆነውን የኢሳይያስን ጥቅልል በተመለከተ G. L. Archer እንደጻፈው የኢሳይያስ 95% ያህል የሚሆነው ቃል በቃል ከማሶሬቲክ ቅጂ ጋር አንድ ሲሆን ከልዩነት የተፈረጀው 5% መልእክቱን የማይለውጥ እዚህ ግባ የማይባል የብዕር ወለምታና የአጻጻፍ ልዩነት ነው፡፡ እንዲህ ነው ያለው፡– “the two copies of Isaiah discovered in Qumran Cave 1 proved to be word for word identical with our standard Hebrew Bible in more than 95 percent of the text. The 5 percent of variation consisted chiefly of obvious slips of the pen and variations in spelling” (G. L. Archer, Jr., A Survey of Old Testament Introduction, p. 19)
6 · Like · React · Reply · Edit · Dec 4, 2018
የመጀመሪያ ነጥብ ከላይ ስለ ቁምራን ማኑስክሪፕት እያወራን በመሀል ቁርዓንን እያነሳህ ጭንቅ ጥብብ የምትልበት ምክንያት አይገባኝም። ካስፈለገህ እኮ በአዲስ ርዕስ ፖስት አድርገህ መጥራት ነው። መመለሱ ሲከብድህ «አኔምኮ ጥያቄ አለኝ» አይነት የህጻን አርጊውመንት እያመጣህ እራስክን አታስገምግም።
ወደ ፖይንትህ ስገባ ይዘቱን አስመልክቶ እያንዳንዱን ክፍል ከምሁራን ስራዎች እያነሳህ ትተነትናለህ ብየ ጠብቄ ነበር። ጭራሽ አንተ አለመቻልህን ብቻ መግለጽ ሀፍረት ሁኖብህ ሁሉንም ሰው ባንተ ብልቃጥ ውስጥ አስገባሀው። ስለ ይዘቱ ኢምንት እንኳን አላወራህም። ያመጣሀው ድርሳንም የራሳችሁ ክርስቲያን የጻፈው የአማኝ ልብ ማደንደኛ ከሆነ የድህረ ገጽ ጹሁፎች ውስጥ ነው። ካስፈለገህ ድህረ ገጹን አስቀምጥልሀለው።
https://classicallatin.net/2000-year-old-leviticus-scroll-word-for-word-the-same/
https://bible.net/article/dead-sea-scrolls
ከዛ በዘለለ ያነሳሀውን ስለ ኢሳያስ እንኳን ካወራን እጅግ ሰፊ ልዩነት በማኑስክሪፕቱና በመጽሀፉ መካከል አለ። ይህንን አስመልክቶ በFrank Moore Cross and Shemaryahu Talmon ኢዲት ተደርጎ የተዘጋጀው QUMRAN and the HISTORY of the BIBLICAL TEXT የተሰኘው መጽሀፍ ከገጽ 147 ጀምሮ በሰፊው ይዳስሳዋል። ካስፈለግህ ጥቂቱን ለአብነት እዚህ አስቀምጥልሀለው። ቀድሞም አላውቀውም ብለህ መንገዱን ዘጋሀው እንጅ ። ወይንም ሙሉ መጽሀፉን ከፈለግክም በእጄ ስለሚገኝ ሶፍት ኮፒውን ልሰጥህ እችላለሁ።
2,000 year-old Leviticus scroll word-for-word the same classicallatin.net |
3 · Like · React · Reply · Delete · More · Dec 4, 2018
አያይዠ ኢሜጅ ለማስቀመጥ ብፈልግም ፔጅህ ለዚህ ፈንክሽን ዝግ ነው።
2 · Like · React · Reply · Delete · More · Dec 4, 2018
ፀረ ቦርጭ ነኝ ለእስልምና መልስ። ወዳጄ ሙስሊሞች ይዘው ለሚነሱት የክርስቲያኑ የ manuscript ጥያቄዎች የራሳቸውኑ መፃህፍታትን በራሳቸው መነፅር እዲያስረዱ ማድረጉ ብዙ ርቀው እዳይስቱ ብሎም እዳይከራከሩ ስለሚያደርጋቸው እና በተለይ የቁርአኑን ኦርጂናል ካለማሳየታቸው ጀምሮ ማረጋገጫ ማቅረብ እደማይችሉ መጠቆምህ መልካም አደረክ።
3 · Like · Reply · Delete · More · Dec 4, 2018
መደበቅ እንደቀረ አያውቁም
Like · React · Reply · Delete · More · Dec 4, 2018
አላህአለ ብሎ የቀባጠረው ስለየትኛው መፅሐፍ ቅዱስ ነው ከአላህ ጋር እንኳን አይግባቡም።
1 · Like · React · Reply · Delete · More · Dec 4, 2018
Abdulfatah Kader replied · 1 reply
ለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net Yahya Ibnu Nuhe ሙስሊሞች በሁለት ሚዛን እንደምትጠቀሙ ስለማውቅ በቁርአን ላይ የማትጠቀመውን ክራይቴርያ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ካልጫንኩ ብለህ ስትንፈራገጥ ከታየህ ግብዝነትህን ለማጋለጥ በገዛ ሰይፍህ ላይ እንድትወድቅ አደርግሀለሁ፡፡ ስለ Textual Variants አንስተህ መጽሐፍ ቅዱስ ተዓማኒ አይደለም የምትል ከሆነ በ1924ቱ ቁርአንና በቶፕካፒና ሰመርቃንድ ቁርአኖች መካከል የሚገኙትን ልዩነቶች ጠቅሼ ሚዛንህን ማስጠበቅ ግዴታዬ ነው፡፡ ይህ የማይለወጥ አቋሜ በመሆኑ ካልተመቸህ ከውይይቱ መሰናበት ትችላለህ፡፡
///እያንዳንዱን ክፍል ከምሁራን ስራዎች እያነሳህ ትተነትናለህ ብየ ጠብቄ ነበር /// ማለት ምን ማለት ነው? በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ጥቅሶችን እዚህ አምጥቼልህ ለእያንዳንዱ የምሑራንን ንግግር እየጠቀስኩልህ እንድተነትንልህ ነው የፈለከው? ዝም ብለህ ንግግር ለማሳበጥ አጉል ነገር አትናገር፡፡ ውይይት ለመጀመር የሚያስችለንን አንድ ማኑስክሪፕት ጠቅሼልሀለሁ ስለዚህ ሐሳብህን ሰብሰብ አድርግና በኢሳይያስ ጥቅልል ላይ እንነጋገር፡፡ ጊዜ የሚበቃን ከሆነ ወደ ሌላው ማለፍ እንችላለን፡፡
ሙስሊም አፖሎጂስቶች ከናንተ በላይ አዋቂ የሌለ በማስመሰል የሆነ ውጥር ውጥር የምትሉት ነገር ነው የሚገርመኝ፡፡ የየትኛውንም መጽሐፍ ክፍል ኢንተርኔት ላይ ብትፈልግ ማግኘት ትችላለህ ስለዚህ እኔ የጠቀስኩትን የሆነ ቦታ አገኘህ ማለት እኔ ከዚያ ምንጭ ወሰድኩ ማለት አይደለም፡፡ ብወስድ እንኳ ድረገጹ ተዓማኒ እስከሆ ድረስ ምንም ችግር የለውም፡፡ አንተ ወስደህ የማታውቅ አታስመስል፡፡ የሆነው ሆኖ እኔ የምሑሩን ጥቅስ የወሰድኩት ፕሮፌሰር ኖርማን ጌይዝለር በርዕሱ ላይ ጠቅሰው ከጻፉት መጽሐፍ ላይ ነው፡፡ ማስረጃውን ከፈለክ ፎቶሹት ላሳይህ እችላለሁ፡፡ ዝም ብለህ በግምት አታውራ፡፡ ደግሞ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ማኑስክሪፕት እያወራን ባለንበት ሁኔታ የጉዳዩ ባለቤቶች የሆኑትን ክርስቲያን ምሑራንን ካልጠቀስኩ ማንን እንድጠቅስ ፈለክ? ሙስሊም? ሒንዱ? ኢቲስት? የምታስቅ ሰው ነህ! 😅
2 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
Abdulfatah Kader replied · 1 reply
Yahya Ibnu Nuhe በ Replay ሳይሆን በኮሜንት እንነጋገር፡፡ ሌሎች ወገኖች እባካችሁን በዝምታ ተከታተሉ፡፡
2 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
Abdulfatah Kader replied · 1 reply
Yahya Ibnu Nuhe የኔ ሰዓት እኩለ ሌሊት ላይ ያሳያል፡፡ የምትሰጠኝን ምላሽ ጠዋት አንብቤ እመልሳለሁ፡፡ ቻው፡፡
Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
ፊት ለፊት ተወያይእንደ መሐመድ ድብቅ (ከመጋረጃ) ጀርባ አትሁን
Edited · 1 · Like · React · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
ባልከው መሰረት ከሪፕላይ ወጥቸልሀለው። ወደ ነጥቦችህ ከመግባቴ በፊት አንዳንድ ፈገግ ያደረጉኝን ነገሮች ልግለጽ። ሀሳብ ላይ ትኩረት አድርጌ እየጠየቅኩህ ቃላቶችህ ሁሉ ፐርሰናል ናቸው። ይህ ምን እንደሚጠቁም ታቃለህ? ለአርጊውመንቱ የተሻለ ሙግት እንደሌለህና በባዶ ቀረርቶ ልትደበቅ መሞከርህን ነው። እኔ ሁለቱም አይከብደኝም – እንዳየውህ ብዙም ነፍስ ያወቅክ ተከራካሪ አይደለህም ከዚህችው አቅምህ ጋር ሞራል ቶርች እያደረግኩ የእድሜ ልክ ጠባሳ ልጥልብህ አልፈልግም።
ወደ ቁርዓን ላነሳሀው ሙግት እራሱን በቻለ መልኩ እንመጣበታለን ካስፈለገህ በአዲስ ፖስት አድርገው እንጅ አይነሳ አላልኩም። ስለ ቁምራን እያወራን አስሬ የምታወራው ስለ ቁርዓን ከሆነ ግን ልልህ የምችለው ብቸኛ ነገር ወዳጄ ጨንቆሀልና ትንሽ አረፍ በል ነው።
ከላይ ባስቀመጥኩልህ መሰረት መሞገት ባለመቻልህ እንዲሁ ስትንፈራገጥና ስትዛለፍ ኮሜንትህን ጨርሰህዋል። ምን ይደረጋል አላዋቂነት ጌጥ ሲሆን እንደ ስብራት እንኳን በቫዝሊን አይታሽም። ቫርያንቱን በመጠኑ ከታች እያስቀመጥኩ ላንተ «ከባድ» ብለህ የቆለልከውን ነገር በመጠኑ እናየዋለን።
ከዛ በፊት ጥቂት መግቢያ ልስጥህ
1- የቁምራን ማኑስክሪፕትን አስመልክቶ ከመነሻው ከሙሴ ጊዜ ጋር 1000 ዓመት ገደማ የሚራራቅ እንደመሆኑ መጠን ለአስተማማኝነቱ ምንም ማረጋገጫ የለንም። ይህን ያልኩህ አኔ ሳልሆን የክርስቲያን ምሁራን ናቸው። ዶ/ር ፓውል ፒተርስ Variants of the Isaiah Scroll Adopted by the Revised Standard Version and the Jerusalem Bible በተሰኘው ለፓስቶራል ኮንፈረንስ ባዘጋጀው ጥናታዊ ጹሁፉ ላይ በኢንተርዳክሽኑ ላይ ጠቅሶታል። ተጨማሪ ሌሎችንም ልሰጥህ እችላለሁ።
2- ከላይ አንተ በጥቂቱ ብለህ ለማመን እንደሞከርከውም ማኑስክሪፕቱ ላይ የተለያዩ ስህተቶች ተገኝተዋል። የብሉይ ኪዳን ምሁራን ስህተቱ መፈጸሙ ላይ ክርክር የላቸውም። ዋናው ነጥብ ግን ስህተቱ ተራ የሚባል ስህተት ነው ወይንስ አይደለም የሚለው ነው። እሱን ከታች ማሳያ እያነሳሁ ለማብራራት እሞክራለሁ።
6 · Like · React · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
.
Like · React · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
የኢሜጅ ማስቀመጫ ቦክሱን ብትከፍተው ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት የተሻለ ነበር። ለማንኛውም ባልኩት መሰረት ጥቅል በሆነ መልኩ አንዳንድ ነጥቦችን ከታች ላብራራ። ሀሳቡን ለመመለስ እንዲቀልህ በነጥብ አደርግልሀለው።
1- ጥቅሉ አንተ እንዳልከው «ጥቂት» ስህተት ብቻ ሳይሆን አያሌ ስህተቶችና ልዩነቶችን በውስጡ ያቀፈ ነው። ከዋናው የማሶርቲክ ኮዴክስ ጋር እንኳን ወደ 2600 የሚጠጉ የቴክስት ልዪነቶችን ይዟል። በእየሩሳሌም የሚገኘው የእስራኤል ሙዝየም ይህንኑ አረጋግጧል።
2- በጣም ብዙ አነስተኛ የሚባሉ የቃላት ስህተቶች፣ ቃላትን የመዝለል፣ አናባቢዎችና የመተውና የመጨመር ስህተቶች እንደነበሩት ሁሉ ከበድ ያሉ ስህተቶችንም ማኑስክሪፕቱ አካቷል። ይህ የሚያሳየው ለአብነት የኢሳያስ መጽሀፍ ያሳለፈውን የብረዛ ሒደት ወይንም 1QIsaa የተሰኘው የማኑስክሪፕቱ ክፍል ስህተትን ነው። በሁለቱም መንገድ ቢሆን መጽሀፉ በእጃችን ካለው መጽሀፍ ጋር የቴክስት ልዩነት እንዳለው በቂ ማሳያ ነው።
3- ረዳት ፕሮፌሰር አንድሪው ፔሪን ስለ ጥንታዊ ማኑስክሪፕቶች በጻፈው አርቲክሉ ላይ ሲናገር እንዲህ ይላል if the Scrolls taught us anything about Old Testament scripture, it is generally true that the older the manuscripts the more varied they become. እነዚህ ጥቅሎች ያስተማሩን ነገር ቢኖር አዳዲስ ማኑስክሪፕቶች በተገኙ ቁጥር ከብሉይ ኪዳን ጋር ያላቸውን ልዩነት ነው። ከዛ በኋላ አርቲክሉ ላይ ተጨማሪ ሀሳቦችን ይዘረዝራል። እዚህ ጋ ላነሳልህ የፈለግኩት ዋና ነጥብ እነኝህ የጥንት ማኑስክሪፕቶች በውስጣቸው ያሉ ይዘቶች ብሉይ ኪዳንን ለያዘ ሰው የሚያኮሩ አይደሉም። የቁምራን ማኑስክሪፕትን ጨምሮ እያንዳንዳቸውን ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ማኑስክሪፕቶች ብንመለከት ሁለት እንኳን የሚመሳሰል አናገኝም። ኢንሳይክሎፒዲያ አሜሪካ ላይ ስለ ኮዴክስ በሚያነሳው ክፍሉ ይዳስሰዋል። የጆሆቫ ምስክሮች ባዘጋጁት Introduction To the holy bible መጽሀፍም ከላይ ያልኩትን ቃል በቃል ይናዘዛሉ።
4- መጽሀፍቶቹ ለአስርተ ዓመታት ከአማኙ እንዲደበቅ ተደርጎ ነበር። መጽሀፍቶች የክርስትናን መሰረት ያናጋሉ በሚል እስቅርብ ጊዜ ድረስ በሚስጥር ተይዘው እንዲቆዩ ተደርገዋል። ጥቅሎችን በማጥናት እውቅ የሆነው ጆሴፍ ፊዝማየር ስለ ጥቅሎቹ መደበቅ ሲናገር ጥቅሎቹ ከመጽሀፍቱ ጋር ያላቸውን ልዩነት እንደ ስህተት በመውሰድ የተደረገ እንደነበር ይናገራል። ታዲያ በአንድ ወቅት ቫቲካን ለእምነቱ ሰግታ ደብቃው በነረው መጽሀፍ ነው የምትኩራራው?
5- ጥቅሉ በሚያስገርም ሁኔታ የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ቁጥር 52 አንቀጽ ይዞ እናገኘዋለን። በተዓምር ከእየሱስ ጊዜ በፊት ተጽፏል ተብሎ የሚታመን መጽሀፍ ወንጌልን ሊያካትት አይችልም። ይህ ማኑስክሪፕቱ ላይ ከሚገኙ አያሌ እክሎች መካከል አንዱ ነው። እነዚህ እክሎች ደግሞ መጽሀፉ ተዓማኒ እንዳይሆን የሚያደርጉ አብነቶች ናቸው። ጹሁፉን ራሳችሁ ማየት ከፈለጋችሁ https://www.deadseascrolls.net.il/explore-the-archive/manuscript/7Q5-1
ስናጠቃልለው – ጥቅሉ በተለያዩ የሙግት ነጥቦች ሲዳሰስ ጭራሽ አንድ ክርስቲያን ሊኮራበት የማይችልና የተዓማኒነትን መስፈርት የማያሟላ ነው።
Edited · 1 · Like · React · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
እንዲህ ብለህ ጽፈሃል፡– ///ወደ ነጥቦችህ ከመግባቴ በፊት አንዳንድ ፈገግ ያደረጉኝን ነገሮች ልግለጽ። ሀሳብ ላይ ትኩረት አድርጌ እየጠየቅኩህ ቃላቶችህ ሁሉ ፐርሰናል ናቸው። ይህ ምን እንደሚጠቁም ታቃለህ? ለአርጊውመንቱ የተሻለ ሙግት እንደሌለህና በባዶ ቀረርቶ ልትደበቅ መሞከርህን ነው። እኔ ሁለቱም አይከብደኝም – እንዳየውህ ብዙም ነፍስ ያወቅክ ተከራካሪ አይደለህም ከዚህችው አቅምህ ጋር ሞራል ቶርች እያደረግኩ የእድሜ ልክ ጠባሳ ልጥልብህ አልፈልግም።///
ሰውየው እኔ ለብሽሽቅ እዚህ አልተቀመጥኩም፡፡ መጀመርያ በሰጠኸኝ ምላሽ ዘለህ ወደ ዘለፋ የገባኸው አንተ ነህ፡፡ ምን ብለህ እንደጻፍክ እስቲ መለስ ብለህ አንብብ? ///ጭራሽ አንተ አለመቻልህን ብቻ መግለጽ ሀፍረት ሁኖብህ ሁሉንም ሰው ባንተ ብልቃጥ ውስጥ አስገባሀው/// ነበር ያልከው፡፡ የኔ ምላሽ ተረጋጋ፣ ሁለታችንም ሊቃውንት አይደለንም፣ በአቅማችን ልክ ሊቃውንትን እየጠቀስን እንነጋገር የሚል ነበር፡፡ አይ እኔ ሊቅ ነኝ፣ በጉዳዩ ላይ የግል ጥናት አድረጌያለሁ፣ ማኑስክሪፕቶቹን በግሪክና በእብራይስጥ ማንበብ እችላለሁ የምትል ከሆነ ከእግርህ ስር ቁጭ ብለን እንማራለን፡፡ አንድ የግሪክና የእብራይስጥ ቃል ማንበብ በማትችልበት ሁኔታ ግን አጉል ራስን መወጠር ስለማይጠቅምህ ረጋ ብትልና ለመማር ዝግጁ እንደሆነ ሰው ብታወራ መልካም ነው፡፡ ለማንኛውም የማን ንግግር ግላዊ ስሜት የተቀላቀለበትና የህፃን እንደሆነ የሁለታችንንም ምልልስ በማንበብ ፍርድ የሚሰጡ ወገኖች ስላሉ ብዙም አያሳስብህ፡፡
እንዲህ ብለህ ጽፈሃል፡– ///ወደ ቁርዓን ላነሳሀው ሙግት እራሱን በቻለ መልኩ እንመጣበታለን ካስፈለገህ በአዲስ ፖስት አድርገው እንጅ አይነሳ አላልኩም። ስለ ቁምራን እያወራን አስሬ የምታወራው ስለ ቁርዓን ከሆነ ግን ልልህ የምችለው ብቸኛ ነገር ወዳጄ ጨንቆሀልና ትንሽ አረፍ በል ነው።///
ሙስሊም አፖሎጂስቶች ሁለት ሚዛን በመጠቀም የታወቃችሁ ስለሆናችሁ ከናንተ ጋር ስኬታማ ውይይት ለማድረግ ትክክለኛው መንገድ ቁርአንንም በስሌቱ ውስጥ እንድታስገቡ ማስገደድ ነው፡፡ እናንተ እኮ ኦሪጅናል የቁርአን ጽሑፍ በእጃችን አለ ብላችሁ ሕዝባችሁን የምትዋሹ ፈሪሃ እግዚአብሔር የራቃችሁ ሰዎች ናችሁ! ፍትሃዊ ከሆንክና ከዚህ አመል ነፃ ሆነህ ከተገኘህ ቁርአንን አልጠቅስም፡፡ የሊብራል ሊቃውንት ትችት በመዘብዘብ ጊዜዬን ለማቃጠል ከመጣህ ግን የማልጠቅስበት ምክንያት የለም፡፡
2 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
እንዲህ ብለህ ጽፈሃል፡– ///የቁምራን ማኑስክሪፕትን አስመልክቶ ከመነሻው ከሙሴ ጊዜ ጋር 1000 ዓመት ገደማ የሚራራቅ እንደመሆኑ መጠን ለአስተማማኝነቱ ምንም ማረጋገጫ የለንም። ይህን ያልኩህ አኔ ሳልሆን የክርስቲያን ምሁራን ናቸው። ዶ/ር ፓውል ፒተርስ Variants of the Isaiah Scroll Adopted by the Revised Standard Version and the Jerusalem Bible በተሰኘው ለፓስቶራል ኮንፈረንስ ባዘጋጀው ጥናታዊ ጹሁፉ ላይ በኢንተርዳክሽኑ ላይ ጠቅሶታል። ተጨማሪ ሌሎችንም ልሰጥህ እችላለሁ።///
ውይይቱን ከመጀመራችን በፊት ስለ ዘመን ልዩነት መወያየት ትፈልግ እንደሆን ስጠይቅህ “እርሱ ይቅር፣ ስለ ይዘት እንወያይ” ብለህ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ቃልህን አጥፈህ ስለ ዘመን ልዩነት ማውራት ጀመርክ፡፡ ረስተኸው ነው ወይንስ የሙግት ሐሳብ አጠረህ? ለማንኛውም የቁምራን ጽሑፎች የዘመን ክፍተት ከሙሴ ጀምሮ የሚታሰበው ለአምስቱ መጻሕፍት እንጂ ለተቀሩት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አይደለም፡፡ እያንዳንዱ መጽሐፍ በተለያየ ዘመን ስለተጻፈ የዘመኑ ቅርበትና ርቀት እንደየመጽሐፉ ይለያያል፡፡ ስለዚህ ሁሉንም በአንድ መውቀጫ ውስጥ መክተትህ ለጉዳዩ የጀማሪ ጥናት እንኳ አለማድረግህን ያሳብቃል፡፡
የዘመን ክፍተቱን ለማሳየት ደግሞ የምሑር ማጣቀሻ መስጠትህ አስቂኝ ነው፡፡ በሙሴና በቁምራን ጥቅልሎች መካከል ያለውን የዘመን ክፍተት ለማወቅ የምሑር ማጣቀሻ መስጠት አያስፈልግም፡፡ በጣም ኤሌመንተሪ ነው፡፡ ለምን ዓይነት ሙግት የምሑር ማጣቀሻ እንደሚያስፈልግ የምታውቅ አትመስልም፡፡
ደግሞ የጠቀስከውን ምንጭ እስኪ ተመልከት፡፡ አንድ ዶክተር በሆነ ኮንፈረስን ላይ ያቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ ነው፡፡ ቀደም ሲል ግን እኔ የጠቀስኩት መጽሐፍ ኢንተርኔት ላይ ተጠቅሶ ስላየኸው ያዙኝ ልቀቁኝ ስትል ነበር፡፡ በሕትመት ላይ የሚገኙ መጻሕፍትን ብቻ በመጥቀስ የምታምን ከሆነ ለምን የገዛ መስፈርትህን ጠብቀህ አትሄድም? ለምን ከኢንተርኔት ላይ የሌክቸር ኖቶችን ትለቃቅማለህ? በFrank Moore Cross and Shemaryahu Talmon ኤዲት ተደርጎ የተዘጋጀው Qumran and the History of the Biblical Text የሚለው መጽሐፍ በእጅህ እንደሚገኝ ስለነገርከን ሌሎች ተመሳሳይ መጻሕፍት ካሉህ ከእነርሱ ጠቅሰህ ብታስረዳን ጥሩ ነው፡፡
ለማንኛውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ሐዋርያቱ የቅዱሳት መጻሕፍትን ሐቀኝነት ስላረጋገጡልን እንደ ክርስቲያኖች ወሳኝ አድርገን የምንመለከተው ከእነርሱ ዘመን ጀምሮ እስከ እኛ ዘመን የሚገኘውን የቅዱሳት መጻሕፍት የአስተላለፍ ሒደት ነው፡፡ ከነቢያት ዘመን ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ዘመን ድረስ የሚገኘውን ክፍተት በክርስቶስና በሐዋርያቱ ምስክርነት ስለምንታመን አሳሳቢ አድርገን አናየውም፡፡ አንተም እንደ ሙስሊምነትህ ተውራት በመሐመድ ዘመን በትክክለኛ ይዘቱ እንደነበረ መሐመድ ስለመሰከረ የዘመን ክፍተቱ ሊያሳስብህ አይገባም፡፡
2 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
እንዲህ ብለህ ጽፈሃል፡– ///ከላይ አንተ በጥቂቱ ብለህ ለማመን እንደሞከርከውም ማኑስክሪፕቱ ላይ የተለያዩ ስህተቶች ተገኝተዋል። የብሉይ ኪዳን ምሁራን ስህተቱ መፈጸሙ ላይ ክርክር የላቸውም። ዋናው ነጥብ ግን ስህተቱ ተራ የሚባል ስህተት ነው ወይንስ አይደለም የሚለው ነው። እሱን ከታች ማሳያ እያነሳሁ ለማብራራት እሞክራለሁ።///
የኢሳይያስ መጽሐፍ 95% በላይ በእጃችን ከሚገኘው ጋር ፍፁም አንድ እንደሆነና የተቀሩት መልእክቱን ሊለውጡ የማይችሉ ቁርአንን ጨምሮ በማንኛውም መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙ ዓይነት ግድፈቶች እንደሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ለዚህም ቀደም ሲል ምሑራን ምንጭ ጠቅሼልሃለሁ፡፡ በተጨማሪም አንተ ቀደም ሲል የጠቀስከው መጽሐፍ ገፅ 116 ላይ ይህንኑ ያረጋግጣል፡፡ ከዚህ የተለየ መረጃ ካለህ ማስረጃህን አቅርብ፡፡
1 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
እንዲህ ብለህ ጽፈሃል፡– ///1- ጥቅሉ አንተ እንዳልከው «ጥቂት» ስህተት ብቻ ሳይሆን አያሌ ስህተቶችና ልዩነቶችን በውስጡ ያቀፈ ነው። ከዋናው የማሶርቲክ ኮዴክስ ጋር እንኳን ወደ 2600 የሚጠጉ የቴክስት ልዪነቶችን ይዟል። በእየሩሳሌም የሚገኘው የእስራኤል ሙዝየም ይህንኑ አረጋግጧል።///
የፊደል አጣጣልና ትርጉሙን የማይለውጡ ሌሎች ጉዳዮች ከስህተት ወይም ከልዩነት አይቆጠሩም፡፡ እብራይስጥ እንደማንኛውም የሴሜቲክ ቋንቋ ኢቮልቭ ስላደረገ ጥቃቅን ልዩነቶች መኖራቸው ግድ ነው፡፡ ይህ ቆጠራ ሁሉንም ያካተተ ነው ወይንስ የምንባቡን ትርጉም ሊለውጡ የሚችሉትን ብቻ? ደግሞ ምንጭ አልጠቀስክም፡፡ መረጃውን ከየት አመጣኸው?
እንዲህ ብለህ ጽፈሃል፡– ///2- በጣም ብዙ አነስተኛ የሚባሉ የቃላት ስህተቶች፣ ቃላትን የመዝለል፣ አናባቢዎችና የመተውና የመጨመር ስህተቶች እንደነበሩት ሁሉ ከበድ ያሉ ስህተቶችንም ማኑስክሪፕቱ አካቷል። ይህ የሚያሳየው ለአብነት የኢሳያስ መጽሀፍ ያሳለፈውን የብረዛ ሒደት ወይንም 1QIsaa የተሰኘው የማኑስክሪፕቱ ክፍል ስህተትን ነው። በሁለቱም መንገድ ቢሆን መጽሀፉ በእጃችን ካለው መጽሀፍ ጋር የቴክስት ልዩነት እንዳለው በቂ ማሳያ ነው።///
የሆነ ነገር እያነበብክ እየተረጎምክ ያለህ ነው የሚመስለው፡፡ የእንግሊዘኛ ጽሑፉን ብትለጥፍልን ይበልጥ ሐሳቡን እናገኛለን፡፡ ከበድ ያሉ ስህተቶች ያልከው ምን የሚል ነው? እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት እንደ ችግር የታየው ጥቂት ክፍሎቹ በዘመን ብዛት በመበላሸታቸው ምክንያት ምን እንደሚሉ አለመታወቁ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የማንም ስህተት አይደለም፡፡ ልዩነት ተብሎ የሚታሰብም አይደለም፡፡ አሁንም ምንጭ አልጠቀስክም፡፡
እንዲህ ብለህ ጽፈሃል፡– ////3- ረዳት ፕሮፌሰር አንድሪው ፔሪን ስለ ጥንታዊ ማኑስክሪፕቶች በጻፈው አርቲክሉ ላይ ሲናገር እንዲህ ይላል if the Scrolls taught us anything about Old Testament scripture, it is generally true that the older the manuscripts the more varied they become. እነዚህ ጥቅሎች ያስተማሩን ነገር ቢኖር አዳዲስ ማኑስክሪፕቶች በተገኙ ቁጥር ከብሉይ ኪዳን ጋር ያላቸውን ልዩነት ነው። ከዛ በኋላ አርቲክሉ ላይ ተጨማሪ ሀሳቦችን ይዘረዝራል። እዚህ ጋ ላነሳልህ የፈለግኩት ዋና ነጥብ እነኝህ የጥንት ማኑስክሪፕቶች በውስጣቸው ያሉ ይዘቶች ብሉይ ኪዳንን ለያዘ ሰው የሚያኮሩ አይደሉም። የቁምራን ማኑስክሪፕትን ጨምሮ እያንዳንዳቸውን ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ማኑስክሪፕቶች ብንመለከት ሁለት እንኳን የሚመሳሰል አናገኝም። ኢንሳይክሎፒዲያ አሜሪካ ላይ ስለ ኮዴክስ በሚያነሳው ክፍሉ ይዳስሰዋል። የጆሆቫ ምስክሮች ባዘጋጁት Introduction To the holy bible መጽሀፍም ከላይ ያልኩትን ቃል በቃል ይናዘዛሉ።////
ምንጭ! ምንጭ! ምንጭ! ያለ ማስረጃ ነው እያወራህ ያለኸው፡፡ ደግሞ የይሆዋ ምስክሮች ከመቼ ጀምሮ ነው የመጽሐፍ ቅዱስ የጥንት ጽሑፎች ሊቃውንት የሆኑት? ማን የሚባል የጥንታውያን መዛግብት ሊቅ አላቸው? የትኛውን ጥናት አድርጎ ምን የሚል መጽሐፍ ጻፈ? በማይረባ ነገር ጊዜያችንን እያቃጠልክ ነው፡፡
1 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
እንዲህ ብለህ ጽፈሃል፡– ///4- መጽሀፍቶቹ ለአስርተ ዓመታት ከአማኙ እንዲደበቅ ተደርጎ ነበር። መጽሀፍቶች የቅርስትናን መሰረት ያናጋሉ በሚል እስቅርብ ጊዜ ድረስ በሚስጥርተይዘው እንዲቆዩ ተደርገዋል። ጥቅሎችን በማጥናት እውቅ የሆነው ጆሴፍ ፊዝማየር ስለ ጥቅሎቹ መደበቅ ሲናገር ጥቅሎቹ ከመጽሀፍቱ ጋር ያላቸውን ልዩነት እንደ ስህተት በመውሰድ የተደረገ እንደነበር ይናገራል። ታዲያ በዚህ በአንድ ወቅት ቫቲካን ለእምነቱ ሰግታ ደብቃው በነረው መጽሀፍ ነው የምትኩራራው?///
ይህ ያንተና የመሰሎችህ ተራ ግምት ነው፡፡ ጥንታውያን መዛግብት በገንዛብ የማይተመን ዋጋ ያላቸው ውድ ቅርሶች ናቸው፡፡ ብዙዎቹ በከፍተኛ ጥንቃቄ ካልተያዙ በስተቀር የጸሐይ ብርሃን እንኳ ቢያገኛቸው በቅፅበት ወደ አመድነት ይቀየራሉ፡፡ ብዙ አሉባልታዎች ተሰራጭተው መጽሐፍትን እስከ መጻፍ የደረሱ ወገኖች ቢኖሩ እንኳ ቫቲካን ለጥናቱ የሚመጥኑ መሣርያዎችና ሊቃውንት እስኪገኙ ድረስ በጥንቃቄ ይዛለች፡፡ አሁን ደግሞ ማንኛውም ሰው ሊያገኛቸው በሚችል መንገድ ታትመው ይፋ ሆነዋል፡፡ ክርስትና ይበልጥ ጠንካራ ማስረጃ አገኘ እንጂ እንደ ምኞታችሁ አልተናጋም፡፡ በዚሁ እግረ መንገድህን የሰነዓ ቁርአን ማኑስክሪፕቶች ለምን እስከ ዛሬ በድብቅ እንደተያዙና አውሮፓውያን ሊቃውንት እንዳያጠኗቸው እንደተከለከሉ ልትነግረን ትችላለህ? ዝም ብለህ በመንደር ወሬ አታድክመን፡፡
እንዲህ ብለህ ጽፈሃል፡– ///5- ጥቅሉ በሚያስገርም ሁኔታ የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ቁጥር 52 አንቀጽ ይዞ እናገኘዋለን። በተዓምር ከእየሱስ ጊዜ በፊት ተጽፏል ተብሎ የሚታመን መጽሀፍ ወንጌልን ሊያካትት አይችልም። ይህ መጽሀፉ ላይ ከሚገኙ አያሌ እክሎች መካከል አንዱ ነው። እነዚህ እክሎች ደግሞ መጽሀፉ ተዓማኒ እንዳይሆን የሚያደርጉ አብነቶች ናቸው። ጹሁፉን ራሰችሁ ማየት ከፈለጋችሁ https://www. deadseascrolls.net.il/explor…/manuscript/7Q5-1///
አቤት አቤት አቤት! ምን ዓይነት አፋችንን የሚያስዘጋ ማስረጃ አመጣህ ባክህ! የመረጃ እጥረት እንዳለብህ ብቻ ነው ያረጋገጥክልን፡፡ የቁምራን ጥቅልሎች ዕድሜያቸው ከሁለተኛው ክፍለ ዘመን ቅድመ ክርስቶስ ጀምሮ እስከ ሰባ ዓመተ ምህረት መካከል መሆናቸው የተረጋገጡ ብዙ ጽሑፎችን ይዘዋል፡፡ የኢሳይያስ ጥቅልል ከክርስቶስ በ200 ዓመታት የሚቀድም ሲሆን ሌሎች ዕድሜያቸው እስከ 70 ዓ.ም. የተገመቱ አሉ እንደ ማርቆስ ወንጌል ቁርጥራጮች ዓይነት ክፍሎች አሉ፡፡ ይህ የሚያሳየው የማርቆስ ወንጌል ከኢየሩሳሌም መፍረስ በፊት እንደተጻፈ በማመላከት ለተዓማኒነቱ ማስረጃ ይሆናል እንጂ የሌሎች ቀዳሚያን ጽሑፎችን ተዓማኒነት አይቀንስም፡፡ መረጃዎችን የምትተረጉምበት መንገድ በጣም እያሳቀኝ ነው፡፡
እንዲህ ብለህ ጽፈሃል፡– ///ስናጠቃልለው – መጽሀፉ በተለያዩ የሙግት ነጥቦች ሲዳሰስ ጭራሽ አንድ ክርስቲያን ሊኮራበት የማይችልና የተዓማኒነትን መስፈርት የማያሟላ ነው።///
ስህተቶችህን አብዝተህ ራስህን ከምታስገመግም ትንሽ ጊዜ ወስደህ ርዕሱን አጥናና ተመለስ፡፡
1 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
ጨረስክ? 😀
1 · Haha · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
መልካም እንገዲህ – ከክርስቲያኖች ጋር ስወያይ ሁሌም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር የረባ ማብራሪያ ባለመስጠት ወይ ከእውቀታቸው አልያም ከጨዋነታቸው አለመጠቀሜ ነው። ያንተም ከዚህ የሚለይ አይደለም። ጠንከር ያለ አርጊውመንት ሲመጣብህ የምትለው ነገር እንዳያንስ ሙሉ ኮሜንት በብሽሽቅ ትጨርሰዋለህ። ብሽሽቅ ውስጥ እንዳልገባህ እራሱ ለማስረዳት አንድ ሌላ ሙሉ ኮሜንት ትጠቀማለህ 😀 የረባ አርጊውመንት እንደሌለው በሱ ጊዜኝ ማቃጠል አልፈልግምና ወደ ነጥቦችህ ልግባ
የመጀመሪያው ነገር የዘመናት ልዩነቱን አስመልክቶ ላነሳሁት አርጊውመንት ምላሽ ስትሰጥ እዛ ውስጥ መግባት እንደማትፈልግ ተናግረህ ስለነበር እንዴት ገባህ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አልክ። ወዳጄ መጀመሪያ ጥያቄ አቅርቤልህ የነበረችዋን ፖይንት ለመደባበስ ስትሞክርና በዚህኛው ለሰልማን ባነሳሁት ነጥብ ውስጥ ለመደበቅ ስትሞክር ጊዜ ወደ ዋና «ጣቢያ» መልሸህ ይህንን ትተህ ያኛውን እንድትመለስ ማነገሬ ነበር። ያለመታደል ሁኖ የመጀመሪያው ሀሳቤ ዙሪያ ብዙም መወያየት ስላልፈለግክ ሰፋ አድርገነው ቀጠልንበት። ያነሳሁት እራሱ ስለ ይዘቱ ሳወራ ሳይሆን ስለ ማኑስክሪፕቱ ለሌላው አንባቢ መግቢያ ስሰጥ ነው።
በጣም ያሳቀኝ ክፍል ደግሞ እንዴት ምንጭ አስቀመጥክ ብለህ ለመውቀስ ያደረግከው ሙከራ ነው 😀 ምናልባት ምንጭ ባላስቀምጥ ኖሮ ደግሞ ከታች እንደጠየቅከው ምናልባት ምንጭ አምጣ ብለህ ትከራከረኝ ይሆናል። ለማንኛውም ምንጩን ያስቀመጥኩት ስለብሉይ ኪዳንና አጻጻፉ በተለይ በሙሴ ጊዜ ተጽፈዋል ተብለው ስለሚታመኑት አምስቱ ፔንታተቾች የጊዜ ሁኔታ በቂ እውቀት ለሌለው አካል ሀሳቡ የኔ እንዳይመስለው በመረጃ ማስደገፌ ነው። እዚህ ጋር የተለያየ የእውቀት ደረጃ ያለው አንባቢ እንደሚከታተልህ መዘንጋትህም አስገራሚ ነው። በርግጥ ልክ ነህ ሌሎች ፖስቶችህንም ሳይ ጠንከር ያለ ሀሳብ ይዞ ሲደግፍህም ሲሟገትህም ያስተዋልኩት ክርስቲያን የለም።
ያመጣሁትን ምንጭ ደግሞ ለማጣጣል የሞከርክበት መንገድ ከቅንነትም ከእውቀትም ጋር ጠብ እንዳለህ የሚያሳይ ነው። አሁን በፈጠረህ የቲዮሎጂ ፕሮፌሰር የሆነ ሰው የቲዮሎጂ ምሁራን በተሰበሰቡበት መድረክ ያቀረበው ጥናታዊ ጹሁፍ መረጃ ካልሆነ ሌላ ምን መረጃ ሊሆን ይችላል? ሲደንቅ
2 · Like · React · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
1- አንደኛው ሀሳብ ላይ አቅርቤው ለነበረው ሙግት የሰጠኸው መከራከሪያ ያን ያህል የረባ አይደለም። እንዲሁ ካለወቅከው መረጃ ስጠኝ ብቻ ብለህ ብትጠይቅ ይቀል ነበር። ለውጦቹ ተራ ብቻ ናቸው ብየ ባስብማ ምን አደከመኝ ነበር? ለውጦቹ ከተራ ጀምሮ እስከ አንቀጽ የደረሱ እንደሆነ ነው እየገለጽኩ ያለሁት። መረጃ መጠየቅህ መልካም ነው። ይኸው http://dss.collections.imj.net.il/isaiah
2- ለሁለተኛው ሀሳብ ያቀረብከው መልስም ቢሆን ስለምንወይበት ጊዳይ በራሱ ገና ብዥታ ውስጥ እንዳለህ የሚያሳይ ነው። የሆነ ነገር እያነበብክ ነው ትለኛለህ እንዴ? ታዲያ የኔ በ«መንፈስ ቅዱስ» መሪነት ቃላት የሚያሰባጥር የመጽሀፍ ቅዱስ ጸሀፊ ነኝንዴ? ያገኘሁትንና ስማር ያነበብኩትን ነው የማካፍልህ። አንዳንዴ አርጊው የምታደርግባቸው መንገዶች በራሱ ያስቃሉ። ለዚህ መከራከሪያ ብለህ የጠፉ ክፍሎችን ማምጣትህ ደግሞ የበለጠ የሚገርም ነው። የጠፋ ክፍልማ አንዴ ጠፍቷልኮ ከምን ጋር አወዳድረህ ነው ተሳሳተ የምትለው? ልዩነት አለባቸው ብየ የጠቀስኩልህ ክፍሎች ያሉ እንጅ የሌሉና የጠፉ ጹሁፎች አይደሉም።
1 · Like · React · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
3- በዚህኛው ክፍል ያነሳሀው መከራከሪያም ተመሳሳይ ማስረጃ የተጠማ ነው። ጭራሽ የጆሆቫ ምስክሮችን ለማጣጣልቅ ሞክረሀል። አንድ ሰው ስለመጽሀፍ ቅዱስ ምሁር ነው ተብሎ ክሬዲት ሊሰጠው ዘንድ ያንተ ቡድን አባል መሆን አለበት ማለት ነው? ለማንኛውም የአንደኛውን ምንጩን ከታች አስቀምጥልሀለው The Gospels, their origin and their growth, Frederick Grant, pp 32 አይዞህ ይህ ሰው የኒዎርክ ቲዮሎጂስት ነው።
4- የጥቅሉ ሚስጥራዊ ሁኖ መቆየቱን ከጥንታዊ መዛግብት ጥበቃ ጋር ማገናኘትህ ራስክን ትዝብት ውስጥ የሚጥልና የሚያስቅ ነው። ጥንታዊ መዛግብትን ጥበቃቸው አስተማማኝ በሆኑ ቦታዎች ማስቀመጥ ሌላ ነገር ሲሆን ይዘታቸው እንዳይጠና በምሁራን መከልከል ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው። በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን ግድ ከብራና ጋር እንዲታገሉ ሳይሆን እነዚህ ጥቅሎች ስካን ማድረግና ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ማቀበል ይቻላል። ያ ግን አልሆነም –ጉዳዩም አንተ ካለከው የቅርስ ጥበቃ ጋር አይገናኝም።
Like · React · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
አስቸኳይ ስራ ገጥሞኛል ስመለስ የምቀጥል ይሆናል፤ በቀረቡ ሀሳቦች ዙሪያ የተሻለ መልስ በማምጣት ታግዘኛለህ ብየ አስባለሁ። የቅድሙ አዬነት የድካም መፍጨርጨር ከሆነ ጊዜ ባታባክን መልካም ነው
2 · Like · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
እስኪ መለስ ብለህ መጀመርያ የሰጠኸኝን ምላሽ ተመልከት፡፡ ራስህን አጉል ወጥረህ አላስፈላጊ ቃላትን መናገር የጀመርከው አንተ ነህ፡፡ ከዚያ በረድ እንድትል ስነግር እንደገና ደግመህ ወደ ብሽሽቅ ሄድክ፡፡ አሁንም ቢሆን በጨዋ መንገድ መናገር ስትችል የጀማሪ ተሟጋች እስታይል እየተከተልክ ያለኸው አንተ ነህ፡፡ የኔ ምላሽ ካበሸቀህ ጥፋቱ ያንተ እንጂ የኔ አይደለም፤ ስለዚህ ማለቃቀሱን አቁምና ዋናው ነጥብ ላይ አተኩር፡፡ ያው የለመደ አመል ስለማይተው አሁንም ደግመህ ብሽሽቁን እንደምትቀጥል ግልፅ ነው፡፡
///መጀመሪያ ጥያቄ አቅርቤልህ የነበረችዋን ፖይንት ለመደባበስ ስትሞክርና በዚህኛው ለሰልማን ባነሳሁት ነጥብ ውስጥ ለመደበቅ ስትሞክር ጊዜ ወደ ዋና «ጣቢያ» መልሸህ ይህንን ትተህ ያኛውን እንድትመለስ ማነገሬ ነበር። ///
ያንተ ትልቁ ችግር መጀመርያ የጻፍካቸውን ኮሜንቶች አለማስታወስህ ነው፡፡ አሁንም ተመልሰህ ኮሜንቶችህን አንብብ፡፡ ስለ ማኑስክሪፕቶቹ ድፍን ጥያቄ ጠየቅህ፤ ስለ ዘመን ልዩነት ኮሜንት አደረግህ፤ እኔ ደግሞ በምን ርዕስ ላይ ለመወያየት እንደምትፈልግ ጠየኩህ፤ ስለ ዘመን መወያየት እንደማትፈልግና ስለ ይዘት መወያየት እንደምትፈልግ ስትነግረኝ በዚያ ቀጠልኩ፡፡ አሁን ደግሞ ያንን ርዕስ ሳንጨርስ መጀመርያ “ይቅር” ወዳልከው ርዕስ ተመለስክ፡፡ ሰላም ነው ወዳጄ?
የጊዜ ልዩነቱን የጠቀስከው በአጠቃላይ በቁምራን ጥቅልሎችና በሙሴ መካከል ያለውን የዘመን ልዩነት በማመላከት እንጂ ለይተህ ስለ ፔንታቱክ ብቻ አልተናገርክም፡፡ ይሁን እንኳ ብንል እያወራን ያለነው ስለ ኢሳይያስ ጥቅልል ሆኖ ሳለ ስለ ቴንታቱክ ምን አስወራህ? ዕውቀት ለሌላቸው ወገኖች አስበህ ቢሆን ኖሮ ለይተህ ፔንታቱክን ትጠቅስ ነበር እንጂ በደፈናው ስለ ቁምራን ጥቅልሎች ባልተናገርክ ነበር፡፡ ምንጭ የጠቀስከውም ለጀማሪዎች አስበህ ሳይሆን አንተ ራስህ ጀማሪ ስለሆንክ ትልቅ ማስረጃ የሰጠህ መስሎህ ነው፡፡ ለምን እንወሻሻለን ጌታው? ለምንጭ ግድ ያለህ ሰው ብትሆን ኖሮ እዚህ ቦታ ለተናገርካቸው ትልልቅ ጉዳዮች የረባ ምንጭ በጠቀስክ ነበር፡፡
///ያመጣሁትን ምንጭ ደግሞ ለማጣጣል የሞከርክበት መንገድ ከቅንነትም ከእውቀትም ጋር ጠብ እንዳለህ የሚያሳይ ነው። አሁን በፈጠረህ የቲዮሎጂ ፕሮፌሰር የሆነ ሰው የቲዮሎጂ ምሁራን በተሰበሰቡበት መድረክ ያቀረበው ጥናታዊ ጹሁፍ መረጃ ካልሆነ ሌላ ምን መረጃ ሊሆን ይችላል? ሲደንቅ///
ከቀልብ ሆነህ እየተከታተልከኝ አይደለም ማለት ነው፡፡ አሁንም ደግመህ የመጀመርያውን ምላሽህን አንብብ፡፡ እኔ የጠቀስኩትን መጽሐፍ ኢንተርኔት ላይ ተጠቅሶ አይተኸው አይደል እንዴ ለምን ከኢንተርኔት ላይ ጠቀስክ ብለህ ስትበሳጭ የነበረው? በሕትመት ላይ የሚገኙ መጻሕፍትን ብቻ በመጥቀስ የምታምን ከሆነ ለምን የገዛ መስፈርትህን ጠብቀህ አትሄድም? ነው ጥያቄው፡፡ ስለዚህ በደቂቃ ውስጥ ቃላባይ ሆነህ ስለተገኘህ ቅንነትም ሆነ ዕውቀት የሌለህ አንተ ነህ፡፡ ደግሞ “እከሌ የተባለ ፕሮፌሰር እንትን ሀገር በሰጠው ትምሕርት መሠረት…” ብሎ ማለት ምን የሚሉት የምንጭ አጠቃቀስ ነው? ምንጭ ሲጠቀስ መጽሐፍ ከሆነ ገፅ ይጠቀሳል፤ ከኢንተርኔት ላይ ከተወሰደ ደግሞ አድራሻው ይጠቀሳል፡፡ ስለ ምንጭ አጠቃቀስ ትንሽ ራስህን አስተምር፡፡
1 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
///1- አንደኛው ሀሳብ ላይ አቅርቤው ለነበረው ሙግት የሰጠኸው መከራከሪያ ያን ያህል የረባ አይደለም። እንዲሁ ካለወቅከው መረጃ ስጠኝ ብቻ ብለህ ብትጠይቅ ይቀል ነበር። ለውጦቹ ተራ ብቻ ናቸው ብየ ባስብማ ምን አደከመኝ ነበር? ለውጦቹ ከተራ ጀምሮ እስከ አንቀጽ የደረሱ እንደሆነ ነው እየገለጽኩ ያለሁት። መረጃ መጠየቅህ መልካም ነው። ይኸው http://dss.collections.imj.net.il/isaiah///
አይ ያሕያ! ዝም ብሎ የሆነ ሊንክ ገጭ ማድረግ ማንን ያሳምናል? እስኪ ከባድ የተባለውን ክፍል አሳየንና በከባድነት ይፈረጅ እንደሆን እንይ?
አንተ ከሰጠኸው ሊንክ ውስጥ ስለ ልዩነት የሚያወራው እንዲህ የሚል ነው፡– The version of the text is generally in agreement with the Masoretic or traditional version codified in medieval codices, such as the Aleppo Codex, but it contains many variant readings, alternative spellings, scribal errors, and corrections.
የተባለው ሁሉ ተደማምሮ የመጽሐፉ 5% ነው፡፡ ይህ ደግሞ ባንተ ቁርአንም ውስጥ ሊገኝ የሚችል ነው፡፡ መሠረታዊ ልዩነት የሚያስከትልና የመጽሐፉን ተዓማኒነት የሚሸረሽር ምንም ነገር የለም እያልኩህ ነው፡፡ መሠረታዊ ምንባቡን ለውጦ የመጽሐፉን ተዓማኒነት ይለውጣል የምትለውን እስኪ አቅርብና እንይ፡፡
///የሆነ ነገር እያነበብክ ነው ትለኛለህ እንዴ? ታዲያ የኔ በ«መንፈስ ቅዱስ» መሪነት ቃላት የሚያሰባጥር የመጽሀፍ ቅዱስ ጸሀፊ ነኝንዴ? ያገኘሁትንና ስማር ያነበብኩትን ነው የማካፍልህ።///
ማንበብማ ሁላችንም አንብበን ነው የምንነጋገረው፡፡ አንተ ግን ቃል በቃል ከእንግሊዘኛ እየተረጎምክ እንደሆነ ስለሚያሳብቅ የትርጉም ምንጩን አሳየን እያልኩህ ነው፡፡ ሐሳቡ ያንተ ከሆነ ያንተ ነው፤ ነገር ግን ከሆነ ቦታ ቀድተህ ተርጉመህ እስካቀረብክ ድረስ ምንጭ የመጥቀስ ግዴታ አለብህ፡፡
1 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
የጆሆቫ ምስክሮችን በተመለከተ የጠቀስከው በደፈናው ነው፡፡ የቁምራን ጥቅልሎችን አጥንቶ ምሁራዊ መጽሐፍ የጻፈ የጆሆቫ ምስክር የለም፡፡ አለ የምትል ከሆነ ስሙ ማን ነው? የትኛውን ጽሑፍ አጥንቶ ምን የሚል መጽሐፍ ጻፈ? ትክክለኛ ምሑራዊ ጥናት ያደረገ ሰው ከሆነ የማልቀበልበት ምክንያት የለም፡፡ አንተ ግን ምንም በሌለበት ነው በደፈናው ዝም ብለህ “የጆሆቫ ምስክሮች እንዲህ ብለዋል” ያልከው፡፡ የ10ኛው ክፍለ ዘመን ሺኣዎች ከቁርአን 500 ያህል ጥቅሶች እንደተበረዙ ተናግረዋል፡፡ ይህን አባባል ዝም ብለህ ትቀበላለህ? እሺ The Gospels, their origin and their growth, Frederick Grant, pp 32 ብለህ የጠቀስከው መጽሐፍ ምን ይላል? ከመጽሐፉ የወሰድከው ሐሳብ ምን የሚል ነው? ያንተን ሙግት የሚደግፈውን ጥቅስ አሳየንና እናንብብ፡፡
ይኸኛው ምላሽህ ደግሞ አስቂኝ ነው፡– ///4- የጥቅሉ ሚስጥራዊ ሁኖ መቆየቱን ከጥንታዊ መዛግብት ጥበቃ ጋር ማገናኘትህ ራስክን ትዝብት ውስጥ የሚጥልና የሚያስቅ ነው። ጥንታዊ መዛግብትን ጥበቃቸው አስተማማኝ በሆኑ ቦታዎች ማስቀመጥ ሌላ ነገር ሲሆን ይዘታቸው እንዳይጠና በምሁራን መከልከል ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው። በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን ግድ ከብራና ጋር እንዲታገሉ ሳይሆን እነዚህ ጥቅሎች ስካን ማድረግና ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ማቀበል ይቻላል። ያ ግን አልሆነም –ጉዳዩም አንተ ካለከው የቅርስ ጥበቃ ጋር አይገናኝም።///
ሰውየው! የቁምራን ጽሑፎች አብዛኞቹ ክፍሎች ገና ከጅምሩ ሲታተሙና ለምሑራን ብቻ ሳይሆን ለሕዝብም ጭምር ይፋ ሲሆኑ ነበር፡፡ በተወሰኑ ምሑራን እጅ ብቻ ይገኙ የነበሩት ጥቂት ክፍሎችም ቢሆኑ ታትመው ለምሑር ይቅርና እንደኔና እንዳንተ ላሉት ተማሪዎችም ጭምር ይፋ ከሆኑ ብዙ ዘመናት አልፈዋል፡፡ ምንድነው የምትቀባጥረው? እርግጠኛ ነኝ በሰራኸው በዚህ ስህተት እየተጸጸትክ ነው LOL
Edited · 2 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
የሚገርመው እያንዳንዱን መልስ በሰጠኸኝ ቁጥር እየተወያየውህ ሳይሆን ገና ሀ ብለህ ማጥናት እየጀመርክ የምትመልስልኝ ነው የሚመስለኝ። ለምሰጥህ መከራከሪያ እራሱ በሰል ያለ የመልስ ምት ከመስጠት ይልቅ መልሰህ እኔኑ በመጠየቅ ስትደናበር ነው የማይህ። ምናልባት ከላይ እንደገለፅኩልህ ፎሎወሮችህ መረጃ ላይ እምብዛም በመሆናቸው ምክንያት ለነሱ ስል እስከመጨረሻው እቀጥላለሁ እንጅ አንተ እንኳን ዝምብለህ ነው። ለማንኛውም የቀሩ ሀሳቦችን ከታች እዳስሳለሁ።
2 · Haha · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
ከላይ “ለምን ስለዘመናት ርዝማኔ ጠየቅከኝ?” ብለህ አስሬ የምታለቃቅስበትን ጉዳይ ምክንያቱን ከላይ ተናግሬያለሁ፤ የትኛውም ውይይታችን የተከታተለ ሰው ኮሜንቱን ካልሰረዝከው በስተቀር ከፍ ብሎ ሊያየው የሚችለው ነገር ነው። አስሬ በማስረዳት ልንደክምበት የሚገባ ጉዳይ አይደለም።
ስለሙሴ አውርተህ ስለፔንታተች አላወራህም እያልክ የምትከራከርበት መንገድ በጣም ያስቃል። ሙሴን ካነሳሁ የማወራው ስለ ኦሪት እንጅ ስለ ኢሳያስ ትንቢት አይደለም። ጭራሽ ይህንን ስላላወቅከው ነው ሳትገልፅ ያለፍከው ስትል እንዲህ ስቄብህ 🤣 ከማለፍ ውጭ ሌላ ምንም አልልህም። ሲቀጥል ቀጥየ የጠቀስኩልህን መረጃ ኢንተርኔት ላይ ነው ብለህ አሁንም በሳቅ አድክመህኛል። ጥናቱ በሶፍትኮፒ እጄ ላይ አለ፤ የኢሜጅ ገፁን ክፈተው ያልኩህ መሠል ስራዎችን በስክሪን ሹትም እንዳስቀምጥ ነበር። በተረፈ ከላይ ያመጣውልህ መረጃ ግለሰቡ በመግቢያው/Introduction/ ላይ የጠቀሰው እኖደሆነ አስቀምጫለሁ፤ ከዚህ የበለጠ ካስፈለገህ መፅሀፉን አጋራህና ማንበብ ትችላለህ። የማልቀሻ መንገድ ካልፈለግክ በስተቀር ይህ የሚነሳ ጉዳይም አልነበረም።
1 · Like · React · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
ቀጥሎ በአንደኛው ነጥቤ ዙሪያ ያቀረብኩትን ምንጭ ገብተህ “የት ላይ ነው እንደዛ የሚለው?” ብለህ ታደክመኛለህ። መጀመሪያውኑ መረጃ ስትጠይቅ አንብበህ የምትረዳ አዬነት ሰው መሆን አለብህ። ካልሆነ ለቃላት ማሳመሪያና ራስን ለመስቀል ከሆነ መረጃ የምትጠይቀው እንዲህ በሚሰጥህ ሰአት ታፍራለህ። ያልኩህ ቃል በድህረ ገፁ ውስጥ ይገኛል ወይንስ አይገኝም? 🙂
Like · React · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
የጆሆቫ ምስክሮችን አስመልክቶ የፃፍኩት ልክ ነው በጥቅሉ ማኑስክሪፕቶችን አስመልክቶ ያላቸውን አመልካከት ነው የገለፅኩት። ስለቁምራን አወራ ያልኩህ ግለሰብም ሆነ ድርሳን አልነበረም። ያንተ ዋነኛ ችግር የምትረዳው አዳምጠህ ሳይሆን ገና ለገና “ይህንን ይለኛል” በሚል ደመነፍስ ብቻ ነው። ከዛ ስለጆሆቫዎችና ቁምራን በመጠየቅ መከራህን ትበላለህ። እየተደማመጥን ወዳጄ
1 · Like · React · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
በመጨረሻ በጣም የገረመኝ ንግግርህ መፅሀፉ ወዲያው ነው ለህዝብ ይፋ የተደረገው ያልክበት መንገድ ነው። መፅሀፉ በጥቂት ሰዎች እጅ ላይ ተገድቦ ለአካዳሚክ ሰዎች ባለመለቀቁ ምክነያት ከፍተኛ ውዝግብን ፈጥሮ ነበር። መፅሀፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሞ ለህዝብ ይፋ የሆነው በ1991 እኔደ አውሮፓ አቆጣጠር ነው። ይህንን እንኳን ሳታውቅ ነው ያዙኝ ልቀቁኝ የምትለው። ለዚህም ደግሞ መረጃ ልትጠይቀኝ ባልሆነ 🤔 አይገርመኝም
1 · Like · React · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
ስለ ዘመን መነጋገር ትፈልግ እንደሆን ስጠይቅህ እምቢ ብለህ በአንድ ርዕስ ላይ ከተስማማን በኋላ ሙግት ሲያጥርህ ጣልቃ ያስገባኸው አንተ ነህ፡፡ ቅጥፈትህን ለማጋለጥ ማስረጃ ይኸው፡–
Yahya Ibnu Nuhe ለእስልምና መልስ ሌላውን ላቆይልህና ስለ ቁምራን እናውራ፤ እስኪ ዲቴል ይዘቱ የት እንዳለና ይፋ ስለመሆኑ ንገረኝ
1
Delete or hide this
Like
· Reply · Message · 21h
Yahya Ibnu Nuhe ሰል ማን የቁምራን ማኑስክሪፕት እራሱኮ ከሙሴ ዘመን ጋር ያለው ልዩነት ወደ አንድ ሺህ አመት ይጠጋል Regardless of its Content.
3
Delete or hide this
Like
· Reply · Message · 21h
ሰል ማን ከYahya Ibnu Nuhe ጋር ቀጥሉ። ኢንሻአላህ ከእኔ ጋር እጠራሃለሁ በዚሁ ርዕስ።
Delete or hide this
Like
· Reply · Message · 21h
ለእስልምና መልስ ስለ ዘመኑ ልዩነት ነው መነጋገር የምትፈልገው? ከተስማማህ በዚያ እንሂድ፡፡
1
Edit or delete this
Like
· Reply ·
Yahya Ibnu Nuhe ለእስልምና መልስ እሱን ለሰልማን ነው ያነሳሁለት ከላይ አንተን የጠየቅኩህ ስለይዘቱ ነው። ጊዜ ያለመኖር እንጅ ሁሉንም ባየው እኔም ደስ ይለኛል። እስኪ ያለችንን ሰአት የተሻለ ክፍል ላይ በመወያየት ላይ እናሳልፋትና በይዘቱ ላይ እናውራ
Delete or hide this
Like
· Reply · Message · 21h
/////
አሁንም ደግመህ ወሽ አሉህ!
1 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
በሙሴና በቁምራን ጥቅልሎች መካከል ስላለው የዘመን ልዩነት ጠቅሰህ አሳሳች ምልከታ የሰጠኸው አንተ ነህ፡፡ የዘመን ልዩነቱ መሰላት ያለበት ከሙሴ ዘመን ሳይሆን ከእያንዳንዱ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ዘመን ነው፡፡ በራስህ አስተያየት ግራ ከተጋባህ የሰጠሁህን ምላሽ ደግመህ አንብበው፡– የጊዜ ልዩነቱን የጠቀስከው በአጠቃላይ በቁምራን ጥቅልሎችና በሙሴ መካከል ያለውን የዘመን ልዩነት በማመላከት እንጂ ለይተህ ስለ ፔንታቱክ ብቻ አልተናገርክም፡፡ ይሁን እንኳ ብንል እያወራን ያለነው ስለ ኢሳይያስ ጥቅልል ሆኖ ሳለ ስለ ቴንታቱክ ምን አስወራህ? ዕውቀት ለሌላቸው ወገኖች አስበህ ቢሆን ኖሮ ለይተህ ፔንታቱክን ትጠቅስ ነበር እንጂ በደፈናው ስለ ቁምራን ጥቅልሎች ባልተናገርክ ነበር፡፡
ይህንን ያልኩበት ምክንያት ምንጭ መጥቀስ ለማያስፈልገው ተራ መረጃ ምንጭ በመጥቀስህ ምክንያት ላቀረብኩት ትችት “ዕውቀት ለሌላቸው ወገኖች አስቤ ነው” የሚል ሰበብ ስለሰጠህ ነው፡፡ ዕውቀት ለሌላቸው ሰዎች የምታስብ ከሆነ ስለ ዘመን ልዩነት ስታነሳ ስሌቱ ፔንታቱክን ብቻ እንደሚያመለክት ለምን አልገለፅክም? ነው ጥያቄው፡፡ አታጭበርብር!
የፈረንጁን ጥናት ሶፍት ኮፒ ከኢንተርኔት ላይ ካላወረድክ መጀመርያ ከየት አገኘኸው? ከነጃሺ ቤተመጻሕፍት ነው የገዛሁት እንዳትለኝ ብቻ! ሙሉ የጽሑፉን ርዕስ ስጠኝና እኔ ደግሞ የኢንተርኔ ሊንኩን እሰጥሃለሁ፡፡
ሲጀመር የጠቀስኩልህን መጽሐፍ ኢንተርኔት ላይ ተጠቅሶ በማየትህ ማለቃቀስ የጀመርከው አንተ ነህ፡፡ አስተያየትህ ምን ያህል ደካማ እንደሆነ እንድትረዳ በሚል ነው ይህንን ጉዳይ ያነሳሁት እንጂ የኢንተርኔት ላይ ጽሑፎች ከተዓማኒ ድረገፅ እስከተገኙ ድረስ መጥቀስ ምንም ችግር የለውም፡፡ ይህንን ደግሞ በመጀመርያው ምላሼ ነግሬሃለሁ፡፡ የተጻጻፍነው እያስታወስክ፡፡
Edited · 1 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
እስከ አሁን ድረስ ስለ ልዩነት ያወራኸው በሙሉ በማስረጃ የተደገፈ አይለም፡፡ አጭርና ቀላል ጥያቄ ነው የጠየኩህ፡፡ የኢሳይያስ ጥቅልል አሁን በእጃችን ከሚገኘው የኢሳይያስ መጽሐፍ መሠረታዊ በሆነ መንገድ ልዩነትን ያሳያል ብለሀል፡፡ እስኪ ይህንን ትልቅና አስደንጋጭ ልዩነት ጥቀስልን ነው ያልኩህ፡፡ “አለ አለ አለ” እያልክ አታደንቁረን፡፡
በነገራችን ላይ የጅሆቫ ምስክሮች እንዲህ ይላሉ ብለህ ተናገርክ እንጂ ምንጭ በትክክል አላስቀመጥክም፡፡ Introduction To the holy bible የሚል መጽሐፍ በስንት አመተምሕረት ነው የተጻፈው? ገፅ ስንት ላይ ነው የጠቀስከው ሐሳብ የሚገኘው? ለመሆኑ እንዲህ የሚልስ መጽሐፍ አለ?
የመጽሐፍ ቅዱስን ጥንታውያን ጽሑፎች ያጠና ምሑር በጅሆቫ ምስክሮች ማሕበር ውስጥ መኖሩን ካላወክ አመለካከታቸውን የሙግትህ ግብዓት አድርገህ የተጠቀምከው ከምን በመነሳት ነው?
Edited · 2 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
ይኸኛው አስተያየትህ ደግሞ አጭበርባሪነትህን ይፋ የሚያወጣ ነው፡–
///በመጨረሻ በጣም የገረመኝ ንግግርህ መፅሀፉ ወዲያው ነው ለህዝብ ይፋ የተደረገው ያልክበት መንገድ ነው። መፅሀፉ በጥቂት ሰዎች እጅ ላይ ተገድቦ ለአካዳሚክ ሰዎች ባለመለቀቁ ምክነያት ከፍተኛ ውዝግብን ፈጥሮ ነበር። መፅሀፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሞ ለህዝብ ይፋ የሆነው በ1991 እኔደ አውሮፓ አቆጣጠር ነው። ይህንን እንኳን ሳታውቅ ነው ያዙኝ ልቀቁኝ የምትለው። ለዚህም ደግሞ መረጃ ልትጠይቀኝ ባልሆነ 🤔 አይገርመኝም///
እስኪ ይህንን አስተያየትህን ቀደም ሲል ከጻፍከው ጋር እናስተያይ፡–
///4- የጥቅሉ ሚስጥራዊ ሁኖ መቆየቱን ከጥንታዊ መዛግብት ጥበቃ ጋር ማገናኘትህ ራስክን ትዝብት ውስጥ የሚጥልና የሚያስቅ ነው። ጥንታዊ መዛግብትን ጥበቃቸው አስተማማኝ በሆኑ ቦታዎች ማስቀመጥ ሌላ ነገር ሲሆን ይዘታቸው እንዳይጠና በምሁራን መከልከል ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው። በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን ግድ ከብራና ጋር እንዲታገሉ ሳይሆን እነዚህ ጥቅሎች ስካን ማድረግና ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ማቀበል ይቻላል። ያ ግን አልሆነም –ጉዳዩም አንተ ካለከው የቅርስ ጥበቃ ጋር አይገናኝም።///
“ያ ግን አልሆነም?” ሆኗል እንጂ! ለዚያውም ምናልባትም አንተ ከመወለድህ በፊት! አይ ያህያ! በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ማለት ይሄ ነው፡፡ መጀመርያ መጽሐፉ እስከ ዛሬ ድረስ ለሕዝብ ይፋ አልሆነም ብለህ ካለቃቀስክ በኋላ ኢንተርኔት ላይ ስትፈልግ በ1991 ዓ.ም. እንደተለቀቀ መረጃ አገኘህ፡፡ እጥፍ አልክና ቅጥፈትህን ያጋለጥኩትን እኔኑ መረጃ የሌለው ሰው አስመስለህ በአግራሞት ራስህን ነቀነክ፡፡ እስኪ ትንሽ እፈር?
Edited · 2 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
በዚህ አስተያየት ውስጥ ሌላ ቅጥፈት ላሳይህ፡–
///በመጨረሻ በጣም የገረመኝ ንግግርህ መፅሀፉ ወዲያው ነው ለህዝብ ይፋ የተደረገው ያልክበት መንገድ ነው። መፅሀፉ በጥቂት ሰዎች እጅ ላይ ተገድቦ ለአካዳሚክ ሰዎች ባለመለቀቁ ምክነያት ከፍተኛ ውዝግብን ፈጥሮ ነበር። መፅሀፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሞ ለህዝብ ይፋ የሆነው በ1991 እኔደ አውሮፓ አቆጣጠር ነው። ይህንን እንኳን ሳታውቅ ነው ያዙኝ ልቀቁኝ የምትለው። ለዚህም ደግሞ መረጃ ልትጠይቀኝ ባልሆነ 🤔 አይገርመኝም///
ሲጀመር አንድ መጽሐፍ ብቻ ሳይሆን ብዙ ናቸው፡፡ የዋሻ 1 ግኝቶች በሙሉ በ1950 እና 56 መካከል ነበር የታተሙት፡፡ የ 8 የተለያዩ ዋሻዎች ግኝቶች ደግሞ በ1963 ነበር የታተሙት፡፡ የዋሻ ቁጥር 11 ግኝቶች ደግሞ በ1965 ነበር የታተሙት፡፡ ሳይታተሙ እስከ 1991 የቆዩት ጥቂት ቁርጥራጭ ጽሑፎች ብቻ ናቸው፡፡
ይህቺኛዋ ፓርት በጣም አስቂኝ ስለሆነች በኤዲት ልድገማት
መፅሀፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሞ ለህዝብ ይፋ የሆነው በ1991 እኔደ አውሮፓ አቆጣጠር ነው።
መፅሀፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሞ ለህዝብ ይፋ የሆነው በ1991 እኔደ አውሮፓ አቆጣጠር ነው።
መፅሀፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሞ ለህዝብ ይፋ የሆነው በ1991 እኔደ አውሮፓ አቆጣጠር ነው።
ለመጀመሪያ ጊዜ! ለመጀመሪያ ጊዜ! ለመጀመሪያ ጊዜ! ለመጀመሪያ ጊዜ! ለመጀመሪያ ጊዜ! ለመጀመሪያ ጊዜ!
መፅሀፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሞ ለህዝብ ይፋ የሆነው በ1991 እኔደ አውሮፓ አቆጣጠር ነው!!!!!!!
ቅጥፈት 😅🤣
Edited · 1 · Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
???
Like · React · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
Yahya Ibnu Nuhe is just an ignorant guy who picks fast information from the slump of the internet. He is so desperate to save face in the eyes of his Muslim audiences. All his ignorant deceptions are being exposed on this thread.
Like · React · Reply · Edit · Dec 5, 2018
መልስ ሰጠሀል እንዴ? እስኪ ደግሞ ልይህ። የመጨረሻ አስተያየትህን ብቻ አይቸ እየሳቅኩ ነበር 🤣 ብቻህን ሰው እየቆረጠምክ የሀሜት ከበሮህን ትደልቃለህ እንዴ? ሚስኪን “አፖሎጂስት” 🙂
1 · Haha · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
የሚገርመው ከላይ ጀምሮ ያቀረብከውን ሀሳብ በጠቅላላ አየሁት። እንዲሁ በራስህ ፖስት ላይ ኮሜንት ማቋረጥ መሸነፍ መስሎህ እንደምንም ትፍጨረጨራለህ አንጅ ምንም የረባ አዲስ ነገር አላመጣህም። አንዳንዶቹን ትርኪምርኪ ባዶ ችክቸካዎችን እራሱ በጣም ስለደከመኝ ለህሊናህና ለአዋቂ ፍርደኞች ትቸልህ አልፋቸዋለሁ እንጅ ብዳስሳቸውም አይጠቅሙም። ኮንሴፕት ላይ ፎከስ ያደረግክባቸው ቦታዎች ጥቂት ናቸውና እሱን መርጨ ትንሽ ነገር ልበልህ። ሌላው የባልቴት ወሬ የመሰለ አሰልቺ «አሉባልታ» ነው።
በመጨረሻ ያቀረብኩት ሀሳብ ላይ ምንም የተለየ ማስተባበያ ሳትሰጥ የላግጣ ኮሜንት ስትሰጥበት የነበረው ምክንያት ያስቃልም ያስገርማልም። እኔ ስላልታተመውና ውዝግብ ፈጥሮ ስለነበረው ክፍል እያወራውህ አንተ ስለታተሙት ታወራኛለህ። ይሄ ማለት «አበበ ለምን ምሳ አልበላም?» ተብሎ እየተጠየቀ «አበበ ባይበላም ከበደ ግን ምሳ በልቷል» ብሎ እንደመመለስ ነው። ዳሩ ምን ዋጋ አለው እነኝህን መሰል ውይይቶችን ለማካሄድ የውይይት አካሄድን ከማወቅ በዘለለ የተወያይን ሀሳብ መረዳትም ይጠይቃል። አንተ ደግሞ በተቃራኒው ነህ። ተወዛግቦ እንደሚያነብ ሰው ተወዛግበህ ትረዳውና የተወዛገበ መልስ ትሰጣለህ ሲያሻህም እንደ ጆሆቫው ጉዳይ ተወዛግበህ ያልተባለ እያነሳህ መልሰህ እኔኑ ትጠይቃለህ። እና ወዳጄ ከዚህ በላይ በዚህ ርዕስ ዙሪያ ካንተ ጋር ጊዜ ማቃጠል የሚኖርብኝ ይመስልሀል?
3 · Haha · Reply · Delete · More · Dec 5, 2018
You are finished Yahya. መቸስ ምላስህን አትውጠው፡፡ እስኪ ትንሽ ተንፈራገጥ ☺️
1 · Like · React · Delete · More · Dec 5, 2018
ፀረ ቦርጭ ነኝ ድንቅ ውይይት!
በተለይ ቁርአን ውስጥ እዲገባ ቢፈቀድ ብዙ መፈራገጦች እደምንታዘብ ውይይቱ በቂ ማሳያ ነው። እናመሰግናለን ለእስልምና መልስ እና ኡስታዝ yahya
3 · Likes · React · Delete · More · Dec 5, 2018
እንግዲህ ከዚህ ውይይት እንደምንታዘበው ኡስታዙ በርዕሱ ዙርያ ጥልቅ ጥናት ያደረገ በመምሰል ቢቀርብም ስለ ጉዳዩ ቅድመ ዕውቀት ስላልነበረው መረጃዎችን ገና ኢንተርኔት ላይ እያሰሰ እየተረጎመ ያቀርብ ነበር፡፡ ምንጮቹንም ስንመለከት የተሳከሩና አንዳንዶቹም በህትመት ላይ እንኳ የሌሉ ናቸው፡፡ ይህንን በተመለከተ ከውይይቱ በኋላ በወቅቱ ወንድም ዳንኤል የጻፈውን እናስነብባችኋለን፡-
ለእስልምና መልስ ewnetlehulu.net
Yahya Ibnu Nuhe ከተሰኘ ሙስሊም ሰባኪ ጋር ባለፉት ሁለት ቀናት ባደረግነው ውይይት ምንጮችን ባልተሟላ መንገድ ሲጠቅስ ነበር፡፡ ይባስ ብሎ የመጽሐፍ ቅዱስን የቁምራን የእጅ ጽሑፎች በተመለከተ በሊቃውንት ዘንድ ምንም ዓይነት ቦታ የሌላቸውን የይሖዋ ምስክሮችን መጽሐፍ እንደ ማስረጃ ሲጠቅስ ነበር፡፡ የጠቀሰልኝ መጽሐፍ ደግሞ Introduction To the holy bible እንደሚልና አቋሙን እንደሚደግፍለት በድፍረት ሲናገር ነበር፡፡ ከይሖዋ ምስክሮች መካከል በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት ያደረገ አንድ ሊቅ ሊጠቅስልኝ ይችል እንደሆን ስጠይቀው ምንም ምላሽ ሊሰጠኝ አልቻለም፡፡ የከፋው ስህተት እርሱ አይደለም፡፡ Introduction To the holy bible የሚል መጽሐፍ በይሖዋ ምስክሮች ማሕበር በስንት ዓመተ ምህረት እንደተጻፈ፣ እርሱ የጠቀሰው ሐሳብ በመጽሐፉ ገፅ ስንት ላይ እንደሚገኝና እንዲህ የሚል ርዕስ ያለው መጽሐፍ በይሖዋ ምስክሮች ታሪክ ታትሞ ያውቅ እንደሆን ስጠይቀው ምንም ዓይነት ማስረጃ ሊሰጠኝ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ሲጀመር ይህ ሁሉ ነገር የግል ፈጠራው እንጂ መሬት ላይ ያለ እውነታ አይደለምና፡፡ እንዲህ የሚል ርዕስ ያለው መጽሐፍ በይሖዋ ምስክሮች አልታተመም፡፡ ይህንን በእርግጠኝነት መናገር የምንችልበት አንዱ መንገድ እነዚህ ወገኖች “Holy Scriptures” ወይንም “Bible” ብቻ ሲሉ እንጂ “Holy Bible” ሲሉ እምብዛም አለመታየታቸው ነው፡፡
ከዚህ ምን እንማራለን? ሙስሊም ሰባኪያን ብዙ ጊዜ የተጭበረበሩ ምንጮችን የመጥቀስ አባዜ በእጅጉ የተጠናወታቸው ናቸው፡፡ የሊቃውንት መጻሕፍትን ሐሳባቸውን እንዲደግፉላቸው ቆራርጠው ከመጥቀስም አልፈው ሐሳባቸውን የሚደግፍ የመሰላቸውን ማንኛውንም ነገር ከቆሻሻ ገንዳዎች ሳይቀር ከማንሳት አይቆጠቡም፡፡ የድፍረታቸው ጥግም ያልተጻፉ መጻሕፍትን በምናባቸው ፈጥረው እስከ መጥቀስ የተለጠጠ ነው፡፡ (አሕመድ ዲዳትም “ሃምሳ ሺህ ስህተቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ” የሚለውን መዝሙር የጻፈላቸው በዚሁ መንገድ ነበር http://www.ewnetlehulu.net/am/our-answers/errors/ ) የሚጠ83ሷቸውን ምንጮች አይታችሁ ካላረጋገጣችሁ በስተቀር በፍፁም ልታምኗቸው አትችሉም፡፡ ይህንን ሁሉ የሚያደርጉት ደግሞ በእስልምና ካፊር የሆነን ሰው መዋሸት የተፈቀደ በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ሲዋሹ ትንሽ እንኳ ህሊናቸውን አይጎረብጣቸውም፡፡
