በእስልምና ውሸት ሃይማኖትን እስከ መካድ
በዓለም ላይ ከሚገኙት ታላላቅ ሃይማኖታት መካከል እስልምና ውሸትን የሚፈቅድ ብቸኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእስልምና ውስጥ ብዙ የተፈቀዱ የውሸት ዓይነቶች አሉ፡፡ የሱኒ ሙስሊሞች “ሙደራት” የተሰኘ የአታላይነት አስተምህሮ አላቸው፡፡ በሺኣ ሙስሊሞች ዘንድ ደግሞ “ታቂያ” በመባል ይታወቃል፡፡ ከዑላማ (የእስልምና ሊቃውንት) ክበብ ውጪ የሚገኙ ብዙ ሰዎች ስለዚህ አስተምህሮ ብዙም አያውቁም፡፡ “ሙደራት” ማለት ማደናነቅ፣ የግብዝነት አድናቆት፣ ማታለል፣ ቆዳን ማስወደድ፣ ማጭበርበር፣ እኩል መራመድ፣ መሸፈን፣ መደበቅ ወይንም መሰወር ማለት ነው፡፡ ይህ የማታለል ጠባይ አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ሰዓት ሁሉ በማንም ላይ ተግባራዊ ሊደረግ ይችላል፡፡ ነገር ግን የሱኒ ምሑራን በቋሚነት የሙደራት ዒላማ ውስጥ መግባት አለባቸው ያሏቸውን አሥር ዓይነት ሰዎች ለይተው አስቀምጠዋል፡፡ ካፊር (ሙስሊም ያልሆነ ሰው)፣ “ክፉ” የሆነ መሪ፣ አዲስ የሰለሙ ሰዎች፣ ከእስልምና ልቡ ያፈነገጠውን ሰው ወደ እስልምና ለመመለስ፣ አማኞች ያልሆኑትን በመምሰል የሳተን ሙስሊም ለመመለስ፣ የተማረን ሰው ወይንም ሳይንቲስት ከዕውቀቱ ለመጠቀም፣ ጓደኛን ለማስደሰት፣ ከጠላት ለማምለጥ ወይም ለመጉዳት፣ የትዳር አጋርን ለማስደሰት፣ የታመመ ሰው (ለምሳሌ ያህል ደህና እንደሚሆን ወይንም ደህና መምሰሉን በመንገር)፡፡ የሱኒ ሊቃወንት ይህንን አመለካከት ለማፅደቅ የተለያዩ የቁርአን ጥቅሶችን ይጠቅሳሉ፡፡ (Sam Solomon & E. Al-Maqdisi. Al-Hijra, Islamic Migration: Accepting Freedom or Imposing Islam?; 2009, pp. 72-79) ሙሐመድ አንድ ሙስሊም በአደጋ ውስጥ በሚሆንበት ሰዓት ሃይማኖቱን እስከ መካድ የሚደርስ ውሸትን መዋሸት እንደሚችል በማስተማር ሙስሊም መሆንን ርካሽ አድርጎታል (16፡106)፡፡ ነገር ግን እውነተኛ አማኞች የሆኑት ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብድናጎ አምላካቸውን ክደው ለጣዖት እንዲሰግዱ በንጉሥ ናቡከደነፆር በታዘዙ ጊዜ እንዲህ የሚል ምላሽ በመስጠት እሳት ውስጥ መጣልን መርጠዋል፡-
“ናቡከደነፆርም፦ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ፥ አምላኬን አለማምለካችሁ፥ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን? ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡንም፦ ናቡከደነፆር ሆይ፥ በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም። የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፥ ንጉሥ ሆይ! ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ አሉት።” (ዳንኤል 3፡16-18)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃልም ሆነ በተግባር በእምነት ፀንቶ ስለመገኘት እንዲህ ብሏል፡-
“ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ። ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል። እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ። ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።” (ማቴዎስ 10፡28-33)
ክርስትና የሕይወት መንገድ ስለሆነ ክርስቲያን መሆን ውድ ነው፡፡ እስልምና ሰው ሰራሽ ሃይማኖት ስለሆነ ሙስሊም መሆን ቀላልና ርካሽ ነው፡፡ ነገሮች ሲከብዷችሁ ትክዱታላችሁ፤ ሲመቻችሁ አብራችሁ ትጎርፋላችሁ፡፡
ሙሐመድ በአንድ ወቅት ከኣብ ኢብን አል-አሽራፍ የተሰኘውን ሰው ለመግደል የእርሱ ወዳጅ የነበረው ሙሐመድ ቢን መስለማ የተሰኘ ሰው ውሸትን እንዲጠቀም ፈቃድ ሰጥቶት ነበር፡፡ (al-Bukhari Vol 5 Book 59 Num 369)
በእስልምና የሸሪኣ መጽሐፍ ውስጥ እንዲህ ተብሏል፡- it is permissible to lie if attaining the goal is permissible. የሚፈለገው ግብ የተፈቀደ ከሆነ (ትክክል ከሆነ) መዋሸት የተፈቀደ ነው እንደ ማለት ነው፡፡ (Ahmad ibn Naqib al-Misri, The Reliance of the Traveller, translated by Nuh Ha Mim Keller, amana publications, 1997, section r8.2, page 745)
ስለዚህ በዚህ ረገድ ያለው እስላማዊ አስተምሕሮ “የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው” ዓይነት ነው፡፡ እስልምና በምንም መስፈርት እውነተኛና ቅዱስ ከሆነው አምላክ ዘንድ ሊሆን አይችልም፡፡