በሙሐመድ ዘመን ወንጌል በጽሑፍ አልነበረምን

በሙሐመድ ዘመን ወንጌል በጽሑፍ አልነበረምን?

በሙሐመድ ዘመን ወንጌል በጽሑፍ አልነበረም የምትሉ መጽሐፋችሁን የማታውቁ ሙስሊም አፖሎጂስቶች ይህንን አንብቡ:-
“ኸዲጃ ነቢዩን ወደ አጎቷ ልጅ ወደ ወረቃ ወሰደችው… እርሱም ከእስልምና ዘመን በፊት ክርስቲያን የሆነ ሲሆን የእብራይስጥ ጽሑፎችን ይጽፍ ነበር፡፡ አላህ እንዲጽፍ በፈቀደለት መጠን ወንጌልን በእብራይስጥ ይጽፍ ነበር፡፡” (Sahih Al-Bukhari Vol 1, Book 1, No 3)
“ወረቃ ከእስልምና ዘመን በፊት ክርስቲያን የሆነ ሲሆን አላህ እንዲጽፍ በፈቀደለት መጠን ወንጌልን በአረብኛ ይጽፍ ነበር፡፡” (Sahih Al-Bukhari Vol 6, Book 60, Number 478)
በሌላ ዘገባ መሠረት ወረቃ ወንጌላትን በአረብኛ ቋንቋ ያነብ ነበር፡፡ (Sahih Al-Bukhari Vol 4, Book 55, Number 605)
በቁርአን የተጠቀሰው ኢንጅል በክርስቲያኖች እጅ የሚገኝ ካልሆነ ክርስቲያን የነበረው ወረቃ በአላህ ፈቃድ ሲጽፍና ሲያነብብ የነበረው ምን ነበር?