የኢየሱስ አምላክነትና የሊቀ ክህነት ሹመት

 

59. ዕብራውያን 5:5-6 «እንዲሁም ክርስቶስ ሊቀ ካህናት የመሆንን ክብር ለራሱ አልወሰደም፣ ነገር ግን እግዚአብሔር “አንተ ልጅ ነህ! እኔ አባት ሆንኩህ” አለው» በሌላ ስፍራ ደግሞ እንደ መልክ ጼዴቅ ሹመት ለዘለዓለም ካህን ነህ ይላል፡፡ ይህ ጥቅስ ክርስቶስ ሊቀ ካህናት የመሆንን ክብር ለራሱ አልወሰደም» ይላል፡፡ የእርሱ ስልጣን ዘለዓለማዊ ከሆነና ከነበረ እንዴት ከጊዜ በኋላ የመወሰድና ያልመውሰዱ ጥያቄ ይነሳል? በራሱ ባይወስድም ከመውሰዱ በፊት ምን ነበር?

የክርስቶስን ልጅነት ለተመለከተው ጥያቄ በቁጥር 30 ላይ በቂ መልስ ስለተሰጠ አንደግምም፡፡ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ! ክህነቱን በተመለከተ ግን የምንለው ይኖረናል፡፡ ጌታችን ወደ ምድር በመምጣት ሥጋን እስከለበሰበት ጊዜ ድረስ ሊቀ ካህን አልነበረም፡፡ ክህነት እንደ ነቢይነት ሁሉ ለሰው የሚሰጥ አገልግሎት በመሆኑ ከትስብዕቱ በፊት ኢየሱስ ካህን ነበረ ብሎ ማለት አይቻልም፡፡ ከትስብዕቱ በኋላ ይህንን አገልግሎት መቀበሉ ዘለዓለማዊ አምላክ መሆኑን ለማስተባበል የሚቀርብ የሙግት ሐሳብ ሊሆን አይችልም፡፡